ንግስት ይርጋ ” ቤተሰብ አስተዳድራለሁ፣ ደካማ እናት አለችኝ፣ በማዕከላዊ ቆይታዬ የሰባዊ መብቴን በሚጋፋ መልኩ ምርመራ ተካሂዶብኛል” ስትል አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ባለማቅረቡ የሚከሰተውን የፍርድ ማጓተት ፍርድ ቤቱ እንዲያጤነውና አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማሰማት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ እንዲያደርግ ከረር ብላ መናገሯን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቪኦኤ ተናገረዋል።

በአነ ንግስት ይርጋ መዝገብ የተከሰሱት ስድስት ተከሳሾች  በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አመፅ በማስነሳት፣ አመፁን በመምራትና በማስተባበር የሽብርተኝነት ድርጊት ፈፅመዋል በሚል ነው። ለ11 ወራት የዋስ መብት የተከለከለችው ትግስት፣ ከባድ የሰብአዊ ጠሰት እንደተፈጸማባት ቢገለጽም በዝርዝር አልተብራራም።  ይሁን እንጂ ethiopian human rights project በጁላይ 12  ንግስት ደረሰብኝ ያለችውን ይፋ አድርጓል።   ይህንኑ ሪፖርት በመንተራስ ዛጎል  “ሰው ወይም አውሬ፡ እስከ መቼ እንደ አውሬ እያደናችሁን፣ እንደ ሰው እየተሰቃየን እንኖራለን?” በሚል ርዕስ ሙሉ ዘገባ ይህንኑ ምንጭ ጠቀሶ መዘገቡ ይታወሳል። የንግስትን ለመሰማት የሚከበድ ሮሮ አስመልከቶ ከመንግስት ወገንም ሆነ፣ ከፍርድ ቤቱ የተሰጠ መልስ ስለመኖሩ አቶ ሄኖክ ያሉት ነገር የለም። በደፈናው ግን ይህንን መሪር ጉዳይ ማንሳትዋን አረጋግጠው ” ያነሳቸው እገረመንገዷን በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አላነሳውም” ነው ያሉት። ቀጠሮው ግን በበነጋታው እንዲሆን መወሰኑንን አረጋግጠዋል።

Related stories   የባይደን አስተዳደር ፖሊሲ አምስተኛው ምሰሶ የኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን ቡድን መወሰንና የ 2021 ምርጫን ማዋደቅ (1ኛ ክፍል 2)

የ24 ዓመቷ ንግስትን ጨመሮ በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል በተደጋጋሚ ክስና ዘገናኝ ሪፖርቶች፣ ምስክርነቶች፣ እንዲሁም መረጃዎች ቢወጡም ምላሽ የሚሰጥ ወይም የሚያስተባብል ባለድርሻ አካል አለተሰማም። በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ጉዳዩን አምርረው ሲይዙት አይታዩም።

የቪኦኤ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ይህንን ሪፖርት አቅርባለች

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *