የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲነሳ እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል 164,475 ፣ በአማራ ክልል ብቻ  143,459 አዳዲስ የጸጥታ ሃይላት ተመልምለው ወደ ስራ መግባታቸውን አመልክተው ነበር። እነዚህ የጸጥታ ሃይሎች ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በጥምረት እንደሚሰሩና የየክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚችሉ አረጋግጠው ነበር። ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ ምልምል ከመከላከያ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከክልል ፖሊስና ከልዩ ሃይል ጋር ሲዳመር የአገሪቱን የጸጥታ ሃይል ቁጥር በጅጉ ያሻቅበዋል። ይህ ሁሉ ሃይል ተደራጅቶም በተለይዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙ መሆኑ ሁሉንም የሚያስማማ ፖለቲካዊ ምፍትሄ ከመፈለግ ውጪ አማራጭ እንደሌለ አመላካች እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

ኦሮሚያና አማራ ክልል በስፋት፣ በደቡብ ክልል በከፊል የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመጽ ኢህአዴግ የተንገዳገደበት ነበር። ሕዝባዊ ተቃውሞው በወጉ የሚሰበስበውና የሚመራው ቢያገኝ ኢህአዴግን አስገድዶ ወደ ድርድር በማምጣት በአገሪቱ ፖለቲካዊ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል አጋጣሚም የመፍጠር አቅም የነበረው እንደነበርም የተለያዩ ሚዲያዎች ዘገበዋል። ኢህአዴግ በበኩል ራሱን ህዝብ በፊት በመስደብና ” ጥፋቱ የኔ ነው” በሚል ንስሃ እየገባ፣ ያወጀውን የማስተር ፕላን አዋጅ በማንሳት አየር ሳበ። ከዛም የሚችለውን ያህል ሃይል ተጠቅሞ አመጹን ጋብ አደረግ። በአናቱ ላይ አስችኳይ አዋጅ አውጆ አፈሳ አካሄደ።

በአገሪቱ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ አዳዲስ የቆዩና የታፈኑ ጥያቄዎችን እያስተጋባ መጨረጻው ” ኢህአዴግ ወግድ ” የሚል ሆነ። መቶ ከመቶ ተመረጥኩኝ ያለው ኢህአዴግ፤ ይህንን ባለ የወራት እድሜ ውስጥ አደገኛ የለውጥ ወረርሽኝ ገባበት። አቻ የሚባሉት ፓርቲዎቹ በተለይም ኦህዴድና ብአዴን የመክዳት ያህል የተነሳውን ተቃውሞ ለመታገል ተሳናቸው። እንደውም ” ራሳቸው አሉበት” የሚል ድምዳሜ ላይ ተደረሰ።

Related stories   Let’s See the Proof of “Ethnic Cleansing” in Ethiopia, New York Times!

አቶ መለስ በአንድ ወቅት  እንዳሉት  ኢህአዴግ ውስጡ ገምቶ ነበር። ኢህአዴግ በስም እንጂ እንደ ድርጅት የለም ነበር። አባላቱ፣ ሚሊሺያዎቹና በፖሊስ ደረጃ ያደራጃቸው ሁሉ እንደሚፈልገው አልሆን አሉት። ቃል በቃል ” ተከዳሁ፣ ተሞኘሁ” ባይልም በሺ የሚቆጠሩ አባላቱን አገደ፣ አባረረ፣ አስቸኳይ ጊዜ አወጀ። ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ ቁጥጥሩን ወደሚያምነው አካል ሙሉ በሙሉ በአዋጅ አዞረ።

በዚህ መልኩ የተወሰደው ርምጃ ሁሉ ተወስዶ ኢህአዴግ ከገባበት ተስቦ አገገመ። እሱ እንዳለው ከማገገምም አልፎ ” ዳነ” ከዛም አስቸኳይ አዋጁን ማንሳቱን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አበሰረ። ተነስተው የነበሩት የሕዝብ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ስለማግኘታቸው የሚጠቀስ ማስረጃ ባይኖርም፣ አምጹን ለማርገብ የተወሰዱት እርምጃዎች አሻራዎቻቸው ግን ገና ትኩስ በመሆኑ በዚህም በዚያም እያዳመነ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ነሃሴ 1 ቀን 2008 ዓ ም በባህር ዳር የተገደሉ ዜጎች የሃዘን አሻራ አንዱና ጠባሳው አለመሻሩ፣ በቀላሉም ሊሽር የማይችል እንደሆነ የተጠቀሰው ትናት ነው። አስተባባሪዎች ቢሚስጢር የመሩት የአድማ ጥሪም የተደረገው በዚሁ ሳቢያ እንደሆነ ተዘግቧል። የአማራ ክልል ፖሊስም ይህንኑ አምኗል።

Related stories   በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

በመላው አገሪቱ ከዚሁ አመጽ ጋር በተያያዘ የፈሰሰው ደም ሃዘኑና ቁስሉ እንዳለ ነው። የዚህ አመላካች የሆነው የባህር ዳሩን  አድማ አስመልክቶ ቪኦኤ ያነጋገራቸው እንዳሉት ከማለዳ አንስቶ እስከ ቀኑ ስምንትና ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ባህር ዳር በሯን ዘግታ ሃዘን ተቀምጣ ነበር። እንደ ምስክሩ ገለጻ አድማ የተሳካ ነበር። በተጠቀሰው ሰዓት አንዳንድ ባጃጆች ውር ውር ሲሉ ከመታየያቸውና አንዳንድ ሱቆች ከመከፈታቸው በቀር ባህር ዳር ሃዘን ላይ ነበረች።

የጸጥታ አድማ፣ የቤት መቀመጥ አድማ ለመቆጣጠርና ርምጃ ለመውሰድ አዳጋች ስለሆነ አድማው እንደሚመታ አስቀድሞ ያወቀው አስተዳደሩም ሆነ የጸጥታ ክፍሉ ምንም ሊያደርግ አልቻለም። እንደ ምስክሩ ገለጻ ቢሞከርም አልተሳካም። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የአንድ ክልል ዋና ከተማ ስትፈልግ የምታድም፣ ስትፈልግ አድማዋን የምትተው መሆኗ ነው። አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ብአዴንና ህዝብ በገሃድ መፋታታቸውን አመላካች የሆነው ይህ ቤት ውስጥ ጸጥ ብሎ የመቀመጥ አድማ ከማንም በላይ ለብአዴን ካድሬዎች ህመም ነው። ለፌደራል መንግስትም በሽታ ነው። ይህ አድማ የሚቆም አይመስልም።

የክልሉ ፖሊስ እንዳለው በባህር ዳር ቦንብ ተጥሏል። የተጣሉት ቦንቦች ስላደረሱት ጉዳት የተገለጸ ነገር ባይኖርም የክልሉ ፖሊስ አምስት ተጠርታሪዎችን መያዙን አመልክቷል። ፋናም የአማራ መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ አድርጎ ዜናውን ይፋ አድርጓል። የአስቸኳይ አዋጁ በተነሳና ለዲፐሎማቶች ማብራሪያ እየተሰጠ ባለበት ወቅት ነው ፍንዳታው የደረሰው።

Related stories   ም.ጠ.ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከካናዳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያዩ

 

በባህር ዳር በታጣቂዎች ህይወታቸው ያለፉትን ከሃምሳ በላይ ዜጎች ለማስታወስ በተጠራው የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ቀስቃሽ የተባሉ አራት ሰዎች መታሰራቸውን ፖሊስ ይፋ ቢያደርግም በጅምላ የታፈሱ ብዙ መሆናቸውን የሚናገሩ አሉ።

ባለፈው ሳምንት የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈርጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲነሳ እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል 164,475 ፣ በአማራ ክልል ብቻ  143,459 አዳዲስ የጸጥታ ሃይላት ተመልምለው ወደ ስራ መግባታቸውን አመልክተው ነበር። እነዚህ የጸጥታ ሃይሎች ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በጥምረት እንደሚሰሩና የየክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚችሉ አረጋግጠው ነበር። ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ ምልምል ከመከላከያ፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከክልል ፖሊስና ከልዩ ሃይል ጋር ሲዳመር የአገሪቱን የጸጥታ ሃይል ቁጥር በጅጉ ያሻቅበዋል። ይህ ሁሉ ሃይል ተደራጅቶም በተለይዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙ መሆኑ ሁሉንም የሚያስማማ ፖለቲካዊ ምፍትሄ ከመፈለግ ውጪ አማራጭ እንደሌለ አመላካች እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *