ፍርድ ቤት የአቶ አየልን አሟሟት በተመልከት ከሆስፒታል  ማስረጃ እንዲያቀርብ አዘዘ፤ ማረሚያ ቤቱ የተየቀውን ደብዳቤም ከልክሏል። በቁጥጥሩ ስር ያሉትን ታራሚዎች ድህንነት የመጠበቅ ግዳጅ ያለበት በመሆኑ ተግባሩን ራሱ እንዲወጣ ተነገሮታል

“የልጅነት ባሌን ነው ያጣሁት፣ የልጄን አባት ነው ያጣሁት ” ሲሉ ወ/ሮ ሰላም ውድነህ  የሃዘናቸውን ከባድነት ይናገራሉ። ፍትህ የጠማቸው ስለመሆናቸው ገለጻቸው ያስረዳል። ይህንኑ ስሜታቸውን ሲገልጹ እንዲህ አሉ። ” ፍትህ የሚያስገኝ ከሆነ” እንደ ሃዘንተኛዋ አባባል ፍትህ በትክክል የማይበየነ ከሆነ አሁን ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ዋጋ የለውም።

በሽርተኛነት ክስ ተመስርቶበት በወህኒ ቤት በቂ ህክምና እንዳያገኝ ተከልክሎ ህይታቸው ያለፈው የአቶ አየለ በየነ ባለቤት ይህንን ያሉት ፍርድ ቤት ” ጥብቅ ትዕዛዝ  ሰጠ ” መባሉን ተከትሎ ነው። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ የወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ቤት ስለሞቱት አቶ አየለ በየነ ሞትና የሞታቸውን ምክንያት ከሚመለከተው ሆስፒታል ማስረጃ አንዲያቀርብ፣ ለአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ጥብቅ ትዛዝ እንደሰጠ የዘገበው የቪኦኤው መለስካቸው አመሃ ነው።

ተበዳይ እንዳሉት አሁን ፍርድ ቤቱ የሰተው ትዕዛዝ የሚፈልጉት ነበር። ይሁንና ትዕዛዙ እሳቸው እንደሚሉት የሚተገበር ሲሆንና በትክክል ብይን የሚያስገኝ ሲሆን ባቻ ነው። ባለቤታቸውን ያጡት ወይዘሮ ከባለቤታቸው ያገኙትን መረጃ ተንተርሰው እንደተናገሩት ጥርጣሬያቸው ከፍተኛ ነው። ባለቤታቸው በህይወት እያለ አግኝተውት መታማቸውን ነግሯቸዋል። ህክምና ማግኘት በሚገባቸው ወቅት አልታከሙም። ከሁሉም በላይ መናገር አይችሉም ነበር። እንዲያም ሆኖ  የቦክስ ምልክት በማሳየት ምት እንደጎዳቸው ገልጸውላቸዋል።

ጠበቃቸው አቶ ወንደሙ ኢብሳ  የፍርድ ቤቱን ትዕዛዘ  አግባብና መሆን ያልበት ነው ብለዋል። የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የደንበኛቸውን አሟሟት የሚያስረዳ ማስረጃ ሊያቀርብ ግድ ነውና። የመለስካቸው አመሃን ዘገባ ያድምጡ

 

 

Related stories   ኢህአዴግ እንዲህ አለ "በኢትዮጵያ ህዳሴ ጉዞ ሩቅ አዳሪዎች ይሻማሉ፣ የተቸከሉ ያላዝናሉ"

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *