“ማኅበሩ፣ ሕዝቡን ከፍሎ ይዞብናል” ያሉት ፓትርያርኩ፣ “አቋማችሁን ከእኛ ጋራ አንድ ማድረግ አለባችሁ፤” በማለት እንዲቃወሙት ቅስቀሳ አካሔዱበት፤ ማኅበሩ፥ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብሩ ብቻ፣ በየዓመቱ እልፍ ሐዲሳን ጥሙቃንን እያስመዘግበ ቢኾንም፣ ለምእመኑ ቁጥር መቀነስም ተጠያቂ አደረጉት፤ መለካዊነት የተጠናወታቸው ተሿሚው አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፥ “አቶ ካሳ ይጠራልን፤ መመሪያም ይስጠን፤” እያሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትን ሲወተውቱና በማኅበሩ ላይ ሲያሳድሙ ሰነበቱ፤ […]

via ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ: ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲቃወሙ ቀሰቀሱበት፤ አባ ተ/ሃይማኖት፥ “ካሳ ይጠራልን፤ መመሪያም ይስጠን” ሲሉ ወተወቱ — ሐራ ዘተዋሕዶ

  • “ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳቱን፣ የመረጠቻቸውና የምትሾማቸው ቤተ ክርስቲያን እንጅ መንግሥት አይደለም፤” ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ፣ ጥያቄው ተገቢነት እንደሌለው ገልጾ አባ ተክለ ሃይማኖትን ቢገሥጻቸውም የአድማ ውትወታቸውን ወደ ፓትርያርኩ አዞሩ፤
  • ፓትርያርኩም፣ ትላንት ረቡዕ፣ ሐምሌ 5 ቀን ማምሻውን፣ ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳትን ያለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ ዕውቅና በራሳቸው ወደ ቢሯቸው ጠርተው ሻሂ እና ቡና በመጋበዝ፣ “ማኅበሩን ተቃወሙ፤ ለማኅበሩ እንዳትወግኑ፤ ከእኛ ጋራ ሥሩ” በማለት ከአድማው አበሩ፤ አድማውን አስተባበሩ፤
  • በሚጣረሰው የፓትርያርኩ አነጋገርና በአድማው ያዘኑ ብዙኃኑ ተሿሚዎች ሐሳባቸውን እንዳይሰጡም፥ “መልስ እንዲመለስልኝ አልፈልግም፤ ያለውን ነገር ሒደቱን ማወቅ አለባችሁ፤” በማለት ቅስቀሳው፥ “የሥራ መመሪያ” እንደኾነ አስቀድሞ በማሳወቅ አሸማቀቁ፤
  • የኦርቶዶክሳውያን ካህናትና ምእመናን ኹሉ መንፈሳዊ አባት ሊኾኑ በቃለ መሐላ የተሾሙት ፓትርያርኩ፣ “የሥራ መመሪያ ለመስጠት ነው፤” በሚል በራሳቸው ተሿሚዎችን በመጥራት የፈጸሙት አድመኝነት ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን የጣሰ ነው!
  • የመለካዊውን አባ ተክለ ሃይማኖት ውትወታ ሳያገናዝቡ ያካሔዱት ቅስቀሳ፣ የሕግ ጥሰት ብቻ ሳይኾን፣ “ገና እንዳላወቁንና እንደናቁን ያሳያል፤” ያሉት ብዙኃኑ ተሿሚዎች፣ በየጊዜው፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በመቃወም አድርጎ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚካሔደውን ደባ ለማስቆም ቆርጠዋል! …
  • … ዕጩዎቹ፣ በኤጲስ ቆጶስነት ሢመታቸው ቀን፣ በኦርቶዶክሳውያን ጉባኤ ፊት ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት፣ “የሚድኑ ምእመናንን ቁጥር ለመሰብሰብ፣ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና ግንባታ ነው፤ እግዚአብሔር በንጹሕና በክቡር ደሙ የዋጀውን ሕዝብና መንጋውንም ለመጠበቅ ነው፤ በመልካም ምድር ለማሰማራት ነው፤ ሊጠፉ ቢወዱ እንኳ እንዲጠፉ ላለመተው ነው፤” እንጅ፤ በአንድ በኩል፣ “የምእመኑ ቁጥር ቀነሰ” እያሉ፣ በሌለና ባልተተነተነ ዳታ እያላዘኑ፣ በሌላ በኩል፣ በብዙ ድካም የተሰበሰበውንና ለታላቅ ተልእኮ በሕግ የተደራጀውን አገልጋይና ምእመን ለመበተን አይደለምና!!!

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *