በአምቦና ወሊሶ ለአምስት ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ መጀመሩን የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ አስታወቀ። እንደ ዜናው ከሆነ አድማው የተጠራው ታዋቂው ፖለቲከኛና ምሁር ዶክተር መረራና በቀለ ገርባን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱ በሚልና አዲሱን የገቢ ግብር በመቃወም ነው። ዜናውን አስመልክቶ ከመንግስት ወገን እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

Image result for ambo protest

ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶችን ጠቅሶ አድማው ወጀመሩን ያወሳው ዜና በአምቦ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮጵያ ሆቴል በስተቀር አድማው ሙሉ በሙሉ ተገባራዊ ሆኗል። አድማው ለአምስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን፣ ወደ ሌሎች ከተሞችም እንደሚዛመት ቄሮዎች ተናግረዋል። የኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክ በሰበር ዜና የፎቶ ምስሎችን አስደገፎ እንደዘገበው የአምቦ ከተማ ጭር ብላ ታይታለች።

በፖለቲካ እምነታቸው አክራሪ እንዳልሆኑና የዘር ችግር እንደሌለባቸው አገር የሚመሰክርላቸው ዶክተር መረራ ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚያሳየው ምስል ብዙዎችን አነጋግሯል። በእጅ ብረት ወደሁዋላ ታስረውና ከፊትና ከሁዋላ መሳሪያ ተደግኖባቸው የታዩት ዶክተር መረራ የብዙዎችን ስሜት ነክተዋል። በምስል የታዩበት አግባብ ሰብአዊነት የጎደለውና ተከታዮቻቸውን፣ ደጋፊዎቻቸውን፣ እንዲሁም ነጻ ዜጎችን በጥቅሉ ያበሳጨም እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች በስፋት ተዘግቧል። ከሁሉም በላይ ለህግ ትርጉም በሚል ለሚቀጥለው ዓመት መቀጠራቸው ስጋት አስፍኗል።

ይህንኑ በማጉላት ዜናው እነ ዶከተር መረራ ባስችኳይ እንዲፈቱ የሚጠይቅ እንደሆነ የተነገረለት አድማ በመላው ኦሮሚያ ከተስፋፋ ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅሰቃሴ መናወጥ ሊፈጠር ይችላል። ይህ ከመሆኑ ስድስት ወር በፊት አቶ ጁሃር መሐመድ፣ “በቀጥዩ ዓመት አዲስ የትግል ስትራቴጂ ይቀየሳል” ሲሉ ኢህአዴግ ላይ የኢኮኖሚ ጫና የመፈጠር እቅድ እንዳለ መናገራቸው አይዘነጋም። የዚሁ እሳቸው ያሉት አዲስ ስትራቴጂ አካል ይሁን አይሁን በይፋ ባይነገርም አዲሱን የንግድ ገቢ ተመን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ በፖለቲካ ጥያቄዎች መታጀቡን ዜናው ይፋ አድርጓል።

ዶክተር መረራ በዋስ እንዲፈቱ፣ ጉዳያቸው ባስቸኳይ ሊታይ እንደሚገባው የቀረበው ጥያቄ አቃቤ ህግ ተቃውሞ በማሰማቱና ፍርድ ቤት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የህገመንግስት ማብራሪያ ያስፈለገዋል በሚል ለቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ነው። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያስረዱት በኦሮሚያ አዲሱ የትምህርት ዘመን ሲጀመር በእስር ላይ የሚገኙ የክልሉ ነዋሪዎች ይፈቱ በሚል ጥያቄ እንደሚነሳ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን የማካሄድና ጥያቄው ተቀባይነት ካላገኘ የተለያዩ የተቃውሞ ስልቶች ተጋባራዊ የማድረግ እቅድ ተይዙእል። ኢህአዴግ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የጸጥታ ሃይሎችን በመመልመልና በማስልጠን የአስቸኳይ አዋጁን ማንሳቱን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

አስተያየት የሰጡ ወገኖች እንደሚሉት አዲስ የተመለመሉት የጸጥታ ሃይሎች የየክልሉ ተወላጆች በመሆናቸው ቀደም ሲል መዘገባቸን ይታወሳል። አሁን ተደረገ የተባለውን የስራ ማቆም አስመልክቶ ከመንግስት ወገን ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ የተባለ ነገር የለም። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክም አድማው እንደተባለው ለተከታታይ አምስት ቀን መጠራቱን ከመዘገቡ ውጪ ተጨማሪ መረጃዎችን አላስከተለም። አምቦ በተደጋጋሚ ተቃውሞ የሚነሳባት ከተማ እንደሆነች ይታወቃል።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *