“ ‘ሕይወት ቢራቢሮ’ የተሰኘችው ግጥሜ በጋዜጣ ታትማ በወጣች ማግስት መንግሥቱ ለማ ከቢሮዬ መጥቶ፣ ‘ቢራውን እስቲ አምጣው ወይስ ዝም ብለህ ነው ቢራ ቢሮ ያልከው!’ ብሎ እንደቀለደብኝ ትዝ ይለኛል … አሁን እኮ ደማም ቋንቋ የሚናገር ሰው ሁሉ ጠፋ” ብለው ጋሽ ጸጋዬ ትክዝ አሉ።

via ውሎ ከጋሽ ጸጋዬ ጋር — አንድምታ

“ውሎ ከጋሽ ጸጋዬ ገብረመድኅን ጋር”

ከግርማ መኮንን

.

በአካልም በስሜትም ከሀገሬ በጣም መራራቅ ጀመርኩ መሰለኝ ትዝታዎቼ ከአምስቱም የስሜት ሕዋሳቶቼ መፍለቅ ጀምረዋል።

ሰው ሁሉ አፍንጫውን ዘግቶ መንገድ ለመሻገር እንደመንጋ ሲንጋጋ እኔ እርምጃዬን ገታ አደርግና ፖሊሱ ወደተቀመጠበት ፈረስ አቅራቢያ ስደርስ ደረቴ እስኪወጠር ድረስ አየሩን እስባለሁ። የፋንድያው ሽታ እኔን የሚያስታውሰኝ ሰፈሬን ሽሮሜዳን ነዋ! እሱም ቢሆን እኮ ይናፍቃል። አዘውትሬ የምሄድበት ቡና ቤትም በአንድ ጥግ በኩል ኮርኒሱ ተቦርድሷል … ያደግኩበት ቤትም እንደዚሁ።

ጆሮዬም ቢሆን የሚናፍቀው የራሱ የሆነ ትዝታ አለው።

አሁን አሁን የእግር ኳስ ጨዋታን እምብዛም ባልከታተልም አንዳንዴ የስፖርት ዘጋቢዎቹ “ጎል!” ብለው ሲጮሁ ለመስማት እጓጓለሁ። እሷን በሰማኹ ቁጥር ትዝ የሚለኝ አባቴ ነው። እኔና ወንድሜ ሕፃን እያለን በሳምንት እንዴ የሚተላለፈው የእንግሊዞች ኳስ ጨዋታ እንዳያመልጠን ተንደርድረን ከሶፋው ላይ ጉብ እንላለን። የኛም ልብ እንደተሰቀለ አይቀርምና አንድ ጎል ይገባል። ደስታችን ገና በጩኸት ሳይመነዘር በፊት አባታችን ጎል ብሎ ይጀምራል …Esat wey Abeba

“… እንዲያ ነው ጎል! …

 

 

ከዚያማ ጎል አባ ቁርጡ

 

 

ያንን ሁዳድ ሙሉ ጀግና፥ ከገላገለው ከምጡ …

 

ምኑ ቅጡ! ምኑ ቅጡ!”

(እሳት ወይ አበባ – ገጽ ፻፲፩)

 

አባታችን ዘወትር ቅድሜና እሑድ ጠዋት፣ መኝታ ቤታችን ድረስ እየመጣ ከሚያነብልን ግጥሞች መሐል ተቀንጥባ እንደወጣች እናውቃለን። ሁሌም ጎል በገባ ቁጥር ስለሚላት ጭፈራ ወይ ሐዘን ከመጀመራችን በፊት የሱን አፍ እንጠብቅ ነበር።

ተለቅ ስንል ግን እሱን መጠበቅ አቆምን። ታዲያ የሁለት ሳምንቱን ሸመታ ለማካሄድ በሶማሌ ተራ አድርገን፣ የተክለ ሃይማኖትን መንገድ አሳብረን፣ በጠመዝማዛ መንገድ ተጠማዘን፣ ቅቤና ቡላ ከሚቸረቸርበት መደዳ ደርሰን፣ እናቴ ለብቻዋ ከመኪና ስትወርድ እኔ የአባቴን አፍ መከታተል እጀምራለሁ። እንደለመደው ግራና ቀኙን ካየ በኋላ አንድ ቁም ነገር እንዳስታወሰ ሁሉ ወሬ ሊጀምር ሲል እቀድምና፣

Read more  ውሎ ከጋሽ ጸጋዬ ጋር — አንድምታ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *