ዛጎል ዜና – በኢትዮጵያ ሐይቆች ፈተና ላይ መውደቃቸው ከየአቅጣቻው ሲነገር መስማትና የተለመደ ነው። ድፍን ስምጥ ሸለቆ ውስጥ ያሉት ሐይቆች አደጋ ላይ መሆናቸው ቢሰማም መላ ሲፈለግና ሲታከሙ አይደመጥም። በወጉ ሰለማይጠናና ስለማይመረመር እንጂ መሪዎቿ በኢትዮጵያ የውሃ ሃብት ላይ ያላቸው ዳተኛነት ጉድ የሚያሰኝ ስለመሆኑ ጣና ምስክር ነው።

አንድ የፌስ ቡክ ጸሃፊ “ጣና” አሉ ” ጣና ከብሄር፣ ከጎሳ፣ ከዘርም በላይ ነው፤ ጣና አገር ነው!!” ይህ አስተያየት እንዲሁ በቀላሉ አፍ ላይ እንደመጣ የተነገረ አይመስልም። ለምን ቢባል ” ጣና በወገኖቹ ሞት የተፈረደበት” ስለሚመስል ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ በአጭሩ ጣናን ” ፈረደብህ” አሉት። ባጭሩ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ ” ሳይቸግርህ አማራ ክልል ተፈጠርክ” ነበር ያሉት።

ሁሉንም ጉዳይ ወደ ፖለቲካ መቆልመም አግባብ ባይሆንም አሁን እየዘገዩ የሚወጡት መረጃዎች ግን ጉዳዩን የግድ የፖለቲካው በርጩማ ውስጥ ይከተዋል። አለያም ቀላል የማይባል ጥያቄ ያስነሳል። የአማኤሪካ ሬዲዮ ያናገራቸው የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህርና የጣናን ሃይቅ የወረረውን እንቦጭ አረም አስመልክቶ የምርምር ስራ እየሰሩ ይስሉት ዶክተር ዋሴ አንተነህ እንዳሉት ጣና ያጣው 14 ሚሊዮን ብር ነው። ጣናን ከሞት ለምታደግ  የተጠቀሰው ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ያጠናልን ደግሞ የዓለም የምግብ ድርጅት ፋኦ ነው።

በተመሳሳይ ለቪኦኤ ቃላቸውን ሲሰጡ የተደመጡት አርሶ አደር  ” አረሙ ከብቶቻችንን ጨረሳቸው” ሲሉ የአረሙን ክፋት ይገልጻሉ። አምስት ዓመት ሙሉ አርሶ አደሩ ሃይቁ ውስጥ በመግባት አረሙን ለማምከን ቢዳክርም አልሆነለትም። የአርሶ አደሮቹን መከራና ፈተና መስማት የሚያሳዝን ከመሆኑ ውጪ!! ውሃው ቀዝቃዛ ነው። ውስጡ ትላትሎች፣ የሚናከሱ ወሃ ወለድ አውሪዎችና እባብ ይገኛሉ። ኑሯቸውን በውሃው ላይ የተከሉት አርሶ አደሮች ያለ አንዳች የሰውነት መከላከያ ሃይቁ ውስጥ ገብተው ዳፈቀው ከአረም ጋር ይዋደቃሉ። በቅዝቃዜው እየደነዘዙ፣ እየተመደፉና እየተለከሱ አምስት ዓመት ታገሉ እንቦጭ አረም ግን የሚሸነፍ አልሆነም።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ይህንን ዘመቻ የሚረዳው የክልሉ መንግስት ሲሆን፣ አስተባባሪው እንዳሉት አርሶ አደሮቹ አረሙን እንዲዋጉ መመሪያ ከመሰጠቱ ውጪ ስለ ደህንነታቸው የታሰበ ነገር አልነበረም። የእጅ ጓንት እንኳን አልታደላቸውም። ሁሉም ሆኖ ግን አርሶ አደሮቹ ሁሉንም ችለው ጣናን ለመታደግ ያደረጉት ትግል ከአምስት ዓመት በሁዋላ በሽንፈት ተጠናቀቀ።

ዶክተር ዋሴ እንደሚሉት ይህ አደገኛ አረም የታወቀው የጣናን 4 ሺህ ሄክትር የሰውነት ክፍል ከበላ በሁዋላ ነው። ይህ ሁሉ ጉዳት እስኪደርስ ለምን አልታወቀም? እንዴት ላይታወቅ ቻለ? ታውቆ ነው ዝም የተባለው? ይፋ እንዲሆን አልተፈለገም? የሚሉትን ጥያቄዎች የሚመለሱ መረጃዎች ባይሰጡም ዶክተሩ የችግሩን አደገኛነት ግን ፍንትው አድርገው አሳይተዋል።

አረሙ እንዴት ወደጣና ሃይቅ እንደገባ የታወቀ ነገር ባይኖርም ፋኦ ባካሄደው ጥናት ጣናን ለመታደግ 14 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈለግ ተመልክቷል። ዶክተር ዋሴ እንዳስረዱት በእነሱ ጥረትና ጥያቄ ፋኦ ባጠናው መሰረት ጣናን ለመታደግ ራሱን የቻለ አስተዳደር፣ በጅትና ተጠሪ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነና አሁን ባለው ሁኔታ ዝምታ ከተመረጠ ጣናን የበላው ዓረም ጊዜ ቆጥሮ ጣናን ተረት ያደርገዋል። ይህ ብቻ አይደለም ጣናን የከበቡትና ህይወታቸውን እሱው ላይ የተከሉት ውድ ዜጎችም አብረው ተረት ይሆናሉ። አዲስ አበባን የሚያክለው የውሃ ክፍል በዓረም ሲወረር ሚዲያው፣ ተምረናል የሚለው ክፍል፣ ራሱ ብአዴን፣ ስለህይወት የሚቆረቆሩ ዜጎች የት ነበሩ የሚለው ጉዳይ ግን እስከወዲያኛው የሚዘነጋ አይሆንም።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

በተለይ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች ይህንን ታላቅና አገራዊ ካንሰር ዝም ማለታቸው አግባብ እንዳልሆነ የሚናገሩ ክፍሎች፣ አሁንም ቢሆን የፌደራል መንግስት ዛሬ ነገ ሳይል የተጠየቀውን በጀትና አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሊወተውቱ እንደሚገባ በአካባቢው በሚኖሩ አርሶ አደሮች ስም ይማጸናሉ።

“100 ሺህ አርሶ አደሮች አምስት ዓመት ሙሉ እርቃናቸውን ውሃ ውስጥ እየዳከሩ ከአረም ጋር ሲታገሉ ማሳቸውን የሚሰበስብ አልነበረም” ሲሉ ልብ የሚሰብር የተናገሩት አርሶ አደር ከብቶቻቸው እንዴት እንዳለቁ የገለጹበት መንገድም እርፍት የሚነሳ ነው። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ለጣና 14 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ የሚፈለገውን ለማድረግ ዛሬ ድረስ የሚደነግጡ መሪዎች ስለመኖራቸው አልተሰማም።

ዶክተር ዋሴ የተናገሩት አንድ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ጉዳይ ቢኖር ዓረሙን ለማጨድ የሚያስችል ማሽን በጎንደር ዩኒቨርስቲና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አማካይነት ዲዛይኑ ተጠናቆ ለአስፈላጊው ክፍል መላኩን ነው። ይሁን እንጂ ያ ዲዛይኑ የቀረበለት አካል ማን እንደሆነ አልታወቀም። እሳቸውን ከዛ የዘለለ እውቀት የላቸውም።

በስተመጨረሻ “የፌደራል መንድስት እና ሌሎች አካላት በሙያና በማተሪያል እንዲያግዙን እንተይቃለን” በማለት ነው ዶክተሩ የቋጩት። ይህ ካልሆነ ግን ጣናን እያነከተ ያለው እንቦጭ አባይ ወንዝ ይገባና ከተጠናቀቀ ይህዳሴውን ግድብም ያጠቃል። ለዚህ መዘዙ የበዛ አደገኛ አረም ከወዲሁ የሌሎች አገሮችን ተሞክሮ በመጠቀም መፍትሄ መሻት ግድ ነው። ጣና አገር ነውና፤ ጣና ከፖለቲካም፣ ከጎሳ ጣጣም፣ ከብሄርም በላይ ነውንና!!

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

የጣና ሐይቅ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሐይቆች ሁሉ በትልቅነቱ ቀዳሚውን ሥፍራ ይዟል። አጠቃላይ ስፋቱ 3600 ስኴር ኪሎሜትር ነው ፤ ከሰሜን ወደ ደቡብ አቅጣጫ  84 ኪሎሜትር ርዝመት ሲኖረው፣  ከምስራቅ ወደ ምዕራብ 66 ኪሎ ሜትር ይሰፋል። ጣና በውስጡ እጅግ በርካታ ገዳማትና አድባራት እንዲሁም ታሪካዊ ቦታዎች አቅፎ የያዘ መለያችንም ነው። በከፊል አቶ Zemedkun Bekele የሚባሉ የፌስ ቡክ አምደኛ ከዘረዘሯቸው የተውሰደ

ቢርጊዳ ማርያም ፤ ደብረ ሲና ማርያም  ፣ መንዳባ መድኃኔ ዓለም ፣ ማርያም ግምብ  ፣ ጎርጎራ ግምብ ፣ ጎርጎራ ፣ ገሊላዘካሪያስ ፤ ናርጋ ስላሴ ፣ አርሴማ ሰማዕታት ፣ ዳጋ እስጢፋኖስ ፣ ደቅ ደሴት ፣ ዳጋ ደሴት፣ መትራሃ  ፣ ባርየ ግምብ (ሚካኤል) ፣ አብርሐ አጽብሐ ግምብ ፣ እንፍራዝ ፣ ቆጋ ልደታ ፣ ጋርኖ ወንዝ ድልድይ፣ ጉዛራ ግምብ ፣ ሰንዳባ እየሱስ ፣ ዋሻ እንድሪያስ ፣ ተክለ ሃይማኖት ፣ታራግ ህዳም ማሪያም ፣ ክርስቶስ ሠምራ ፣ ጬቅሊ ደሴት ፣ ጣና ቂርቆስ ፣ ምጽለ ፋሲለደስ ፤ ቆራጣ ጨርቆስ ገዳም፣ ሬማ መድኃኔዓለም ፣ ሬማ ደሴት ፣ መሃል ዘጌ ጊዮርጊስ ፣ አቡነ በትረ ማርያም ፣ ይጋንዳ ተክለሃይማኖት ፣ ክብራን ገብርኤል ፣ ኡራ ኪዳነምህረት ፣ እንጦኖስ ደሴት ፣ደብረ ማርያም ፣ ጣና ቂርቆስ ልሳነ ምድር

የቪኦኤን ዘገብ  0:34:49/1:00:00 ላይ ይአኑና ያንብቡ

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *