ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የሳዑዲ አዋጅ ምርኮኞች !! “ቆንጆዎቹ ” ለምን ዝም ይባላሉ ?! ‘ምን ይዤ ልመለስ ‘ የችግሩ ቁልፍ !!

ITALY - SICILY - MAY 3: Migrants are seen on a Italian Navy vessel during Italian coast guard's search and rescue operation for the migrants trying to reach Europe, in Mediterranean Sea near Italy's Lampedusa on May 3, 2015. The Italian coast guard, merchant ships and Navy vessels saved as many as 3,690 migrants trying reach Italy from Africa over the weekend, officials said Sunday. The thousands of migrants saved arrived in the Sicilian and Calabrian ports Sunday and Monday. (Photo by Italian Navy/Anadolu Agency/Getty Images)

Related image

ዛጎል ዜና – ” ቆንጆዎቹ ” ስል ስም የሰጠሁዋቸው አረብ አገር ሰዎችን በመላክ የተደላደለ ህይወት የሚገፉትን ነጋዴዎች ነው። ቆንጆዎቹ ባለ ላንድ ክሩዘር፣ ባለ ቢኤምደብሊው፣ ባለ …. ናቸው። ኑሯቸው የተንቀባረረ፣ ብር የነፋቸው ስግብግቦች ናቸው። አብዛኞቹ የሙስሊሙን እምነት መሪዎች፣ አመራሮችና “አስፈላጊ” የሚባሉ ክፍሎችን የተንተራሱ ልዩ ዜጎች ናቸው። የአሁኑ ባይታወቅም ቀደም ሲል ራሳቸው የመጅሊሱ መሪዎችም የዚሁ ንግድ ፊት አውራሪዎች ነበሩ።

በአንድ ወቅት እነ ሃጂ ኤሊያስ አመራር ላይ በነብሩበት ወቅት የከርስ ውዝግብ ተነስቶ እንደ ነበር የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ያስታውሳል። በወቅቱ የተነሳው ውዝግብ ” ብቻዬን ልብላ” የሚል ይዘት ያለው ነበር። በወቅቱ የነበሩት የመጅሊስ አመራሮች ሳዑዲ በመሄድ የጽሎት ጉዞን ተገን አድርገው የጉዞውን ሁኔታ፣ የቲኬት፣ የምዝገባና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለማከናወን ክሚመለክተው አካል ጋር ሄደው ተስማሙ። ከስምምነቱ በሁዋላ ቀደም ሲሉ የነበሩትን ላኪዎች በጠረባ አሉዋቸው።

የሳዑዲን የጸሎት ጉዞ ተጓዦችን በኮታ ተቀራምተው የጉዞና የቆይታ ሂደት ሲያካሂዱ የነብሩት የጉዞ ወኪሎች በጠረባ መባላቸውን ሲሰሙ ተደናገጡ። የዚህን ጊዜ በቡድን ዘመቻ ጀመሩ። ወደ ተለያዩ ሚዲያዎች ሄደው ሚስጥሩን ያራግፉት ጀመር። ከመጅሊሱ አመራሮች ውስጥ አራትና አምስት የጉዞ ወኪል / ትራቨል ኤጀንሲ/ ያላቸው እንዳሉ ስም እየተቀሱ ይወነጅሉ ጀመር።

ይህ የተካረረና በበጀት የተደገፈ ውዝግብ ማህበራዊ ጉዳይ የወቅቱ ሚኒስትር፣ እንዲሁም ከፍተኛ የሚባሉት መሪዎች ዘንድ ደረሰ። ከላይ እንደተባለው ሁሉም ከጀርባ ታኮ ስላላቸው ውዝግቡ ከሁሉም አቅጣጫ ተገን የነበረው በመሆኑ እልባት አልባ ሆኖ ቆየና በመጅሊሱ አዲስ አመራሮች በግልጽ ባልታወጀ አሸናፊነት ተቋጨ። ለእምነት በሚል ስም የሚደረገው ጉዞ ከአገር መውጫ መሆኑ በግልጽ እየታወቀ አንድም አካል በሳኡዲ አረቢያ የመኖሪያ ህጋዊ ፈቃድ ጉዳይ አሳስቦት አያውቅም። ምክርም ሲለግስ አይሰማም ነበር።

የጉዞውን ሂደት ለማቀናበር ኮንትራት የተፈራረሙት ክፍሎች በሞኖፖል ስለያዙት የቲኬት ውድነትና፣ አማራጭ ማጣት ጉዳይ ያሳሰባቸው ተጓዦች በወቅቱ የእርሻ ከብት ሸጠው፣ ሰርተው ለመክፈል መሬታቸውን አሲዘው፣ አራጣ ተበድረው፣ የቤተስብን ቅሪት ተጠቅመው እንደሚጓዙ በመጥቀስ የ ” መሪዎቻቸውን” ስግብግብነት ይናገሩ ነበር። ከዚሁ ወቀሳ ጋር በማያያዝ አንድ የጉዞ ወኪል በሚሊዮን ብሮች እንደሚያገኝ ይፋ ሆኖ ነበር። እዚህ ላይ አስቡት አራትና አምስት የጉዞ ወኪል ያለው የሃይማኖት ” መሪ” ስንት እንደሚያገኝ? በዓመት ሁለቴ!! በየዓመቱ፣ ከስልጣን እስከሚወርድ… ጉድ ነው!!

በጠረባ የተመቱት የአስጎብኚ ድርጅቶች መስጊድ፣ አሜሪካን ግቢና ወደ ቢስ መብራት አካባቢ ባሉት ህንጻዎች የተሰገሰጉ ሲሆን የተለያዩ የአረብ አገሮች ስራ እናስቀጥራለን እያሉ የሚልኩና በእርግጥም የናጠጡ ናቸው። ፊታቸው ሊፈርጥ የደረሰ፣ በብር የሚያስቡ፣ ሁሉንም ነገር በብር ማከናወን የሚችሉ፣ ቁልፍ የሆኑ ሰዎች ከየ አየነቱ ያላቸው የከተማው ማፍያዎች ናቸው። በውድ ዋጋ በሚሸጡ ተሽከርካሪዎቻቸው እየተግተለተሉ ሲራወጡ ላያቸው የሆዳቸውን ሰፊነትና ሃዘኔታ የሚባል ነገር የደረቀባቸው ዓይነት ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ ከባድ አይደለም።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

በዚህ ሳቢያም ይሁን በሌላ በየስርቻው ያሉትን ጨምሮ፣  ምን አልባትም ” ግብር የማያስገቡ” ሊሆኑ ይችላሉ ” ሀገ ወጥ” ተብለው ታሰሩ ተባለ። ከዛም መንግስት ህጋዊ ያላቸው አዳዲስ ኤጀንቶች ብቅ አሉ። ቢሯቸውን አደባባይ መሃል ከተማ ከፈተው ህዝብ ለሊት ወረፋ ሲተብቅ እያደረ ይመዝገብ ጀመር። የሕዝቡ ግፊያና የህዝቡ ብዛት አንድ ተዓምር የወረደ፣ ወይም ንግስ ያለ እስኪመስል ድረስ የሚቀዘቅዝ አልሆነም ነበር። በሁዋላ ላይ ” መስክረምን ያያችሁ?” የሚል ዜማ ተሰማ።

ይህ ተመዝግበው የሚሄዱትን ለማንሳት ያህል ነው። በበረሃና በባህር ድንበር እያሳበሩ የሚጓዙትን ወገኖች ብዛትና / ከሞት የተረፉትን ለማለት ነው/ ቤቱ እንጂ ማንም ሊያውቀው አይችልም። ሆኖም የሳዑዲ ሰዎች እንደሚሉት በተለያዩ ወንጀሎ የተጠረጠሩና ውል በማፍረስ  በአሁን ከ50 እስከ 60 ሺህ የሚጠጉ እስረኛ ወገኖች በማጎሪያ ቤት አሉ። በ2008 – 2009  ብቻ 89,800 የሚሆኑ ዜጎች ዲፖርት / ወደ አገራቸው ተይዘው ተመልሰዋል። ይህ እንግዲህ በቀን ብቻ 246 ሰዎች ተባረዋል ማለት ነው። ከዚህ ቁጥር የምንረዳው የችገሩ ግዝፈት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ነው።

ተጠያቂው ማን ነው? ምነው እኛ ብቻ!! 

በሳዑዲ ተቀጠርው ስራ የሚሰሩት ወገኖች ኢትዮጵያዊ ብቻ አይደሉም። የተለያዩ አገር ዜጎች አሉ። ፊሊፒንስና ማሌዥያ ዜጎቻቸውን የሚከታተል በሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተደራጀ አካል እንደሰየሙ መረጃዎች ያሳያሉ። ወተለያዩ የማህበራዊ አውታሮች ዋትስ አፕን ጨምሮ ሁሉንም አቆራኝተው አንዱ ስለ አንዱ መረጃና በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርገዋል። በዚሁም መሰረት አንድ ዜጋ ችግር ሲያጋጥመውም ሆነ እርዳታ ሲያሻ ወዲያው ከተፍ ይሉለታል።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ቆንስላ በተለይ የጅዳው ብዙ ያታማል። ለቆንስላው አሰራር ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት ልክ እንደ መጅሊሱ ሰዎች ቆንስላ ጽህፈት ቤት እየሰሩ ንግድ ውስጥ የገቡና የጠገቡ አሉ። ይህ በቂ ክትትልና ምርመራ የሚያሻው ቢሆንም የመረጃ ሰዎች ግን እርገጠኛ ናቸው። በስፋርው የተገኙ ጋዜጠኖችም ይህንን መታዘባቸውን በጓሮ ሲያሙ ይደመጣል።

ታዲያ እውነታው ይህ ከሆነ በሳዑዲ ዜጎች ለሚደርስባቸው ችግር ተጠያቂው ማን ነው። ላለፈው ጥፋትስ ማን ፊት ለፊት ይቅረብና ይናዘዝ? ድንበር ሰብረው የገቡት የራሳቸው ጉዳይ ቢባሉ እንኳ በ ” ህጋዊ” የሄዱትን ወገኖች ህግና ስርዓት እንዲሁም የተለያዩ ምክሮችን ለግሶ የሚከታተል አካል አለ? ኤጀንቶች ቢሮ ከፈተው ይህንን መስራት እንዳለባቸው አስገዳጅ ህግ ሆኖ ሳለ ስንቶቹ ቢሮ ከፍተው እለታዊ ክትትል ያደርጋሉ?

Related stories   የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዲስ የአደረጃጀት ሰነድ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀረበ

ሌላው ትልቁ ጉዳይ ከአሰሪዎቻቸው ዘንዳ የሚጠፉት ሰዎች ጉዳይ ነው። አሁን የማባረሪያው አዋጅ ከወጣ በሁዋላ መንግስት አዲስ የስራ ውል መፈራረሙን ይፋ አድርጓል። በዚሁ ውል መሰረት የአንድ ሰው ደሞዝ 800 ሪያል ነው። በተመሳሳይ የሌሎቹ አገሮች ለምሳሌ የፊሊፒንስ ዜጎች የተገባላቸው ውል 1500 መሆኑንን መረጃዎች ያሳያሉ። እኛ ምን ስለሆን ባነሰ ደሞዝ እንድንሰራ ስምምነት ይደረሳል ሲሉ ጥያቄ የሚያነሱ አሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ውል እያፈረሱ ከአሰሪዎቻቸው የሚተፉ ሰራተኞች አንድም የተሻለ ደሞዝ ፍለጋ፣ አለያም ከግንዛቤ ችግር መሆኑ ይነሳል።

ከላይ እንደተባለው የሚከታተላቸውና ችግር ሲገጥማቸው መፈትሄ የሚፈልግ ክፍል ባለመኖሩ ዜጎቻቸን ሲከፋቸው አማራጭ የሚያደርጉት ሽሽትን ነው። ሌላ ቦታ ሄዶ መስራትን ነው። እዚህ ላይ ታዲያ ኤጀንቶች በገቡት ውል መሰረት ቢሮ ከፈተው እለታዊ የመገናኛ መረብ ዘርገተው ባለመስራታቸው ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂ የማይሆኑት ለምንድን ነው? የሚል አንኳር ጉዳይ የሚያነሱ ክፍሎችን እንዴት ልክ አይደሉም ሊባል ያቻላል?

አስካሉካ ትሬዲንግ በህጋዊ የአገሪቱ ባንክ አካውንት ከፍቶ፣ በአገሪቱ ቲቪ ማስታወቂያ እያሰራ ብር ሲያፍስ ከጅምሩ የተቃወሙና፣ ” እንዴት ነው ነገሩ?” በሚል ቀድሞ የገባቸው ሲናገሩ ሰሚ አልነበረም።  በሁዋላ ላይ ገንዘባቸውን የተበሉ የተከረቸመውን ቢሮ ከበው እዛው በቆሎ እየጠበሱ ሲያድሩ፣ የተቀሩትም ወፍጮ ቤት እያደሩ የአገር ያለ ሲሉ፣ የእርሻ በሬያቸውን፣ መሪታቸውን፣ ቤታቸውን በመሸጥና በማስያዝ የከፈሉት ገንዘብ አንገብግቧቸ ራሳቸውን ያጠፉ ሰዎች ጉዳይ የሚዘነጋ አይሆንም። መጨረሻ ላይ ይህንን ሁሉ የሰራው ሰው ቢያዝም!!

ይህ ብቻ አይደለም። መርካብ ላይ ስራ እናስቀጥራን በሚል አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ ቢሮ ከፍተው የዘረፉ ” ትልልቅ” ሰዎች ጉዳይ የሚዘነጋ አይደለም። ለሜዲካልና ለፎቶ የራሳቸው ሰው ጋር በመላክ የተዘረፈው ብር …. ይህንን ሁሉ የምናነሳው በዚህ በውጭ የስራ ጉዳይ ያለውን ውስብስብ ጉዳዮች ያነሳነው ሳዑዲ አረቢያው ያሉት ሆኑ የተመለሱት ሰዎች ጉዳይ የተወሳሰበ መሆኑንን ለማሳየት ነው።

በተለያዩ መልኩ ከሚሰሙት ድምጾችና በትክክል እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ዜጎቿን አብልታ ማሳደር አልቻለችም። እንኳን ስራ አጥ የሚሰሩትም የኑሮ ካርታ ጠፍቶባቸዋል። ታዲያ እነዚህ ጥሪታቸውን ለቆንጆዎቹ አስረክበው፣ ሰርቼ አገኛለሁ በሚል ተስፋ በቤተሰቦቻቸው ጉሮሮ ላይ ቆመው ባህር የተሻገሩት ወገኖች ወደ ኢትዮጵያ እንዴት ይመለሱ? በሌላ ቋንቋ ” ምን ይዤ ልመልስ?” የሚለው ጥያቄ መልስ አልባ ሆኖባቸዋል።

አገራቸው ቢመለሱ ያላቸውን ተስፋና የሚጠብቃቸውን ጉዳይ ስለሚያውቁ ፣ ምን አልባትም እዛው ሆነው የመጣው ይምጣ ቢሉ ጥፋተኛ ተደርገው ሊወሰዱ እንደሚቹሉ አድርጎ ማሰብ ሊከበድ ይችላል። 8 ሚሊዮን ችጋር የጠበሳቸው ወገኖች ባሉበት፣ አፍጦ የሚጠበቀው ቤተሰብ፣  የአገሪቱ የውስጥ ፖለቲካና የዘር ሽኩቻ ከድህነቱ  ከሚፈጥረው ተስፋ መቁረጥ ጋር ተዳምሮ  ሰው ሞቱን ቢመርጥ ብዙም አይገርምም የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ትክክል ናቸው ባይባልም መነሻቸውና ለማለት የፈለጉት ጉዳይ ግን ትርጉም አልባ አይሆንም የሚል መከራከሪያ ማቅረብ አይቻልም።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

ከሁሉም በላይ የሚያሳስበው  ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ኬንያ ህገወጥ ስደተኛ እንደሌላቸው መስማት ነው። እነዚህ የባህር በር ያላቸውና ወደ ሳዑዲ ለመኮብለል የተሻለ አማራጭ ያላቸው አገር ዜጎች እያሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ስደት መምረጣቸው ነው። 80 በመቶ የሚጠጉ ዜጎች በሳዑዲ ህገ ወጦች እንደሆኑ ይነገራል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑና በሳዑዲ የሚኖሩ የመንግስት ሰዎች እንደሚሉት ከዘጠኝ ጊዜ በላይ እየተያዘ ቢመለስም በባህር የተመለሰ ዜጋ አለ። እነዚህ ክፍሎች እንደሚሉት ” ሰው እንዴት በባህር ላይ ከዘተን ጊዜ በላይ ከሞት ጋር ይሳፈጣል?” ይህ ምሳሌ ከላይ ” የመጣው ይምጣ” የሚሉትን ክፍሎች መውቀስ አግባብ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው።

አውሮፓ ያሉ ስደተኞች ወደ አገራቸው ከመመለስ በስደተኛ ካምፖች ውስጥ መኖርን የሚመርጡት ኑሮው የሚያጓጓ ሆኖ ሳይሆን አሁን ያለው የአገሪቱ ሁኔታ የሚጋብዝ ባለመሆኑ ነው። አንድ 11 ዓመት ስደት ካምፕ ውስጥ የኖረና የአዲስ አበባን ከተሞች ስም የረሳ ስደተኛ “ለምን አትመለስም”  የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ” የት? ኢትዮጵያ? ብሄሬን እኮ አላውቀውም” የሚል መልስ ነው የመለሰው።

እዚህ ላይ የአውሮፓውንና የአረብ አገሩን ሁኔታ ለማመሳሰል ሳይሆን መንግስት ዜጎች አሁንም ድረስ ሰዎ ወደ ፈረሰችው የመን፣ ወደ እሳትዋ ሶማሊያ፣ ወደ ደቡብ አፈሪካ …. ሲፈልሱ፣ ወገኖቻችን ወደታረዱባት ሲኦል ሊቢያ ሲያቀኑ፣ ሰዎች በባህር እየሰመጡ ባህር ላይ ለመውጣት ሲሽቀዳደሙ….. ምን እየሆነ ነው? በሚል ችግሩን ሊፈትሽ እንደሚገባ፣ ከሁሉም በላይ ቆንጆዎች ለነዋይ ሲሉ ከመንግስት ሹመኞችጋር ሆነው ለአቅመ አዳም ያልደረሱትን ወገኖች በማጋዝ የሰሩትን ግፍና ወንጀል መርምሮ ፍርድ መሰጠት ተገቢ ይሆናል። ቴዲ አፍሮ ” ምን ይዤ ልመልስ ወደ እናቴ ቤት” ሲል ያዜመው እዚህ ላይ ልብ ይሏልና ወገንም ወገንን ለማቋቋም ሊተጋና እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ ብዙዎች ይስማማሉ። በህረት ችግሩን ለመቋቋም ግን ህብረት የሚገነባ ትሥሥር የሚፈጠርበት አግባብ ስለመኖሩ ግን ሁሉም ወገን ይጠራጠራሉ!! ምንም ዓይነት ጥርጥር ቢኖርም ግን መመለሱ ግድ ነውና ጉዳዩ  ብሔራዊ አጀናዳ ይሁን!!