ከትናንት በስቲያ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሶስት ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ። በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ የወንጀል ችሎት በፅህፈት ቤት ጉዳያቸው የታየው ተጠርጣሪዎች ብርጋዴር ጀነራል ኤፍሬም ባንጌ፣ የቀድሞው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ በጋሻው እና የኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እቃ አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ካሳዬ ካቺ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ ከ293 ሚሊየን ብር በላይ መንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረዋል። በተለይም ብርጋዴር ጀነራል ኤፍሬም ከኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ፕሮጀክት በጀት ላይ ተቀናሽ በማድረግና ከሌሎች ያልተያዙ ደላሎች ጋር በመመሳጠር ከ184 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን መርማሪ ፖሊስ ጠቅሷል።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

ፕሮጀክቱም ለሁለት አመታት ከውል ውጭ እንዲጓተት ማድረጋቸውን ነው ፖሊስ የተገለፀው። የቀድሞው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ በጋሻው ደግሞ ሀላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው በትውስት በአርማታ እና የሲሚንቶ አቅርቦት ከተከፋይ ሳይቀነስ ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ባለመቀነሱ ጉዳት ማድረሳቸውን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።

በጨረታ የተሰጠ የአገዳ ምንጠራ ስራን ከባቱ ኮንስትራክሽን በመቀማት ለየማነ ግርማይ በመስጠትና ቀድሞ የነበረውን የአንድ ሄክታር የውል ዋጋ ከ25 ሺህ ወደ 72 ሺህ 150 ብር በማሳደግ ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውም ተጠቅሷል። አቶ ዮሴፍ በተመሳሳይ የአገዳ ምንጠራ ስራም 10 ሚሊየን ብር ክፍያ በመፈፀማቸው በአጠቃላይ ከ82 ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

ሶስተኛው ተጠርጣሪ የኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እቃ አቅርቦት ቡድን መሪ አቶ ካሳዬ ካቺ፥ ከአራት አመት በፊት ለሁለት የግንባታ ተቋራጭ ድርጅቶች ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ሰጥተው ገንዘቡ ባለመመለሱ በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ተጠርጥረዋል። ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል። ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው የፖሊስን የጊዜ ቀጠሮ በመቃወም ዋስትና እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

የመርማሪ ፖሊስ እና የተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ያዳመጠው ፍርድ ቤትም የብርጋዴር ጀነራል ኤፍሬም ባንጌ እና ዮሴፍ በጋሻው የክስ መዝገብ ከሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር ተዳምሮ ለነሃሴ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል። ፍርድ ቤቱ ለካሳዬ ካቺ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ለምርመራ በመስጠት ፖሊስ ቀረኝ ያለውን ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 27፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *