​ የአለም ሪከርድ በሆነ ዋጋ ታላቁን ባርሴሎና ለቆ ወደፈረንሳዩ ክለብ ፔዤ የተዘዋወረው ነይማር ጁኒየር የቀድሞ ክለቡን በፊፋ ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተዘገበ፡፡

via ኔይማር የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎናን ሊከስ ነው — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የአለም ሪከርድ በሆነ ዋጋ ታላቁን ባርሴሎና ለቆ ወደፈረንሳዩ ክለብ ፔዤ የተዘዋወረው ነይማር ጁኒየር የቀድሞ ክለቡን በፊፋ ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተዘገበ፡፡

እንደግሎቦስፖርት ዘገባ ከሆነ ነይማር የካታላኑን ክለብ ለመክሰስ የወሰነው ባለፈው አመት ውሉን ባደሰበት ወቅት “ሊከፈለኝ የሚገባ የ 23 ሚልየን ፓውንድ የጉርሻ ክፍያ አልተከፈለኝም ” በሚል ነው፡፡

እጅግ ተወዳጅ ከነበረበት የኑካምፕ ቤት ወደፓሪስ ያቀናው ነይማር ወኪሉ ከሆኑት አባቱ ጋር በመሆን ለክስ እየተዘጋጁ መሆኑ መሰማቱ በክህደት እያብጠለጠሉት ለሚገኙት የብሉ ግራናዎቹ ደጋፊዎች ይበልጥ ጥላቻን የሚፈጥር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ባርሴሎና በበኩሉ በቃል አቀባዩ ጆሴፍ ቪቬስ አማካኝነት ገንዘቡን እንደማይከፍሉና ለዚህም በቂ ምክንያት እንዳላቸው አሳውቀዋል፡፡

እንደቃል አቀባዩ ገለፃ ” የጉርሻ ገንዘቡን የማንከፍልበት ሶስት በቂ ምክንያቶች አሉን፡፡ የመጀመሪያው ከ ጁላይ 31 በፊት ከየትኛውም ክለብ ጋር ድርድር እንዳያደርግ የተደረሰውን ስምምነት መጣሱ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በስምምነታችን መሰረት የኮንትራት ውሉን ለማጠናቀቅ መወሰኑን በይፋ ለህዝብ ማሳወቅ ነበረበት፡፡ የመጨረሻውና ሶስተኛው ደግሞ ክፍያውን ለመፈፀም የወሰነው ሴፕቴምበር 1 ላይ ነበር፡፡(ከአንድ ወር በኋላ) ይህም ተጫዋቹ ከኛ ጋር መቆየቱን እርግጠኛ ለመሆን ነው፡፡እነዚህ ሶስት ስምምነቶች በመጣሳቸው ለተጫዋቹ የምንከፍለው ምንም አይነት ገንዘብ አይኖርም” ብለዋል፡፡.

ከሳምንት በፊት በ198 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ወደፈረንሳይ ያቀናው ኔይማር እሰካሁን ለአዲሱ ክለቡ እንዳልተጫወተ ይታወቃል፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *