– ከኣስገደ ገብረስላሴ

የዚህ ጽሁፍ  መነሻ ስብሃት  ነጋ በ07 /01 /17 – ዓ  /ም  ከወይን ጋዜጣ ጋር   በትግርኛ ቋንቋ  ያደረገው  ቃለመጠየቅ ነው ። ስብሃት ነጋ    በዚሁ ጋዜጣ    ከ1967 ዓ /ም   እስከ ኣሁን የውሸት ተሃድሶ የሚባለው  ቡዙ የውሼት  ዝርክርክ ያሉ ህዝብን የሚያደናግሩና  የህወሓት የተባላሸ  የጠባብነትና ጸረ ዲሞክራሲ  ቁመናዋ  ለማበጀት (ለማጌጥ )  ሞክሯል ።   ስብሃት ካነሳቸው ነጥቦች  ለሁሉም እንኳ  መልስ ለመስጠት ኣድካሚ  በመሆኑ  በዋና ዋና ነጥቦች በማተኮር  ኣለፍ ኣለፍ ብዬ ለመግለጽ ልሞክር ።
1ኛ ++++  በትጥቅ ትግሉ  በጦርነት ሲገባ እንደሚሰዋ እያወቀ  ደስተኛ  ነበረ  ምክንያቱም  የነበረው የህዝብ ረሃብ እርዛት ስደት  የመልካም ኣስተዳደር  እጦት ለማምጣት ስለነበረ ኣላማው ለማሳካት  ለሚከፍለው ደስተኛ ነበር ይላል  ። ኣዎን ከስብሃት ልዩነት የለንም ።ነገር  ግን ነበርና በህወሓት ኣማራር   ስብሃትም  ጭምር  ክህደት ምክንያት ኣላማቸው ሳይሳካ ቀርቶ  ስደት መብታተን ኣፈናና ኣድልዎ  ያልተመጣጠነ  ንሮ ተባብሷል እነዚያ ጸረ ፋዥዝም የተሰው  ጓዶች  መሰዋእት ከንቱ ኣስቀራችሁት ።  እንዳው ለተሰው ጓዶች በናንተ ኣመለካከት  ንጹህ  ሰማእታትና   ግርድ (ያልጠራ ) በማለት በሰማኣታት ልዩነት ፈጥራችኃል  ።  ስለሆነ  ስብሃት ነጋ  እነዚህ ለሃገር ሉኣላውነት ፣ለኣንድነት ፣ለዲሞክራሲ መልካም  ኣስተዳደር ለማምጣት  የተሰው ጓዶች  ላንተና ለጓዶኞችህ  ምናችሁ ኣይደሉም   ክዳችኃልና  ።

2ኛ****  ሌላ   ወይን  ጋዜጣ  ስለ እድገት ሲጠይቀው  ስብሃት  ሲመልስ ከኣካባቢያችን ካሉት ኣገሮች የተሻለ ለውጥ ኣምጥተናል ይላል። ስብሃት ከኣካባቢ ሃገሮች እኛ እንሸላለን ሲለን ከማን ነው ? ከሱማል ?ከየመን ? ከኤርትራ? ከደቡብ  ሱዳን ? እነሱ እማ መንግስት ኦኮ የላቸውም ። ኢትዮጱያችን ከሀገራችን  ህዝብ  ብዛት   75% የሚይዘው  ወጣት ደግሞ ኣብዛኛው ቀለም የቆጠረ ስራ ኣጥ ነው ። ባገሩ ደግሞ የለም ተሰደዋል  ።  ባህርና  ሰሃራ ቦልቶቷል  ።በሱስ እንዲጠመድ  ኣድርጋችሁታል ። ስለዚህ  ስብሃት እያልከን ያለኸው ቅጀት ነው ።

3ኛ **** ስብሃት   ለነገሩ እንግዳ ሆኖ የሀገራችን ፓርላማ ህገመንግስትን ተከትለው  ለስርኣቱ ይቆጣጠሩታል ወይየሚል  ጥርጣሬ ኣለኝ ይላል። ስብሃት   በፓርላማ ያለው እስከ ቀበሌ ያለው  መዋቅር ፣ በህዝብ ውስጥ ያለው ኣንድ ለኣንድ የስለላ  ኔት ወርክ ነው  ያለው   ኣሁን ኣሁን  ህዝብ እየነቃ ሲሄድ ስለኣሰጋቹ   ነው የምት ዘላበዱ ያላቹ  እንጅ  26 ኣመት   ሙሉ  እኮ  ህዝቡ  ከደርግ ኣገዛዝ  በላይ   ኣፍናችሁታል ።  ታስራል ፣ተገድሏል ፣ሁሉም ኣይነት  መብቶች ኣሳጥታችሁቷል ።

4ኛ  ****ወይን የህወሓት ኣማራር  የትቅ  ትግል ከጀመረ  ከጀመረ በኃላ   በፓርቲው ውስጥ ሽግር ሲፈጠሩ  ሽግሩ እየተከተለው የመጣበት ስልት  ምን  ነበር ???? ሰብሓት  ፡፡፡፡ በ1967 ዓ / ም ክረምት  እንታገል ኣለን ብለው  የመጡ የመንደር የመሳፍንት ዲቃሎች  ነበሩ ። እነዚህ ሽፍቶች ህዝብ ን እየቀሙ ለመብላት  ነበር  ኣላማቸው  ። የነበረ ኣላማቸው በህወሓት  ውስጥ ሆነው ሊያሳኩ ስለማይችሉ ለመለስና ለሙሴ  ትተው ለሌሎች ማእከላይ ኮሚቴና  ከማእከላይ ኮሚቴ  ጋር ግንንኝነት  የነበራቸው  ሊረሽኑዋቸው  ነበር ። ይህ   ደግም ባህረ የሚባል  የነሱ ጓደኛ እና ኃላ ኮነሬል የነበረ ነገሩንውናል    ይህ  መጥፎ እርምጃ   ሊወስዱ  ኣስበው በነበሩ  የተከተልነው የግርጭት ኣፈታት  ዲሞክራሲያዊ ነበር ይላል ።
ስብሃት   የበላበት  ድስት የሚሰብር  ነው እንጂ  ፣ በዛን ጊዜ የነበረ   ቀውስ  ድዛይነሩነሩም ፈጣሪውም እሱ ነበር ። እነዚያ ሰዎች ኣብዛኞቹ  ንጹሃን  ኣርሶ ኣደሮች ነበሩ ። በወቅቱ  ።በሙሉ የኣቶ ገሰሰው ዘመዶችና   የኣካባባው ገሰሰውን በጥሩነቱ የሚያውቀት  ናቸው ።
እነዚህ ወደ ደደቢት የኸድን  11 ሰዎች እና 5 ነፍጥና  ኣንድ ሽጉጥ ስለነበሩ  ፣ለራሳችን ለመከላከል  የማንችል ስለነበርን  ከኣካቢው ህዝብ በብርሃነ ኣየለ  የስሁል  ወንድም ኣማካይነት 26 ሰዎች የራሳቸው ነፍጥ ይዘው  ወደ  ደደቢ  ሊጠቡቁን ሲሄዱ  9ኙ ኣርሶ ኣደሮች ደግሞ  ጠቅልለው ሊታገሉ ፍላጎት  ስለኣሳዩ   ፣ሽኣብያም 10 ኣርሶ  ኣደሮች  እና 10 የተማሩ ሰዎች  ላኩና  ኣሰልጥነን ትጥቅ ኣሳጥቀን   እ ንልክላቹሁ ብለው ስለነበር ።  ደደቢት ከወጣን በኃላ  ኣግኣዚ  ገሰሰ   ቀለበት ታዬ   ስዩም መስፍን  9ኙ ኣርሶ ኣደሮች  ይዞዋቸው  ወደ ሳህል ኤርትራ  ሄዱ ። ሌሎች ሙሁራኖች   9 ሰወች ሄደው ነበር   ።መለስ ሁለተኛ  ሰው  ይዞ  ተሰውሮ ቀረ ። ምክንያቱም ጊዜው ከባድ ጦርነት ስለነበር ።
እነዚህ ኣርሶ  ኣደሮች በኤርትራ የሄደው  የሸኣቢያ  ተንኮል  ተገንዝበው ስለነበር ። ተንኮሉም በህወሓት ሱሁል (ኣቶ ገሰሰ በመኖሩ )  ቂም እንዳላቸው ሰለተገነዘቡ ከባድ ጥርጣረ ነበራቸው።  ከሰወስት ወር በኃላ የማይረቡ ግማሾቹ የተሰበሩ ነፍጥ   ታጠቀው  ወደ ቀላቅል ሕርሚ ወደሚባል በታሕታይ  ቆራሮ ወረዳ   ሽሬ ከተማ ኣካባቢ  በሚገኜው  በረሃ  ደረሱ  ።
በሌላ በኩለ ደደቢት በነበርን ሰዎች ቀውስ ተፈጠረ ፈጣሪውም ስብሃትና  መለስ ነበሩ ። የነበረ ቀውስ 1ኛ  ሰብሃትና መለስ ኤርትራ የሄዱ ስለዘገዩ  ጠላት እንዳያጠቃን ወደ ሸኣብያ ወይ ወደ ጀብሃ እንጠጋ  ኣሉ ።  2ኛ ጥቂት ደግሞ  ወደ ሱዳን ንጠጋና ከዛ እየተወረወርን  እንታገል የሚሉ ነበሩ  ።3ኛ  ሱሑል የያዘው ቡዱን ከኣርሶ ኣደሮች ጭምር  ባለን ትጥቅ ትንሽ  የጠላት  ሃይል እያጠናን  ገንዘብ ከባንክ እና ነፍጥ እንማርክ ኣልን ሃሳባች ኣሸነፈ ።በወቅቱ ሃይለ በርሀ ከአድዋ ፣መምህር  ገብረማርያም  ክሕሸን ከሃውዜን  ወደ ጥገኝነት ኣንሄድ ብለው ለስብሃትና  ለመለስ በመቃወማቸው ጠብ ተፈጥሮ ስብሃት በፈጠረው ግጭት  ተመልሰው ከተማ ገቡ  ። ኃላ ወደ ኣመሪካ ተሰድደዋል ።
ሌላ የስብሃት ቀውሲ  የኣዲያቦና  የኣስገደ ህዝብ የገሰሰው ተጋድሎ እያለ ስለሚጠራን ፣ ስብሃት በዚህ ሆን በኣንድ ፊዳል  ግለሰው ለምን እንጠራ ስለዚህ  ከደደቢት ወጥተን  ወደ ቡዙ ህዝብ ያለበት  ኣድዋና ኣክሱም እንሂድ  ፣በተጨማሪ ከሽሬ ኣካባቢ ታጋዮች ኣንቀበል   ኣለ።
ስብሃት እነዛ ለጊዜው ሊጠቡቁን የመጡ ኣርሶ ኣደሮች ሳይቀሩ ኣወቁት ጠሉትም ።
ከዚያ በኃላ ወደ ሕርሚ ቀላቅል ተጓዝን  ድንገት  ከኤርትራ  ከመጡ ጓዶች  ተገናኜን ። ስብሃት ኤርትራ ለነበሩ ኣርሶ ኣደሮች  እንደ ጠላት ተመለከታቸው ። እነሱም ደደቢት ከነበሩ የኣካባው ኣርሶ  ኣደሮች   ተገናኙ  ። ስብሃት ኣስሙረኛ ነው ለኣርሶ ኣደሮቹ ለመናደድ  በፊታቸው ለገሰሰው  ኣየለ   ያሟውና ያብጠለጥለው  ሲብጠለጥ  ሲሙ ይበሳጩነበሩ ።
5ኛ *** ወታደራዊ ፖለቲካዊ ስልጠናችን ለመከለስ ደደቢት  ተመልሰን ገባን ስልጠናው ቀጠለ ። ስብሓትም  በበጋ የሚያነሳው የነበረ  ቀውሲ (ሕንፍሽፍሽ ) ቀጠለበት  ። እንዳውም   ኣውራጃዊ (ከባቢያዊ ? መልክ  ኣሲያዘው  ። ለዚሁ  ኤርትራ ሄደው የነበሩ  ኣብዛኞቹ  የሽሬ በመሆናቸው  ያለን ነፈጥ የሽሬ ኣውራጃ ብቻ ታጠቁት  ትጥቁ እንከፋፈለው ነው ያለው  ።ኣሳፋሪ  ።ሌላ ቀርቶ የራሳቸው የሆነ   ነፈጥም እንከፋፈለው  ብለው  ነበር።
እንግዲህ በእኔ እምነትም በኣካባቢ መከፋፈል ሳይሆን  እንደየየስራ ምድቡ መታጠቅ  ተገቢ ነው ነገሩ የሰብሃት  የነበረ ፍላጎት ተራ ስለነበር የስልጣን  ስስታምነት ነበረው ።
በእኔ እምነት  እነዛ ኣርሶኣደሮች   የመታገል ፍላጎት  እያላቸው   በስብሃት  መጥፎ ተግባር ኣስበውት የነበረ መጥፎ    ስራ ጥሩ ኣልነበረም ።

Related stories   ሀገሪቷን ከጥፋት ለመከላከል ፣ ህግን ለማስከበር ፌዴራል ፖሊስ ተግባሩን ያጠናክራል

የስብሃት  ሕንፍሽፍሽ  እያደገ ሲሄድ እኛም ደደቢት ለቀን  ወደ ሰየምት  ኣድያቦ  ዊዳኽ ወደ ሚባል በረሃ ገባን ። እዚያ  ቦታ  በወቅቱ የነበረ  ማእኸላይ ኮሚቴ  ስለ የወደፊት ስምሪት  ስብሰባ ኣድርጎ ነበር ። በዛን ጊዜ በማእከላይ  ኮሚቴ ውስጥ  የስብሃት ሃሳብ የሚደግፉ ነበሩ ። ስብሃት የኣቶ  ገሰሰውና  ወንድሙ ብርሃነ ኣየለ ቤተሰቦቻቸው  ከፓርቲው መባረር ኣለባቸው ፣ ኣሁን እየተቀላቀሉን  ያሉ የመሳፍንት ልጆች እነ ሓዮሎም የደጀት ኣርኣያ  ፣ተሰፋይ የደጂት ወልደስላሴ ሌሎችም የሽሬ መሳፍንቶች  ልጆች እንዲያባሩዋቸው  መልእክት  ኣስገባ ።
በዛን ጊዜ እዛው የነበርን የሽሬ ልጆች ከ45  በላይ  ተጋዮች ነበርን  እነሃየሎም  ኣዲስናቸው እኛ  የቆዬን ነባር ታጋዮች  ሰማንና ስለ የስብሃት  ቡዱን ሴራ እንዲያስታገሱ  ለስዩም ለኣግኣዚ ነገርናቸው ሁላችን ከስብሃትና ቡዱኖቹ ተፈጠጥን  ሓየሎም በያዘው ስድስት ጥይት  የሚጎርስ  ኣውቶማቲክ ጠበንጃ ሊያዳፍነው  ኣስቦ  ነበር ሁላችን ተቆጣን ። ኣቶ  ገሰሰው በእግራችን  ወደቆ ለመነን ስዩም ኣግኣዚ ሙሴም በዛን ጊዜ ከእሱር ነጥቀን ኣውጥተነው ሰለነበር ከሱሑልና የሰሁል ወንድም  ብርሃነ ኣየለ  ጋር  ግረጭቱ ለጊዜው  ፈቱት ።
ኣንድ ነገር  ግን  ስብሓት ነጋ  ለምንድነው  ለሽሬ መሳፍንት  ልጆች ከመሬት ገጽ ሊያጠፋቸው የፈለገ ? ኣንድ ሃቀኛ ታሪክ ልንገራችሁ  የሽሬ መሳፍንት  ኣብዛኞቹ ጸረ ቱርክ ፣ጣልያን ፣ ድርቡሽ  ፣  የተዋጉና የሃገራችን  ሉኣለውነት ያሰከበሩ በመሆናቸው ፣ የስብሃት ኣባትና  ኣጎቶቹ እንደነ  ደጃት     ተኩሉ  የጣልያን  ሽነባሾች እና  ፎርማቶሪ  ስለነበሩ ነው ። የሌሎች እንተዎውና  ስለሃዮሎም እና ስሁል  ግን ልጠቁማችሁ  ፣ ቀናዝማች ኣርኣያ  ጸለላና   እና ልጆቻቸው ፊተወራሪ ኪዳነማሪያም ደጃት ኣርኣያ ጸረ ጣልያንና ቱርክ ድርቡሽ ሆነው የኣጼ የውንስና  የራስ ኣሉላ  ጦር ኣበጋዞች  ነበሩ ሆነው  ሃገራዊ ግዳጃቸው  የፈጸሙ በመሆናቸው ነው  ኣቶ ገሰሰም  ኣየለም  በ13  ኣመት እድሜው  ጀምሮ  ለ5 ኣመት  ኣርበኛ  የነበረና  ከኣባቱ ጋር ሆኖ ለጣልያን የተዋጋ ነው   ።

Related stories   “የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች አለመምጣት የሚያጎለው አንዳችም ነገር የለም፤ እኛም አንጠብቃቸውም” ፕሮፌሰር በየነ

ስብሃት ነጋ የሃየሎምና  የገሰሰው ኣየለ የጅግንነት ታሪክ ሲያቋሽሽ ስሰማው  ከወላጆቹ ቂምበቀል ይነሳ ይሆን  እላለሁ ። ስብሃት የአቶ ገሰሰ የትግል  ታሪክ ሲያባላሽ ይታያል ። በተጨማሪም  የሀየሎም ታሪክ ሆንብሎ  ለመበላሸት  ከ5 ኣመት  በፊት   በጉንበት 20 በኣል ዋዜማ  የሃየሎም ጅግንነት  ሲጠዩቁት  ***  ሰብሃት ሲመልስ ሃዮሎም 85 %   የህወሓት ፕሮግራም ኣያውቀውም   ነበር፡ግን  ደግሞ በጦርኖት ተዋግቶ ያሸንፍ ነበር ****** ብሎዋል ምን ማለትነው ሃዮሎም ኣለማ ያልነበረው ገዳይ  ወታደር ነበር  እያለን  ነው ። ሃዮሎም ፓለቲካዊ መሪ መሆኑ  የሚመሰክሩለት  ይቅርና የትግራይ  ህዝብ  የደርግ ሙርኮኞች  እንዲሁም የደርግ መሪዎች ይመሰክሩለታል ።  በመሆኑ የስብሃት ነጋ በን ሃዮሎም እና ገሰሰው    የሰነዘረው የታሪክ የመበላሽት  ዘመቻ   ውሼት ነው ። ኣሳዛኝ ነገር እንዴት የ90 ኣመት ኣዛውንት በመቃብር ጉድጓድ ሆኖ ይወሻል ።

5ኛ **** ግጭቱ ከተፈታ በኃላ  ከሸኣብያ ጋር ተገናኝተው ግንኝነት ሊያድጉ  ስብሃት ለህወሓት ሊቀመንበር   ኣቶ ገሰሰ   ኣየለ  ኣጅቦ  እንዲሁም ጀማይካ ለህወሓት ሊያጠና  ኢሳእያስ  ተልኦኮ የነበረ ጥናቱን ኣጠናቅቆ ኣቡራቸው ሄዱ ።
ኤርትራ  እንደገቡ  ሸኣብያ  ኣቶ ገሰሰ የመልእክተኛ  ቡዱን መርቶ መሄዱ ኣልተቀበሉትም እነዳው ይቅርና   እንደ የኣንድ ፓርቲ መሪ  እንደ ከብት  ጠባቂም ሊመለከቱት ኣልቻሉም ። ስብሃት ያደረገው ግን የሚያደርጋቸው  ግንኝቶች ለገሰሰው እያማከረ ኣይሰራም  ነበር ።   ሁሉም  ነገር  ለገሰሰው  ኣየለ  የተደበቀ  ነበር  በመጨረሻም ገሰሰው  ምንም ግንኝነት ሳያደርግ  5 ነፍጥ ይዘው ተባረሩ  ። ስብሓት ገሰሰው ኣየለ ከፓርቲም ከታራ ታጋይም እንዲበረር መልእክት እንደተሰጠው ሚስጢር  ኣውጥታል ። ኃላም ኣቶ ገሰሰ ከኣማራር መልቀቁ የሸኣብያ ትእዛዝ  ለመተግበር ነው   እንቅስቃሴ  የተደረገ ። ደርሰው ከመጡ በኃላ ጸረሱሑል በዱኖችተሰፋፉ።
የሃዮሎምና የሱሑል  እንዳንዳቸው  ሁለት የትግል ታሪክ  መጻህፍት ተጽፈው በኣዲስ ኣበባ እና በመቀሌ  ተመርቀዋል በዚሁ ምርቃ  ኣሁን ያሉ የህወሓት መሪዎች በምርቃው  ኣልተገኙም ።  በተለይ  የሽንባሹ  ልጅ  ስብሃት ነጋ  የህወሓት ተሪክ ነው እየተባሉ በሚጻፉ በምርቃናቸው  ዋና ሪቧን ቆራጭ ነበር  በገሰሰውና ሓዮሎም የመጻህፍት ምርቃን ግን ብቅ ኣላለም ።
እኒህ ሰዎች እነሱ ኢዲት ያላደረጉት መጽሃፍ ሊሰራጭ ኣይፈልጉትም  ።ለምን ይመስላች ኃል የሃየሎም  ታሪክ ይፋ ከወጣ ሁሉም መሪዎች  ታሪክ  ኣይኖራቸውምና ። ለምሳሌ የሀየሎም የትግል ታሪክ ዳግመ ኣሉላ የሚባለው ኣሁንም  በኣማርኛ በጥለቀት  የሃየሎም ታሪክ የሚተነት ሁለቱ መጻፍቶች  ለንባብ ያበቃ ሰሎሞን ገብረኣረጋዊ  በጠላትነት  ነው  የሚመለከቱት ።

7ኛ   ****ለመሆኑ ስብሃት ነጋ ለሸሬ ህዝብ  እንደባእድ የሚመለከተው ለምንድነው ?? ይህ ህዝብ እኮ  ለህወሓት በወታደራዊ ፣ፖለቲካዊ ፣በኢኮኖሚ ፣  በማህበራዊ  ፣በሀይልሰው ደጀን በመሆን  ለህወሓት ኣቅፎ ኣሳድጎ   ወደ ስልጣን እንዲወጣ ወሳይኝ ሚና የተጫወተ ነው ። ጸረ ደርግ  ጦርነት በሃምሌ 28 /11  / 1967  በሽሬ ተጀምሮ በለካቲት ወር 1981  ዓ / ም 604 ኮርና ተደራቢ  ክፍለ ጦሮችና ብርጌዶች ከ40  000 ሰራዊት በላይ ሰራዊት   ተደምስሶ ከዛ በኃላ በትግራይ ጦርነት ኣልነበረም ። ጦርነቱ ወደ ማኸል ኣገር  ተገፋ   ።በኤርትራና  በመላው ሃገራችን የነበረ  የደርግ  ሃይል ከሽሬ ጦርነት በኃላ የተሸናፊነት  ልቦና ኣድሮበት በሁለት ኣመት በሟይሞላ ኣለቀለት ። የሽሬ የገጠር ወረዳዎች  ህዝብ  በ604 ኮር ማጥቃት ጊዜ ከ250 000 በላይ ህዝብ ምግብ ውሃ  ትጥቅ ፣ቃሬዛ ይዞ  ጾታ ሳይለይ  ከተዋጊ ሰራዊት ጋር   ጎን ተሰልፎ መስዋእት ከፍለዋል ።
የሽረ በረሃዎችና ህዝብ ደርግ ብሀገር ደረጃ  እስከ እሚጠፋ  የስንቅና ትጥቅ ፣ የወታደራዊና ፓለቲካዊ የተክነክ ማሰልጠኛ ነበር ።
ይህ ኣካባቢ ወልቃይት ጨምሮ   የትግራይ  ህዝብ በድርቅ በጦርነት  ተሰዶ የሚደበቅበት በዛው ያለው ህዝብ በየቤቱ ተከፋፍሎ ያሳርፈዋል ይንከባከበዋል  ።
የሽሬ   ወልቃይት በረሃዎችና ገጠር ወረዳዎች እጽዋት ልክ እንደ ሌላላው ፍጡር  ኣልቀዋል በኣሁኑ ጌዜ በአንድ  እስኬር ሜትር ከኣስር በላይ ወፍራምና ቀጭን እጽዋት ተሞልቶ የነበረ  መሬት ጫካነቱ ጭራሹን ጠፍቶ  ምድረበዳ ሆነዋለ  ። ከሽሬ ከተማ ወደ ምእራብ ኣቅጣጫ ተከዜን ተሻግረህ  ከ200  ኪሎሜትር  ርቀት  ስፋት ከዛ  በላይ እስከ ወልቃይ  ለቱሪዙም የሚሆን ዛፍ  ወይ እጽዋት የለም የዱር እንስሳ  ዞሆን  ነብር ኣጋዜን ጎሽ  የሜዳ ፍዬል  ኣሳማ  ከርከሮ   ወ ዘ ተ ከእጽዋቱ ጋር ጠፍተዋል  ። የት ገባ ቢባል ለምሽግ የውግያና የተዋጊ ኣየር መከላከያ ማደሚያ የሰራዊትና የሆስፒታሎች የንብረትና ስንቅ መካዝኖች  መስርያ ። ለምግብ ማብሰያ ። እንዲሁም በተደጋጋሚ ዘመቻዎች በጦርኖት  በተዋጊ ኣዬር  ፣ በመድፍና ናፓልም በምሳይል፣ድብደባዎች በእሳት ሰደድ ተቃጥላል።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

ታድያ እንደዚህ   ኣይነት   የሁሉም ነገር ደጀን ሆኖ ለህወሓት መሪዏች  እሽኮኮ ብሎ ተሸክሞ 4 ኪሎ ያደረሳቸው ህዝብ  በነስብሃት ነጋ የሽንቧሾችና   ፎርሟቶሪዎች ልጆች  በጠላትነት  ይፈረጃል ?
ይህ  ህዝብ  የዩንቨርሲቲ ትምህርት ቤት ተነፍጎታል፣ መቸ ሽረ ብቻ  ወለቃይት ጸገደስ  ?
እንዴት ብሎ የእንድስትሪ ጥሬ እቃ በሽሬ መሬት እያለ ማምረቻ እንድስትሪ  በኣካባቢው ተተክሎ የኣካባው ወጣት የስራ እድል    እንዲፈጠር እደማድረግ ፈንታ   ጥረ እቃው ተጭኖ ከኣድዋ እስከ ኣዲስ ኣበባ ተጉዞ ይፈበረካል ። የስሬ ወጣት ግን በሰሃራ እየታረደ በባህር እየተበላ ፣በሸኣብያ  እየታፈነ ይኖራል ።
ይህ ባለውለታ ህዝብ በ26 ኣመት እንዴት የሚጠጣ ውሃ ያጣል  ?
የሽሬ ትልቁ እንድትሪያችን  ከ5000 በላይ እስሮኞች የሚዝ  ወህን ቤት ተሰርቶልናል ።  ዜጎች የሚሰቃዩበት  ህቡእ እሱር ቤት መኖሩ ነው ። መቸ ይብቻ የሽሬ ህዝብ ካመጸ  ኃላ ልንቆጣጠረው ኣንችል በማለት በኣይነ ቁራኛ  ይታያል ።
እረ ለመሆኑ ይህ ንጹህ ኢትየጱያዊ  የማይምበረከክ የነበረ እንዴት በነ ሉቁባሽና ሽባሽ  በነ ፎርሟተረ  ሽፍታ ይባላል ?  ለዚህ  ህዝብ  ሽፍታ የሚሉት  ያሉ እኮ እነሽባሾች ከመሰል ሽንባሽ ጓዶኞቻቸው  በኣራት ኪሎ ህጋዊ መንግስታዊ ሽፍቶች ናቸው ። ታድያ ለራሳቸው ቀማኛ ወራሪዎች ለሽሬ ህዝብ እንዴት ቀማኛ ይሉታል ።

ሌላ ደግሞ  እነ ሽንቧሾች የሽሬ   ህዝብ  የሚባል ባለ ኣባት  የለም።  በሽሬ  ያለው ህዝብ  መጤ ነው ብለውናል ። መለስ ዘይናዊም የሚሊኔም  በኣል ኣስመልክቶ በሽሬ ከተማ  መግለጫ  ሲሰጥ  የሽሬ ህዝብ  ብሎ ከመናገር ይልቅ  የሽሬ ነዋሪዎች በማለት መግለጫ ሰጥቷል ።
ኣንድ ሀቅ ግን ልንገራችሁ  የሽሬ ልማት ማህበር  በደጉተር ሃብተማርያም  ኣሰፋ  ወደ 100 ኣመት  የተጠጉ  የእድሜ ባለጸጋ    ኣዛውንት ሙሁር ከኣውሮፓ  ቤተ መዘክር ( ኣርካይቭ ) ያገኙት ታሪካዊ ሰነድ እንደሚያረጋግጠው  በሽሬ ኣውራጃ   ከ5000 ኣመት በፊት በኦሪት ዘፍጥረት ማለት ነው ሽሬ  የኣስተዳደር  መዋቅር የነበራቸው  ሰዎች እንደነበሩ  ነው የሚያመለክተው ። ከዚሁ  ተያይዞ  እኒህ ደጉተር የጻፍት  የኢትየጱያ ባህልና  ታሪክ ከሚል  720 ገጽ  የያዘው መጽሃፋቸው  ስለሽሬ ህዝብ የጻፉት ኣለ ። የሆነ የታሪክ ሙሁር ነይ የሚል ካለ ለኒህ   ወደ 100 ኣመት እድሜ ባለጸጋ የሆኑ ፈላስፋ  ሳያለፉ ሄዶ ሊጠይቃቸው ይችላል ።
የትግራይ ወጣት በተለይ ደግሞ የሽሬ ወጣት በነዚህ ሽንባሾችና ሉቁባሾች  ኣትንበርከክ ሰላማዊ ትግልህን ኣቃጣጥል ።  የተከበርከው  የትግራይ ህዝብ  በስብሃት ነጋ የተሰነዘረብሀ ንእቀት ያዘለaei የውርደት ስድብ በህወሓት ልሳን ጋዜጣ  ወይን ተጽፎ ያለ የስም ማጥፋት ዘመቻ  ስለ የ1969 ዓ / ም ቀውስ ፣ ስለ ሰርጌን የትግርኛ  መጽሄት  ያናጣጠረ  ሌሎችም ኣስመልክቸ  ቀስ በቀስ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ ።
ከኣስገደ  ገብረስላሴ ፣ 7 /11  / 2009

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *