የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉን ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉን ገለፀ። በዛሬው እለትም ተጨማሪ ሶስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

ዛሬ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ ይፋ እንዳደረጉት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ነጋዴዎችና ደላሎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ታስረዋል። ማንነታቸው ባይገለጽም የተቋሞቹን ስም ጠቁመዋል። እንደ ዶከተር ነገሪ ሌንጮ ገለጻ ህዝብ ላይ እንደ መሽገር ተጣብቀው ሃላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ ራስን በማበልጸግ ተግባር የተሳተፉትን የማደኑ ስራ የሚቀጥልና ክልል ድረስ የሚዘልቅ ነው። ተጠርጣሪዎቹ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ መሆናቸውም ተመልክቷል። ፋና የሚከተለውን ዘግቧል።

https://youtu.be/sW9S6-H1w8o

 ዶክተር ነገሪ ሌንጮ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 18፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት በሙስና የተጠረጠሩ 34 ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ደላሎች እና ነጋዴዎችን ዛሬ በቁጥጥር ስር አውሏል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፥ መንግስት ከሙስና ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ግለሰቦች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ደላሎች እና ነጋዴዎች በአጠቃላይ 34 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉባቸው የመንግስት ተቋማትም የፌደራል እና የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እና ሌሎች ናቸው ተብሏል። ተጠርጣሪዎቹ በቢሊየን የሚቆጠር የመንግስት ብርን ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ መሆናቸውም ነው የተመለከተው።

ሚኒስትሩ መንግስት ለህዝቡ በገባው ቃል መሰረት ከተሰጣቸው ሃላፊነት ውጪ ለልማት መዋል የነበረበትን የህዝብ ሃብት በማጉደል ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ላይ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል።

ከፌደራል አቃቢ ህግ እና ፌደራል ፖሊስ በተውጣጣ ግብረ ሃይል በተደረገው ጥናትና ክትትል መሰረት፥ መረጃ የተገኘባቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋል ተጀምሯል ነው ያሉት።

በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ከዋሉት በተጨማሪም መረጃ የተገኘባቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ባለሃብቶችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ይቀጥላል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ሰፊ ጥናት እና ዝግጅት ሲደረግበት ቆይቶ የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

መንግስት እስካሁን ለህብረተሰቡ ቃል ሲገባ የነበረውና በተደጋጋሚ ሲገለፅ የነበረው የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት እርምጃ በከፍተኛ ደረጃ መጀመሩን የሚያመላክት ነው የተባለው ይህ ኦፕሬሽን በቀጣይ ቀናትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

መንግስት በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን እንደቀጠለ የጠቆሙት ሀላፊ ሚኒስትሩ፥ ይህ ኦፕሬሽን በክልሎችም እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር የዋሉት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ደላሎች እና ነጋዴዎች ማንነት፣ ተሳተፉበት የተባለው የወንጀል መጠን እና የወንጀል አይነትን መንግስት በቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግም በመግለጫው ተጠቅሷል።

–    የቀድሞው የተንዳሆ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የፋይናንስ ዳሬክተር ይገኙበታል

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 34 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባለሀብቶችና ደላሎች፤ በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢፌዴሪ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ::

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ 34 የሚሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ባለሀብቶችና ደላሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ኃላፊዎቹ ተጠርጥረው የተያዙት “በፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግና በፌደራልና አዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መ/ቤቶች በተደረገ የማጣራት ስራ የሙስና ተግባር ውስጥ ተሳትፈው በመገኘታቸው መንግስት ሙስናን ለመከላከል በያዘው ቁርጠኛ አቋም ነው፤” ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል::

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ  ኃላፊዎች ከተገኙባቸው የመንግስት  ተቋማት መካከል፤ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፣ ስኳር ኮርፖሬሽን እና የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ጋር ይገኙበታል፡፡

የሰንደቅ ምንጮች እንደገለጽት፣ በስኳር ኮርፖሬሽ በኩል ተጠርጥረው ከተያዙ መካከል  የቀድሞው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አበበ ተስፋዬ እና የቀድሞው የተንዳሆ የፋይናንስ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ድምፁ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ እንዲሁም፣ አቶ በኃይሉ ገበየሁ የኮርፖሬሽኑ ንብረት አስተዳደር ዳሬክተር እና አቶ ኤፍሬም አለማየሁ የቀድሞ የኮርፖሬሽኑ፣ ግዢና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዳሬክተር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ግዢ ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው ግርማ፤ እንዲሁም ወ/ሮ ሠናይት ወርቁ እና አቶ ኃየሎም ከበደ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ታውቋል፡፡

አንድ የቀድሞ ሚኒስትር እና አንድ ሚኒስትር ዴኤታም ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምንጮቻች የጠቆሙን ቢሆንም፣ ከሚመለከታቸው አካላት ለማረጋገጥ አልቻልንም፡፡

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *