Eskinder Kebede Abebe  – ( እስክንድር ከበደ)

አፉወርቅ ተክሌ 2የሥነ ጥበብ ሊቁ አፈወርቅ ተክሌ ጥበብ ሰዎችን ለማነቃቃትና አገራዊ ስሜትን ለማነሳሳት እንዲሁም ስለህይወት ብሩህ ተስፋ ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጥልቅ እምነት ነበራቸው፡፡

ወደ እንግሊዝ በመሄጃቸው የመጨረሻ ደቂቃዎች በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ቤተመንግስት ተጠርተው ከቀረቡት ተማሪዎች አንዱ የሆኑት አፈወርቅ ተክሌ ፤ ንጉሱ የለገሷቸውን ምክር ፈፅሞ አይረሱትም፡፡ “ጠንክራችሁ መስራት አለባችሁ፤ ስትመለሱ በአውሮፓ ስላያችኋቸው ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ወይም ሰፋፊ መንገዶች እንድትነግሩን አንፈልግም፤ ይልቁንም ኢትዮጵያን ዳግም ለመገንባት በሚያስፈልገው ክህሎትና አስተሳሰብ ራሳችሁን አስታጥቃችሁ መመለሳችሁን እርግጠኛ ሁኑ” ሲሉ እንዳሳሰቧቸው በአንድ ውቅት ተናግረው ነበር፡፡ይሄ ምክር አገራቸውን ከመገንባትና ህዝባቸውን ከማነሳሳት የሃላፊነት ተግባር ነፃ የሆነ ቀላል ህይወት በተፈታተናቸው ቁጥር፣ በአዕምሮአቸው ውስጥ ያንቃጭልባቸው እንደነበር አፈወርቅ ያስታውሳሉ፡፡

በእንግሊዝ ት/ቤት ከመጀመርያዎቹ አፍሪካውያን ተማሪዎች አንዱ የነበሩት አፈወርቅ፤ ቀድሞውኑም ስሜታቸውና ፍላጐታቸው ወደ ነበረው ሥነጥበብ እያዘነበሉ ሄዱ፤ ተሰጥኦዋቸውም እየጐላ መታየት ጀመረ፡፡ ከዚያም ለንደን ውስጥ የሚገኘው የሥነጥበብና የኪነጥበብ ማዕከላዊ ት/ቤት ተቀበላቸው፡፡ በተቋሙ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በዝነኛው የለንደኑ “ስሌድ” የስነጥበብ አካዳሚ የመጀመርያው አፍሪካዊ ተማሪ በመሆን ትምህርታቸውን ተከታትለው አጠናቀቁ፡፡ አፈወርቅ በ”ስሌድ” ኮሌጅ ሳሉ ትኩረታቸውን ያደረጉት ስዕል፣ ቅርፃ ቅርፅና ሥነ ህንፃ ላይ ነበር፡፡አፈወርቅ በእንግሊዝ እየተማሩ ሳሉ በሌሎች የአውሮፓ አገራት እየተዟዟሩ አያሌ የሥነጥበባት መዲናዎችን በመጐብኘት ጠቃሚ ልምዶችን ቀስመዋል፡፡አፉወርቅ ተከሌ 1.jpg

በአፍሪካ አዳራሽ መግቢያ ክፍል ውስጥ ጐብኝውን ከፊት ለፊት የሚቀበለው ዓለም አቀፋዊ ዝናን ያተረፈው የመስኮቶች መስታወት ቅብ ሥዕል ነው፡፡ በ150 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የተንጣለለው ሥዕል በሦስት ሰሌዳዎች ያለፈውን የአፍሪካ አሳዛኝ ታሪክ፣ የወቅቱን ትግልና ለወደፊቱም አፍሪካ ለአንድነት ያላትን ፍላጎትና ጉጉት ያሳያል፡፡

በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ መግቢያ ላይ ‹‹አፍሪካ ያኔ፣ አፍሪካ አሁን እና አፍሪካ ወደፊት›› የሚለው የመስታወት ላይ ሥራቸው ዓለም አቀፋዊም አድናቆት ብቻ ሳይሆን ከፍ ላለው ‹‹ወርልድ ሜዳል ኦፍ ፍሪደም›› የተሰኘውና ከአስርት ዓመታት ወዲህ የተመሠረተውን ሽልማት ተጎናጽፈዋል፡፡ ፡ ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ በሥነ ጥበብ ሥራቸው ውስጥ ስለ ሰው ልጅ የመንፈስ ነፃነት፣ የሰው ልጅ የሌላ ዓይነት መጥፎ ሐሳብ ባርያ አለመሆንን፣ የሰው ልጅ ወደ ሰላምና ወደ አንድነት የሚመራ በአንድ ሥራ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሥራ ውስጥ ይታያል ብለዋል፡

እ.ኤ.አ በ2009 በግዙፉ የአሜሪካ ኮንግረስ ቤተ መጽሃፍ The State of Art in Ethiopia ” በሚል ዲስኩራቸው በአፍሪካ አንድነት ድርጅትና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ውስጥ የመስታወት ላይ ስእሎች ያሰታውሳሉ።

የአፍሪካ አንድነት” ….ECA አዳራሽ ለመክፈት ጥድፊያ ነበር።በወቅቱ ህንጻውን ስራ ጣሊያናዊው ሜዚዲፒ ይቆጣጣር ነበር።ህንጻው ሊከፈት ሲቃረብ የመስታወት ላይ ስራው ለጣሊያናዊ የፔሩዚያ አርቲስት ተሰጥቶ ነበር፡፡ በአጋጣሚ ጣሊያንን አውቃታሉ፡፡ከማቃቸው የዘመኑ ዝነኛ ሳአሊያን ዝርዝር ውስጥ የዚህ ሳአሊ ስም ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡በወቅቱ 300ሺህ ብር ሊከፍሉት ነበር የተስማሙት ። በዘመኑ ብዙ ገንዘብ ነበር፡፡ይህንን ካሸነፍኩ በእድሜ ዘመኔ አይችግረኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ጠንክሬ መስራት እንዳለብኝ እና በውድድሩ መሳተፈ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ንጉሱን ስጠይቃቸው ስራው ቀድሞ መስጠቱን ነገሩኝ፡፡አርክቴክቱ ተጠርቶ ተጠየቀ ። “ለምን እንዲህ አደረክ? ጉዳዩ የአፍሪካ ነው።” ብለው ጠየቁት፡፡” በማለት አፈወርቅ ተክሌ ይናገራሉ፡፡
አርክቴክቱ Stained glass(የመስታወት ላይ ስእሎች) ጥበብን የሚያውቅ ወይም የሚችል አፍሪካዊ እንደሌለ÷ ጥበቡ የአውሮፓውያን መሆኑን በመግለጽ ለንጉሱ ያስረዳቸዋል።አርቲስት አፈወርቅ ግን ጥበቡ ከእውሮፓ በፊት እዚሁ አፍሪካ ውስጥ በግብጽ ከ5ሺሕ አመታት በፊት መጀመሩን ይነግራቸዋል፡፡

“ንጉሱ አንተ እድሉ ቢሰጥህ ትችለዋልህ?” ብለው አፈወርቅን ይጠይቃሉ።

ወጣቱ አርቲስት አፈወርቅ ተክሌም ጥበቡን በሚገባ እንደተማረው እና እንደሚችለው ይናገራል።

አርክቴክቱ ሌላ መከላከያ ይዞ ብቅ አለ። ለንጉሱ ECA በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ስለሚከፈት ጊዜ የለንም አላቸው ።
“እርግጠኛ ነህ በስድስት ወር ውስጥ ትጨርሰዋልህ?” ብለው አርቲስት አፈወርቅን በድጋሚ ይጠይቃሉ።

“በእርግጠኝነት እሰራዋለሁ !”
ንጉሱ የጥበብ ውድድሩ ላይ በመላ አፍሪካ የሚገኙ አርቲስቶች እንዲሳተፉ እና የመወዳደሪያ ሰራቸውን በ30 ቀናት ውስጥ እንዲያቀርቡ ጨረታ ወጣ፡፡ ወጣቱ አርቲስት አፈወርቅ ቤቱን ዘግቶ የመወዳደሪያ ስራውን በ12 ቀናት አጠናቀቀ።

ከ30 ሀገራት ሰራዎች ቀረቡ ።ከ17 ዳኞች ውስጥ 14 የሚሆኑት (ከጣሊያን ፔሩጃ የመጣው ዳኛ ሳይቀር) የአፈወርቅ ተክሌን ስራ መረጡ፡፡ ንጉሱ በተገኙበት የአርቲስት አፈወርቅ ተክሌ አሸናፊ መሆኑ ተበስረ።
አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ስራውን በሚገባ አጠናቀቀ፡፡ንጉሱ ሳይቀሩ “እጅህ ይባረክ” አሉ፡፡ 300ሺህ ብር ለዛ የውጭ አርቲስ የተያዘው ብር እንዲከፈላቸው የጠየቁት አርቲስቱ÷ ግን አንዲት ሳነቲም ክፍያ አላገኙበትም።ንጉሱ ጥያቄውን አይታችሁ ምላሽ ስጡት ያሉት ሚኒስትሮች ያሉብት ኮሜቴ ተሰብስቦ ወሰነ፡፡ “አንተ ማንም ያላገኘውን ነጻ የትምህርት እድል ያገኝህ ነህ፡፡ስለዚህ ለሀገርህ እንደ እስተዋጽኦ ይቆጠራል በሚል” ድፍን ያለ ምላሽ በመስጠት ክፍያው ሳይፈጸም ቀረ፡፡

በዚህ ስራ የተደነቁት የጋናው ፕሬዚዳንት ክዋሜ ኑክሩማ ወደ ጋና መጥትህ የሀገሬን ፓርላማ ውስጥ ስእል እንድትስል እፈልጋለሁ በሚል ወጣቱን አርቲስት አፈወርቅ ይጋብዛሉ። አርቲስቱ በቅድሚያ ንጉሱን አስፈቅዱ ይላቸዋል።የንክሩማን ጥያቄ የሰሙት ንጉሱ በሌላ ሰው “እዚህ በቂ ስራ እጥትህ ነው ጋና ለመሄድ ያሰብከው? ” የምትል መልክት ይልካሉ። በተዘዋዋሪ “አልፈቀድኩም” ማለታቸው ገባው፡፡

ምስጋና ስንዱ አበበ ፌስቡክ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *