መንግስት በይፋ ጀምርኩ ባለው ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በቁጥትር ስር በማዋሉ ሂደት በድህንነትና በአቃቤ ህግ መካከል እምብዛም ስምምነት አለመኖሩን፣ በቦሌ ለብርበራ በመጡ የልዩ አቃቤ ህግ ሕግ ሰዎችና በድህንነት ባልደረቦች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበርና የተሽከርካሪ መተላለፊያ መንገድ ለአርባ አምስት ደቂቃዎች ያህል ዘግ እንደነበር  የአካባቢው ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዋዜማ ሬዲዮ ዘገበ። በአካባቢው እስከ አትላስ በሚዘልቀው መንገድ ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ከ12 የማያንሱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግሥት ሹመኞች መኖርያ ቤት ይገኛል፡
ትናንት አርብ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቀናት ልዩነት አዲስ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን ጠርተው የነበሩት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩጋዜጠኞች ቦታው ከደረሱ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት መግለጫውንመሰረዛቸው መግለጫውን ለመከታተል የተገኙ ጋዜጠኞች ተበትነዋል። በመጨረሻም የልዩ አቃቤ ህግ ሚኒስትር ጌታቸው አምባዬና ባልደረባቸው ቀዳሜ /ዛሬ ሰፋ ያለ መግለጫ እንደሚሰጡ ለጋዜጠኞች ተነግሯቸዋል። የዋዜማ ዜና እንደሚከተለው ይነበባል

ትናንት ማምሻውን ቦሌ የባለሥልጣናት መንደር ግርግር ተፈጥሯል
ደኅንነት መሥሪያ ቤት ባልደረቦች መሐል አለመግባባት እንዳለ እየተነገረ ነው፡፡
ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ትናንት ሊሰጠው የነበረውን መግለጫ ተሰርዟል
ዛሬ ረፋድ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጌታቸው አምባዬ ከጋዜጠኞች ጋር ይገናኛሉ

በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው የሚታሰሩ የመንግሥት ኃላፊዎች ቁጥር ወደ 40 ማሻቀቡን ተከትሎ ትናንት ማምሻውን ቦሌ ኖቪስ ራማዳሆቴል ጀርባበልዩ ኃይሎች ተከቦ ነበር፡፡ ዋዜማ የሰፈሩን የአይን እማኞች በመንተራስ ባገኘው መረጃ ብርበራ ለማካሄድ በመጡ የልዩ አቃቤ ህግ ባልደረቦችና በደህንነት መስሪያ ቤት ባልደረቦች መሐል መነሻው ያልታወቀ አለመግባባት ተፈጥሮ ቆይቷል። ፍጥጫው በግምት ለ45 ደቂቃዎች ከቆየ በሁዋላ መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ክፍት ተደርጓል። ሆኖም ዋዜማ የየትኛው ባለስልጣን መኖሪያ ቤት ሲበረበር ይህ ችግር ሊፈጠር እንደቻለ መረጃ ማግነት አልቻለችም።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

በአካባቢው እስከ አትላስ በሚዘልቀው መንገድ ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ጨምሮ ከ12 የማያንሱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግሥት ሹመኞች መኖርያ ቤት ይገኛል፡፡

ለደኅንነት መሥሪያ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት ‹‹ቅድሚያ ማን ይታሰር፣ ማን ይቆይ›› በሚለው ጉዳይ ደኅንነት መሥሪያ ቤቱ ዉስጥ ባሉ ኃላፊዎች ወጥ አቋም አይታይም። በአቃቤ ህግና በደህንነቱ ሃይሎች መካከል የዕዝ ሰንሰለቱ ላይ መግባባት እምብዛም አይታይም።

ይህ በእንዲህ ሳለ ትናንት አርብ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቀናት ልዩነት አዲስ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን ጠርተው የነበሩት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩጋዜጠኞች ቦታው ከደረሱ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት መግለጫውን ሰርዘውታል፡፡ ጋዜጠኞች ከተበተኑ በኋላም የልዩ አቃቤ ሕግ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዬና ባልደረቦቻቸው በተጠርጣሪዎች ጉዳይ ሰፋ ያለ መግለጫ እንደሚሰጡ ተነግሮ ጋዜጠኞች ለዛሬ ቅዳሜ አራት ሰዓት ተመልሰው እንዲመጡ ተነግሯቸዋል፡፡

ዋዜማ ባገኘቸው ሌላ ተጨማሪ መረጃ በሳምንታት ዉስጥ ከ50 የማያንሱ የነጋዴው ማኅበረሰብ አባላት የእስር ዘመቻውን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በፋይናንስደህንነት መሥሪያ ቤት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በዋናው ኦዲተር እንዲሁም ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ባልደረቦች የተውጣጣ ኮሚቴ ከ120 በላይ ነጋዴዎችን በተጠርጣሪነትበጥቁር መዝገቡ አስፍሯል፡፡ ለወራት ያህልም የሂሳብ ባለሞያዎቻቸውን በመጥራት፣ ስልካቸውን በመጥለፍ፣ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ መረጃ ሲያሰባስብ እንደነበርተነግሯል፡፡ ከነዚህ መሐል በመጀመርያ ዙር የእስር ማዘዣ ይወጣባቸዋል ተብለው የሚገመቱት 18 የሚሆኑ ከፍተኛ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ የብዙዎቹ ክስ ከታክስ ስወራጋር የሚያያዝ ነው፡፡

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *