የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ የሺ ዋስ አሰፋ የጸጥታ ሃይል መሆናቸውን በተናገሩ፣ ነገር ግን ማንነታቸውን ለመግለጽ ፈቃደኛ ባለሆኑ ሰኦውች ተይዘው ማሰፈራሪያ ተሰጥቷቸው መለቀቃቸን እንዲሁም “አስፈላጊ ከሆነ ትገደላለህ” መባላቸውን አስታውቀዋል። በትናትናው እለት ባህር ዳር የፓርቲው አባላቶጭ የፍርድ ሂደት ላይ ለመገኘትና ጠበቃ የሚያገኙበትን አግባብ ለማፈላለገ ወደ ባህር ዳር ካመሩ በሁዋላ የፍርድ ሂደቱን እንዳይከታተሉ ቢደረገም በዳኞች ትዕዛዝ ችሎት ተግኝተዋል። ይሁንና ከችሎት ፍጻሜ በሁዋላ አቶ የሺዋስ መያዛቸው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለቪኦኤ አስታውቀው ነበር።
አቶ የሺህ ዋስ በፌስቡክ ገጻቸው ” ከጥቂት ጊዜ እገታና ማስፈራሪያ በኃላ ነፃ ሆኘ ተመልሻልሁ ” የሚል አጭር መልዕክት አስተላለፈዋል። ይህ ከመጻፉ ሰባት ሰዓት በፊት ነጻ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የአማራ ክልልን ክፉኛ ወቅሰው ነበር። በክልሉ የፓርቲያቸው መዋቅር መፍረሱንና ህገ መንግስት መጣሱን አመልከተው ነበር። ስምና ቦታ በመጥቀስ የሰማያዊ ፓርቲ ላይ የደረሰውን በደል ለቪኦኤ ያስረዱት አቶ የሺዋስ ይህንን ባሉ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው ጭ ለባሾች ይዘዋቸዋል የተባለው።
ሃሙስ ለቪኦኤ በሰጥት መግለጫ የያዙዋቸው ሰዎች ” አርፈህ ብትቀመጥ ይሻላል። አስፈላጊ ከሆነ እንገልሃለን ብለውኛል ” ያሉት አቶ የሺዋስ የአማራ ክልል ዓቃቤ ሕግ ዘጠኝ በሚሆኑ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላትና ሌሎች አባላት ላይ የተመሰረተውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ዛሬ የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደሰጠም አስታውቀዋል።