በ2009 የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 41 በመቶ የሚሆኑት ከ350 በላይ ውጤት ማስመዘገባቸውን የሀገር ዓቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገለፀ።

ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ፈተናውን ከወሰዱት መካከል 178 ሺህ ያህሉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው፡፡

107 ሺህ ተማሪዎች ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መሆናቸውን ነው ያስታወቀው፡፡ በተፈጥሮ ሳይንስ ፈተናቸውን ከወሰዱት መካከል 49 በመቶ የሚሆኑት ከ350 በላይ ውጤት ያመጡ መሆናቸውን የኤጀንሲው ምክትል ሃላፊ ዶክተር ዘሪሁን ዱሬሳ ገልፀዋል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

በዚህ አመት ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአዲስ አበባ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሲሆን፥ ውጤቱም 633 ነው ብለዋል። ሰሞኑን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ተለቋል በሚል የወጡ የተዛቡ መረጃዎች ሀሰት መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ተማሪዎች ትክክለኛውን ውጤት ነገ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በኤጀንሲው ድረ ገፅ www.neaea.gov.et ላይ በመከታተል ማግኘት እንደሚቻልም ነው ዶክተር ዘሪሁን የተናገሩት።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በነጻ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ቁጥር 8181 ላይ የተፈታኞች መለያ ቁጥርን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ አብራርተዋል።

በቅርቡም ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ መቁረጫ ውጤት ይፋ የሚደረግ ሲሆን፥ የ10ኛ ክፍል ውጤት ደግሞ ነሀሴ 25 2009 እንደሚለቀቅ ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል።

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *