[ 3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤቱ ጥሪ ቢያቀርብለትም፣ ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ተከሳሽ መቅረብ ባለመቻሉ ክስ እንዲቋረጥ በማለት ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል ]

በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የፌደራል ዐቃቤ ህግ የሽብር ክስ መስርቶባቸው አንድ አመት ከስምንት ወር በማዕከላዊ እና በቃሊቲ እንዲሁም በቂሊንጦ እስር ቤት አስቸጋሪውንና ፈታኙን የእስር ጊዜ ያሳለፉት አስሩ (10) ተከሳሾች፤ ከተከሰሱበት ክስ ነፃ መባላቸው የሚታወስ ነው። ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በነፃ ካሰናበታቸው መካከል የቀደሞ አንድነት ፓርቲ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ ነፃ ወጥቶበት በነበረው የሽብርተኝነት ክስ አቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቆባቸው እንደነበረ የሚታወቅ ነው።

ይግባኙን ሲመረምረው የነበረው ፍርድ ቤቱ ፤አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ ከኢሳት ጋዜጠኛ ከአቶ ፋሲል የኔአለም ጋር ያደረጉት የስልክ ልውውጥ ሲታይ የሽብር ተግባር ሊፈፅሙ ባያቅዱም፤ በሽብርተኛ ድርጅት ከተፈረጀው ግንቦት 7 ጋር ሁለገብ ትግል በሚለው ሃሳብ የመስማማት አዝማሚያ እንዳላቸው እና ከሰላማዊ ትግል ባለፈ የመንቀሳቀስ ፍላጎት
እንዳላቸው የሚያሳይ ነው በማለት የልደታ ምድብ ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሾች ላይ የቀረበውን የይግባኝ ክስ እንዲከላከሉ ብይን አስተላልፎ ነበር።

ተከሳሽ አቶ ዳንኤል ሺበሺ በይግባኝ የቀረበበትን ክስ ፤ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ ግርማ ሰይፉን የመከላከያ ምስክር በማድረግ ፣በእስር ቤት ሆኖ. የቀረበበትን ክስ ሲከላከል ቆይቶ ነበር ።የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የአቶ ዳንኤል ሺበሺ የመከላከያ ምስክሮች ቃል እንዲሁም ተከሳሽ የሰጠው የራስ የምስክርነት ቃል ፣ በተጨማሪ ተከሳሽ ለፍርድ ቤቱ ያስገቡት የክርክር ማቆሚያ ፤ ስመረምር ቆይቻለው ያለው ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዛሬው እለት ፍርድ ሰጥቷል ።

ፍርፍ ቤቱ በሰጠው ፍርድ፤” አቶ ዳንኤል ሺበሺ የቀረበባቸውን ክስ በአግባቡ የተከላከለ ስለሆነ በነፃ ተሰናብተዋል “በማለት የፍርፍ ብይን ሰጥቷል።በዚሁ መዘግብ ተከሳሽ የሆነው 3ኛ ተከሳሽ አቶ አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤቱ ጥሪ ቢያቀርብለትም፣በተጨማሪ ታስሮ እንዲቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ተከሳሽ መቅረብ ባለመቻሉ በአቶ አብርሃ ደስታ ላይ የተመሰረተው ክስ እንዲቋረጥ በማለት ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን ፣ከሳሽ በተከሳሽ ላይ ይግባኝ ማለት እና ክሱን በድጋሚ ማንቀሳቀስ ይችላል በማለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል ።

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባል አቶ ዳንኤል ሺበሺ በሽብር ክሱ ነፃ ቢባልም ከጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ጋር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፋችውላ ተብለው በእስር ቤት የሚገኙ ሲሆን፣በተመሰረተባቸው ክስ ለ9 ወር ያህል በእስር ቤት ከቆዩ
በኋል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት በ50 ሺህ ብር ዋስ ተፈተው ጉዳያቸውን ከእስር ቤት ውጪ እንዲከታተሉ ብይን የሰጠ ሲሆን፣አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ከአገር እንዳይወጡ ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ትእዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።

በዚሁ ችሎት በልደታ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ወንጀል ችሎት ፣በይደር ያደረው የወ/ሪት ንግስት ይርጋ አቤቱታ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የወ/ሪት ንግስት ይርጋ አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ መስጠቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ወሪ/ት ንግስት ይርጋ በቤተሰቦቿ፣በጠበቃ፣በጓደኞች የሰዓት ገደብ ሳይደረግባት ማንኛዉም እስረኛ እንደሚጠየቀው እሷም እንድትጠየቅ በማለት ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል ።
mereja.com
(ይድነቃቸው ከበደ)

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *