https://youtu.be/yjBq7r3_8KQ

እምቦጭ አረም በቪክቶሪያ ሐይቅ፤ – ሙሉቀን ተስፋውእምቦጭ አረም በቪክቶሪያ ሐይቅ

ሙሉቀን ተስፋው

የእምቦጭ አረም በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የቪክቶሪያ ሐይቅ መውረር የጀመረው በ1980ዎቹ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ የእምቦጭ አረም (Water hyacinth) ከ1992 እስከ 1998 ባለው ጊዜ የቪክቶሪያ ሐይቅን ቀላል የማይባል ክፍል መሸፈን ችሎ ነበር፡፡ በ1998 እ.ኤ.አ ከ20 ሺህ ሔክታር በላይ (77 ስኩየር ማይል) የሚሆነው የሐይቁ ክፍል በእምቦጭ አረም ተይዞ ነበር፡፡ እምቦጭ ሐይቁን ከመውረሩና የአካባቢውን ብዝሃ ሕይወት ከማዛባቱ በተጨማሪ ለወባ ትንኝና ለብላሃርዚያ በሽታ አምጭ ተኅዋስ ሺስቶሶማዎች መራቢያ በመሆን የጤና ጠንቅም ሆኖ ነበር፡፡
የታንዛኒያ፣ የኬንያና የኡጋንዳ መንግሥታት በመተባበር ከ1998 ጀምሮ ሐይቁን ለማዳን ተረባረቡ፡፡ የምዕራብ ለጋሽ አገራትም ሐይቁን ለማዳን በገንዘብና በቴክኖሎጅ ጭምር ረድተዋል፡፡ በ2000 መግቢያ ላይ የእንቦጭ አረምን ማጥፋት ባይቻልም መቆጣጠር ችለዋል፡፡

በቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ያለውን የእንቦጭ አረም ለመቆጣጠር የተንሠራፋውን አረም በተለያዩ ቴክኖሎጅ አገዝ መሣሪያዎች ማረም (መንቀል)፣ Neochitina weevil የተባሉ አንበጣ መሣይ ነፍሳትን በማራበት በአካባቢው መበተንና እንቦጭ አረሙን ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል የመሣሰሉ ዘዴዎች ነበሩ፡፡ መንግሥታቱ ከእንቦጭ አረም ባዮጋዝን ጨምሮ የተላያዩ ነገሮችን ማምረትም እንደመፍትሔ ወስደውታል፡፡

እምቦጭ አረምን መቆጣጠር ቢቻልም ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ብዙም ስኬታማ የሆነ አገር የለም፡፡ የቪክቶሪያውን ጉዳይ ስናየው በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረ ቢሆንም በ2007 አካባቢ መልሦ ሐይቁን አልብሶት ነበር፡፡ መንግሥታቱ እንደገና አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ መልሰው ወደነበረበት በመመለስ አስጊ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡

ወደኛው ጣና ስንመጣ ሐይቁ በእምቦጭ መወረር የጀመረው በ2004 ዓ.ም (የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ በተሠራ ማግስት) ሆኖ ይህን ያክል ሲስፋፋ ዩንቨርሲቲዎችም መንግሥትም ከዚህ ግባ የሚባል እርምጃ አልወሰዱም፡፡ አረሙ በእኛ አገር ብቻ የተከሠተ አዲስ ክስተት ቢሆን ምርምር እስኪደረግ ድረስ ብዙ ዘመን መውሰዱ ላይደንቅ ይችል ነበር፡፡ በቅርብ ርቀት እነኬንያና ኡጋንዳ የቪክቶሪያ ሐይቅን ለማዳን የተጠቀሙበትን ልምድ በመቅሰም በቶሎ አረሙን መቆጣጠር ያን ያክል ከባድ የሆነ ጉዳይም አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው ከሕዝብና ከአገር የተጣላ ሥርዓት ስላለን ብቻ ነው፡፡

የእምቦጭ አረም በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የቪክቶሪያ ሐይቅ መውረር የጀመረው በ1980ዎቹ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ የእምቦጭ አረም (Water hyacinth) ከ1992 እስከ 1998 ባለው ጊዜ የቪክቶሪያ ሐይቅን ቀላል የማይባል ክፍል መሸፈን ችሎ ነበር፡፡ በ1998 እ.ኤ.አ ከ20 ሺህ ሔክታር በላይ (77 ስኩየር ማይል) የሚሆነው የሐይቁ ክፍል በእምቦጭ አረም ተይዞ ነበር፡፡ እምቦጭ ሐይቁን ከመውረሩና የአካባቢውን ብዝሃ ሕይወት ከማዛባቱ በተጨማሪ ለወባ ትንኝና ለብላሃርዚያ በሽታ አምጭ ተኅዋስ ሺስቶሶማዎች መራቢያ በመሆን የጤና ጠንቅም ሆኖ ነበር፡፡ የታንዛኒያ፣ የኬንያና የኡጋንዳ መንግሥታት በመተባበር ከ1998 ጀምሮ ሐይቁን ለማዳን ተረባረቡ፡፡ የምዕራብ ለጋሽ አገራትም ሐይቁን ለማዳን በገንዘብና በቴክኖሎጅ ጭምር ረድተዋል፡፡ በ2000 መግቢያ ላይ የእንቦጭ አረምን ማጥፋት ባይቻልም መቆጣጠር ችለዋል፡፡ በቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ያለውን የእንቦጭ አረም ለመቆጣጠር የተንሠራፋውን አረም በተለያዩ ቴክኖሎጅ አገዝ መሣሪያዎች ማረም (መንቀል)፣ Neochitina weevil የተባሉ አንበጣ መሣይ ነፍሳትን በማራበት በአካባቢው መበተንና እንቦጭ አረሙን ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል የመሣሰሉ ዘዴዎች ነበሩ፡፡ መንግሥታቱ ከእንቦጭ አረም ባዮጋዝን ጨምሮ የተላያዩ ነገሮችን ማምረትም እንደመፍትሔ ወስደውታል፡፡ እምቦጭ አረምን መቆጣጠር ቢቻልም ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ብዙም ስኬታማ የሆነ አገር የለም፡፡ የቪክቶሪያውን ጉዳይ ስናየው በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረ ቢሆንም በ2007 አካባቢ መልሦ ሐይቁን አልብሶት ነበር፡፡ መንግሥታቱ እንደገና አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ መልሰው ወደነበረበት በመመለስ አስጊ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ ወደኛው ጣና ስንመጣ ሐይቁ በእምቦጭ መወረር የጀመረው በ2004 ዓ.ም (የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ በተሠራ ማግስት) ሆኖ ይህን ያክል ሲስፋፋ ዩንቨርሲቲዎችም መንግሥትም ከዚህ ግባ የሚባል እርምጃ አልወሰዱም፡፡ አረሙ በእኛ አገር ብቻ የተከሠተ አዲስ ክስተት ቢሆን ምርምር እስኪደረግ ድረስ ብዙ ዘመን መውሰዱ ላይደንቅ ይችል ነበር፡፡ በቅርብ ርቀት እነኬንያና ኡጋንዳ የቪክቶሪያ ሐይቅን ለማዳን የተጠቀሙበትን ልምድ በመቅሰም በቶሎ አረሙን መቆጣጠር ያን ያክል ከባድ የሆነ ጉዳይም አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው ከሕዝብና ከአገር የተጣላ ሥርዓት ስላለን ብቻ ነው፡፡

 

“የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር” ለማቋቋም እና ለአባላት ምዝገባ የቀረበ ጥሪ

ጣና ሃይቅን የወረረዉን እንቦጭ አረም (Water Hyacinth) ለመከላከልና ሃይቁን በዘላቂነት ለመጠበቅ የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር ለማቋቋም የቀረበ የመነሻ ሃሳብ በደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)፣ በባዳዩ የተቀናጀ ዉሃ ሃብት አስተዳደር ረ/ፕሮፌሰር

መግቢያ

ሃሩርና ሃሩር ቀመስ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ የዉሃ አካላት አንዱና ዋነኛ ችግራቸዉ በዉሃ ላይ በሚንሳፈፍ የእንቦጭ አረም (Water Hyacinth) ወይም በሳይንሳዊ ስሙ (Eichhornia crassipes) መወረር ነዉ። አረሙ በመጀመሪያ ከደቡብ አሜሪካዉ የአማዞን ወንዝ እንደተገኘ የሚታመነዉ ይህ ዝርያ በአሁኑ ወቅት በሃሩርና ሃሩር ቀመስ በሆኑ የአለማችን አካባቢዎች ማለትም በደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን፣ በአፍሪካ፣ በደቡብ ምስራቅ እስያና በፓስፊክ አካባቢ ሃገራት በስፋት ተዛምቶ ይገኛል። በሃገራችን ኢትዮጵያም እንቦጭ አረም ባለፉት አምስት አመታት ዉስጥ በጣና ሃይቅ ላይ ተከስቶ ሃይቁን በመዉረር ላይ ሲሆን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከሦሥት አመት በፊት ባካሄዱት ጥናት መሰረት 50,000 (ሃምሳ ሺ) ሄክታር ወይም 500,000,000 (አምስት መቶ ሚሊየን) ካሬ ሜትር ስፋት ያለዉን የሃይቁን አካል ሸፍኖ እንደሚገኝ ሪፖርት አቅርበዋል።

አረሙ በተዛመተባቸዉ አካባቢዎች የመስፋፋት ፍጥነቱ ከፍተኛ ሲሆን ለዚህ ዋነኛ ምከንያቱ ደግሞ ከእርሻ መስፋፋትና የማዳበሪያ አጠቃቀም መጨመር ጋር ተያይዞ ከተፋሰሶች በጎርፍ ተጠርጎ ወደ ሃይቆች የሚገባዉና በዉሃ አካላቱ ዉስጥ የሚገኙ ንጥረ-ነገሮች (nutrients) በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር (eutrophication) ሲሆን አረሙ ተፈጥሮአዊ አጥቂ ጠላት አለመኖሩም ለመስፋፋቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።

በተለያዩ አገሮች ዉስጥ በተሰሩ ምርምሮች ላይ በስፋት እንደተረጋገጠዉ በስነ-ህይወታዊ ዘዴ አረሙን መከላከል ከሌሎች አማራጮች የተሻለ ዉጤታማና ተመራጭ ነዉ። ለምሳሌ በአዉስትራሊያ Neochetina eichhorniae እና N. bruchi የተባሉ ዕፅዋት ተመጋቢ ጥንዚዛዎችን እንዲሁም the moth Sameodes albiguttalis የተባለ የነፍሳት ዝርያን በመልቀቅ እምቦጭ አረምን ዉጤታማ በሆነ መንገድ መቆጣጠር ተችሏል። እነዚህ መንገዶች በሌሎች የደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ አገሮች ላይም ተሞክረዉ በተመሳሳይ ዉጤታማ እንደሆኑ ተረጋግጧል።

በብዙ አገሮች እንደሚታየዉ ሁሉ በጣና ሃይቅ ላይ ያለዉ የአረሙ መስፋፋት በጣም ፈጣን ስለሆነና በአሁኑ ወቅት ከጅምር ያለፈ በቂ የሆነ የስነ-ህይወታዊ የመቆጣጠር ስራ እየተከናወነ አይደለም። እነዚህን የመቆጣጠሪያ መንገዶች ለመጠቀም በቅድሚያ የጎንዮሽ ጉዳታቸዉን የተመለከቱ ምርምሮችን ማካሄድ አስፈላጊ ነዉ። ስለዚህ የአጭር ጊዜ ርምጃዎችን በመዉሰድ አረሙን የመቆጣጠር ስራ መስራት እንደሚገባ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል። የአጭር ጊዜ የመቆጣጠር ስራዎች በአንድ በኩል አረሙ አሁን ያለዉን ፈጣን መስፋፋት ለመቆጣጠር፤በሌላ በኩል ደግሞ ወደፊት ለሚከናዎኑ ስነ-ህይዎታዊ የቁጥጥር ስራዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ በሚል ታሳቢ ነዉ።

በጣና ሃይቅ ላይ ያለዉን አረም ለመከላከል መደረግ ከሚችሉ የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች መካከል በአካላዊ (በማሽነሪ ወይም በሰዉ ጉልበት በእጅ) ዘዴ ማስወገድ እና ፀረ-አረም ኬሚካሎችን መጠቀም ይገኙበታል። ሁለቱንም ዘዴዎች በተለይ በታዳጊ አገሮች ለመተግበር ተግዳሮቶች ይኖራሉ። በማሽነሪ ለማስወገድ ማሽነሪዎችን ወይም ሃርቨስተሮችን መግዛት የሚያስፈልግ ሲሆን ብዙዎቹ አንድም ዉድ ናቸዉ ወይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች በሃገር ዉስጥ ገበያ አይገኙም። አረሙን በእጅ በሰዉ ጉልበት ማስወገድ ደግሞ ብዙ የሰዉ ሃይልና ጉልበት ይፈልጋል። የታዳጊ አገሮች መንግስታት ለዚህ የሰዉ ሃይል የሚሆነዉን የጉልበት ክፍያ የመክፈል አቅም ወይም ቁርጠኝነትና ፍላጎት ላይኖራቸዉ ይችላል። አረሙን እንደ ቱ-ፎር-ዲ እና ግላይፎሴት አይነት ኬሚካሎችን በመጠቀም መቆጣጠር በአንዳንድ አገሮች አዋጭ ቢሆንም ደሃ አገሮች ይህን ማድረግ አዋጭ ላይሆን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ ኬሚካሎችን በዉሃ አካላት ላይ መርጨት በዉሃ አካላት ብዝሃ-ህይወት ደህንነትና ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለሚያደርሱ በብዙ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ ይተቻሉ።

ስለዚህ የችግሩን ግዝፈት ከግምት ዉስጥ በማስገባት በዘላቂነት በጣና ሃይቅ ዙሪያ የሚከናወኑ የእንቦጭ አረምና መሰል ወራሪ ዕፅዋትን ለመከላከል የበጎ ፈቃደኛ ምሁራን፣ ባለሃብቶች፣ ወጣቶች፣ የማህበረሰብ ድርጅቶችንና ሃላፊነት የሚሰማቸዉን ተቆርቋሪ ዜጎች ለማስተባበር የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የማህበሩ ዓላማና ግብ

ጣና በኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ ሲሆን ለአባይ ወንዝም ዋነኛዉ የዉሃ ፍሰት ምንጭ ነዉ። ሃይቁ ለቱሪስት መስህብነት፣ ለሃይል ማመንጫ፣ለመስኖ እርሻ፣ለመጓጓዣ እንዲሁም ለአሳ ምርት ምንጭ በመሆን ለአካባበዉ ማህበረሰብም ሆነ ለሃገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ይህንን የሃይቁን አስተዋጽኦ በዘላቂነት ለማስቀጠል የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ጎን ለጎን የተደራጁ የማህበረሰብ ድርጅቶች (ሲቪል ሶሳይቲዎች) ጠቃሚ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የበጎ አድራጎት ማህበራት ምዝገባ ክፍል ለማጣራት እንደተሞከረዉ ከዚህ በፊት ሁለት ድርጅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ለመስራት ፈቃድ ቢወስዱም እሰከአሁን ድረስ አጥጋቢ እንቅስቃሴ አላደረጉም። ስለዚህ የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር በሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች ዙሪያ ጠንካራ እንቅስቃሴ ለማድረግ አስቧል፤

1) በጣና ሀይቅ ላይ የተዛመተዉን እንቦጭ አረምና ሌሎች ወራሪ ዕፅዋቶችን የመቆጣጠር ስራን ማገዝ

2) የሃይቁን ጥበቃና እንክብካቤ አስመልክቶ የአድቮኬሲና የማህበረሰብ ትምህርት መስጠት፣

3) ለጣና ሃይቅ ጥበቃና እንክብካቤ በጎ አድራጊ ባለድርሻ አካላትን ማስተባበርና ተያያዥ ስራዎችን መስራት

4) በጣና ሃይቅ ላይ የሚከናወኑ የተቀናጀ የዉሃ ሃብት አስተዳደር ስራዎችን መደገፍ ናቸዉ። ከላይ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች በማሳካት የሃይቁ የዉሃ ጥራትና መጠን ተጠብቆ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲሸጋገር ማድረግ የማህበሩ ግብ ነዉ።

የማህበሩ ህጋዊነትና አደረጃጀት

የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ህግ መሰረት እንዲቋቋም የሚደረግ ሲሆን የሚከተሉት አደረጃጀቶች ይኖሩታል፤

1) ጠቅላላ ጉባዔ

2) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

3) የማህበሩ አባላት

4) የማህበሩ አማካሪና ስራ አመራር ቦርድ

የማህበር ምስረታ ጥሪ

ማህበሩን ለማቋቋም የማህበሩ መመስረቻ ረቂቅ አጀንዳ (7-ገፅ) ፣ መተዳደሪያ ደንብ (14- ገፅ) ፣ የጊዜያዊ ስራ አስፈፃሚ አመራሮች የህይወት ታሪክ ፎርም (1-ገፅ) እንዲሁም የማህበራት ምዝገባ ማመልከቻ ቅፅ (4-ገፅ) አዘጋጅተናል። ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን የማህበሩን ዓላማ የሚደግፍና ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ የአካባቢዉ ተወላጆች፣ ምሁራን፣ ባለሃብቶች፣ ወጣቶችና አርሶ አደሮች እንዲሁም ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለመስራች አባልነት እንድትመዘገቡ ተጋብዛችኋል።

ለምዝገባና ለማንኛዉም ጥያቄ ወይም አስተያየት፡-

በተንቀሳቃሽ ስልክ (+251) 918 764 279 ፡- ደሳለኝ ጫኔ ወይም
በ Email: cdessalegn@yahoo.com ወይም
በ Facebook መልዕክት (ለ Dessalegn Chanie Dagnew)

ሙሉ ስም፣ ፆታ፣ ዕድሜና ስልክ ቁጥር በመላክ መመዝገብ ይቻላል።

ማህበሩ በይፋ የሚመሰረትበት ቀን ወደፊት በስልክና በፌስቡክ ይገለጻል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *