የአገሮች ምርት ወደ አባል አገሮች ከቀረጥ ነፃ እንዲገባ በማሰብ ያቀደው ኅብረቱ እክል እንዳጋጠመው መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያም ከቀረጥ ነፃ ከሚገባ የምርት መጠን አንፃር የኅብረቱን የንግድ ቀጣና ስምምነት ሳትቀበለው ቀርታለች፡፡

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የዙምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ 300 ላሞች ለአፍሪካ ኅብረት በስጦታ የሰጡ ሲሆን፣ ካስፈለገ በማለት የላሞቹን ዋጋ አስበው አንድ ሚሊዮን ዶላር ለኅብረቱ በስጦታ መልክ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ስጦታ የኅብረቱን የበጀት ጉድለት ለመሙላት ሌላ አዲስ አማራጭ ሆኖ እንዲቀርብና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎችም ይህን አርዓያ እንዲከተሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በዋናነት በሦስት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ውሳኔ እንዳስተላለፈ የኅብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት በጉባዔው መዝጊያ ላይ ገልጸዋል፡፡ የመጀመሪያው አጀንዳ ኅብረቱን እንደገና ማደራጀት የተመለከተ ሲሆን፣ የአፍሪካ ኅብረትን እንደገና ለማደራጀት የተሰየመውን ኮሚቴ በዋና ኃላፊነት ሲመሩት የነበሩት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፓል ካጋሜ ያቀረቡትን ሪፖርት አድምጦ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ሁለተኛው ርዕሰ ጉዳይ የአኅጉሪቱ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው በሚጎለብትበት ላይ ውሳኔ መተላለፉን ገልጸዋል፡፡ ሦስተኛና የመጨረሻው ጉዳይ በአኅጉሪቱ ሰላምና ፀጥታ በሚሰፍንበት ላይ የኅብረቱ አባል አገሮች ቁርጠኛ ሆነው እንደሚሠሩ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡ በአፍሪካ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ እየተባባሰ የመጣውን አሸባሪነት ለመከላከልም፣ ኅብረቱ በገንዘብ መደራጀት እንዳለበት ስምምነት ላይ መደረሱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

Related stories   "በፕሮፓጋንዳ እስካሁን የተወናበድኩት ይበቃኛል ብሎ ቆም ብሎ ማሰብም ይገባል ... ወጣቱን ያለ እድሜው ህይወቱን ይቀጩታል"ሌ.ጀ ዮሐንስ

በምሥራቅ አፍሪካ በተለይም ከኳታር ቀውስ ጋር ተያይዞ ፍጥጫ ውስጥ ያሉትን ኤርትራና ጂቡቲን ለማሸማገል ኅብረቱ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ኤርትራ ሁለቱን አገሮች በሚያዋስነው ድንበር የተሰየመውን የእውነታ አፈላላጊ ቡድን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነች ለኅብረቱ አገሮች ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ኅብረቱ ይህንን ችግር የሚያጣራ ኮሚቴ በቅርቡ ተቋቁሞ ችግሩን ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት መደረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ጂቡቲ ኳታር የሁለቱን አገሮች አወዛጋቢ ድንበር ጥላ ከወጣች በኋላ የአፍሪካ ኅብረት የእውነታ አፈላላጊ ቡድን እንዲያሰማራ ከመጠየቋም በላይ፣ ኅብረቱ ተጠባባቂ ኃይል እንዲያሰማራ ጥሪ አቅርባለች፡፡ ለዚህም የአፍሪካ ኅብረት በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ብላለች፡፡ ጂቡቲ ኤርትራ አወዛጋቢውን ድንበር ተቆጣጥራለች በማለት ክስ ማሰማቷ አይዘነጋም፡፡ ኤርትራ የእውነታ አፈላላጊ ቡድኑን አልቀበልም ማለቷን ኢጋድ ማስታወቁ፣ የአካባቢውን ሰላም እንዳያደፈርስ ሥጋት ፈጥሯል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና የደኅንነት ኮሚሽነር ኢስማኤል ቼሪጉዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በሁለቱ አገሮች ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተሰምቷል፡፡