” እጃቸው ረጅም ስለሆነ መረጃውን ከየት እንዳገኙት አላውቅም ” ይላል ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጀርመን ሬዲዮ ዘጋቢ አሜሪካኖች መረጃውን እንዴት አገኙት? ወይም ከየት አመጡት? ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ። በግል የሚያውቃቸውን ባልደረቦቹንና አንድ ከድሬደዋ ጅጅጋ የሚመመላለስ የሚኒ ባስ አሽከርካሪም ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ፣ አንድ ዙር ደርሶ እንደተመለሰና ለድጋሚ እየተዘጋጀ መሆኑንን እንደነገረው ዘጋቢው ለነጋሽ መሐመድ ከአዲስ አበባ ሲያስረዳ ይሰማል። የአሜሪካ ኤምባሲ ዘገባ ” በሬ ወለደ ነው” ባይልም ዮሐንስ ያነጋገራቸውንና የኢትዮጵያ መንግስት ካሰራጨው ዜና ጋር አዳምሮ የተባለው ሁሉ ውሸት መሆኑንን ነው ያሰመረበት።

ከአዲስ አበባ ወደ ጂጂጋ የሚወስደው አዉራ ጎዳና «በፀጥታ አስከባሪዎች ተዘግቷል ፤በአካባቢዉ የተኩስ ልዉዉጥ ተደርጓል» በማለት በአዲስ አበበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ያሠራጨዉን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ነው የጀርመን ሬዲዮ ይህን የዘገበው። በዘገባው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል መካከል ያለውን የድንበር ማካለል ስራ ለመስራት ወደ ስፍራው የሄዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ፍንጭ ተሰጥቷል። እነዚህ ክፍሎች ህዝቡ ስለማያውቃቸው ” አይሆንም” በማለቱ ስራቸውን ሳይሰሩ መመለሳቸውም ተመልክቷል።

Related stories   የባይደን አስተዳደር ፖሊሲ አምስተኛው ምሰሶ የኢትዮጵያ ዙፋን ላይ የሚቀመጠዉን ቡድን መወሰንና የ 2021 ምርጫን ማዋደቅ (1ኛ ክፍል 2)

“አይሆንም” የተባሉት የድንበር አካላይ ሃይሎች፣ ነዋሪዎቹ በመቃወማቸው ሳቢያ ሊሰሩት ያሰቡትን ሳይሰሩ መመለሳቸው ብቻ በስፍራው የታየ አዲስ ነገር ከመሆኑ ሌላ ምንም ኮሽ ያለ ነገር እንደሌለ ማስተባበያ ቀርቧል። ታዲያ ማስተባበያው እንዲህ ከሆነ፣ የአሜሪካን ኤምባሲ ምን ዓይነት መረጃ አግኝቶ መግለጫ አወጣ? የሚለው መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል።

ኤምባሲው ያወጣው መግለጫ በየአቅጣጫው ተተርጉሞ ከፍተኛ ሽፋን ያገኘ ዜና መሆኑና የአሜሪካን ኤምባሲ መግለጫው ስህተት እንዳለው ጠቁሞ ያለው ነገር አለመኖሩ አለ ከተባለው ግጭት በላይ ሌላ ዜና ሆኗል። በኢትዮጵያ በኩል አሜሪካ ቀደም ሲል የጣለችውን የጉዞ ማስጠንቀቂያ እንድታነሳ ከፍተኛ ፍላጎት አለ። ሆኖም ግን በአሜሪካ በኩል ውትወታው ” አይሰማም ” አይነት ምላሽ ነው እስካሁን ያለው።

ችግሩ አሜሪካን ላይ ብቻ የሚያቆም ሳይሆን፣ ሁሉም አሜሪካን ተከታይ በመሆኑ አሜሪካ እያደሰች የምታወታው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በአገሪቱ የቱሪስት ፍሰትና የውጪ ኢንቨስትመንት ላይ ተጽዕኖው ቀላል እንዳልሆነ ነው በቀጥታም ባይሆን በተዛዋሪ የሚወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ስትወትውትና ስታስጠነቅቅ የነበረችው አሜሪካ በሽግግር ጊዜ ውስጥ ብትሆንም እንደ ቀድሞው ከኢህአዴግ ጋር ” እርጥብ እናቃጥል” የሚሉበት ወቅት ላይም አይገኙም።

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

ከሁሉም በላይ በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ ኤች አር 128 የተባለውን አዲስ የህግ ረቂቅ ሲያጸድቅ ኢህአዴግን እነሄዝቦላና ደቡብ ኮሪያ እንዲሁም ቬንዙዌላ አግዳሚ ላይ ማስቀመጡ፣ ” አሜሪካና ኢህአዴግ ወዴት ወዴት” በሚል ነገሮችን መተንተንና ተንተነውም መተንበይ ለሚችሉ ጉዳዩ ፖለቲካዊ ፋይዳው ከመቼውም ጊዜ በላይ የጋለ ደረጃ መድረሱን የሚያመላክት መሆኑንን እየጠቆሙ ነው። እንግዲህ ይህ ግለት ባለበት ሁኔታ ነው የአሜሪካ ኢምባሲ የጅርመን ድምጽ ” ኮሽ ያለ ነገር የለም” ሲል አየር ላይ የጣለውን ዜና ምንነትና ምክንያት ጉያዋ ይዛ ዝም ያለችው።

Related stories   ዓለም ባንክ ተከተለ – ግብጽ ሚስጥሩን ይፋ አደረገች

በተለያየ መልኩ የሚሰነዘሩት አስተያየቶች በሁለቱ የቀድሞ ወዳጆች መካከል ነፋስ ገባ ቢባልም፣ ከኢህአዴግ በኩል በቀጥታ የተሰጠ መልስ የለም። አዲስ ረቂቅ ህጉንም አስመልክቶም የተሰጠ ምልሽ ስለመኖሩ አልተሰማም። ለአሜሪካ ዲፕሎማቶች ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት የውስጥ ለውስጥ የውስወሳ ወይም የሎቢ ስራ እየተሰራ መሆኑንን እንደሚያውቁ ይናገራል።

የሁሉንም ዜና ወደ ጎን በመተው አስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ግን ከሃረር በታች መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን የናገራሉ። በዚህም ሳቢያ ዜናውን ለማጣጣል እንደሚከብድ ያስታውቃሉ። ኢሳትና ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ እንዲሁም የአሜሪካ ሬዲዮ ዜናውን እንደወረደ የኤምባሲውን መግለጫ ተንተረሰው ዘገበዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ከኤምባሲው መግለጫ በተጨማሪ ምንጮች ነገሩኝ ሲል ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱን ጠቁሟል። ይሁን እንጂ የጀርመን ሬዲዮ ሁሉንም ዜና በዜሮ የሚያጣፋ ዘገባ አቅርቧል። በተባለው ቦታ “ምንም ኮሽ ያለ ነገር የለም” በሚል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *