በአሉ ግርማ በ“ከአድማስ ባሻገር” ገጸባሕርያቱን ሲስል እጅጉን ተጠብቦበት እንደነበር ያስታውቃል። የመጀመሪያው ልብወለዱ መሆኑን ስናስታውስ ደግሞ የበለጠ ግሩም ባለሙያነቱን ያሳየናል።

via የበአሉ ግርማ ገጸባሕርያት — አንድምታ

ከብሩክ አብዱ

.

በአሉ ግርማ (1931-1976 ዓ.ም) ልጅነቱን ያሳለፈው በሱጴ (ኢሉባቦር)፣ ጉርምስናውን ደግሞ በአዲስ አበባ (“ልዕልት ዘነበወርቅ” እና “ጀነራል ዊንጌት” ት/ቤቶች) ነበር። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እና በMichigan State University የጋዜጠኝነትና የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርቱን ተከታትሏል። የሥራ ዘመኑንም ባብዛኛው ያሳለፈው በማስታወቂያ ሚኒስትር በተለያዩ የኀላፊነት ቦታዎች ነበር።

በአሉ ስድስት ተወዳጅ ልቦለድ ሥራዎችን አሳትሟል። እኒህም “ከአድማስ ባሻገር” (1962 ዓ.ም)፣ “የህሊና ደወል” (1966 ዓ.ም)፣ “የቀይ ኮከብ ጥሪ” (1972 ዓ.ም)፣ “ደራሲው” (1972 ዓ.ም)፣ “ሀዲስ” (1975 ዓ.ም) እና “ኦሮማይ” (1975 ዓ.ም) ናቸው። ከኒህም በተጨማሪ በርካታ መጣጥፎችን፣ ቃለ-መጠይቆችን እና ርእሰ አንቀጾችን ጽፏል።

በዚች ጽሑፍ፣ በአሉ ግርማ “ከአድማስ ባሻገር” መጽሐፉ ላይ የተጠቀመባቸውን አንዳንድ የገጸባሕርያት አሳሳል ስልቶች በቅርበት ለማሳየት እሞክራለሁ።

.“ከአድማስ ባሻገር”

ይህ መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ የበቃው በ1962 ዓ.ም ነበር። ምንም እንኳን ዳግመኛ እስኪታተም ሁለት አመት ቢፈጅበትም በወጣበት ዘመን በሰፊው ተነቧል (ከ1962 እስከ 2004 ዓ.ም ዘጠኝ ጊዜ ታትሟል)። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ደግሞ በሬድዮ ትረካ ቀርቧል።

Related stories   Egypt-Sudan alliance shifting in row with Ethiopia over Nile dam

ከአድማስ ባሻገር” የበአሉ ግርማ የመጀመሪያ የልብ ወለድ መጽሐፍ ቢሆንም በኩር የፈጠራ ሥራው አልነበረም። ከዚያ በፊት በአሉ በተለያዩ የተማሪ መጽሔቶች (የጄነራል ዊንጌቱ “Chindit” እና የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ “News and Views”) ግጥሞቹን ማቅረብ ለምዶ ነበር። ከፈጠራ ድርሰት ባሻገርም በጋዜጣና መጽሔት አዘጋጅነት (“News and Views”፣ “Addis Reporter”፣ “መነን” እና “አዲስ ዘመን”) የበርካታ አመታት ልምድ ነበረው። በኒህም አመታት በተቻለው መጠን የአዘጋጅነቱን ሚና በመጠቀም (በተለይ በ”መነን” እና “አዲስ ዘመን”) በርካታ ኪነጥበባዊ አምዶችን (ለምሳሌ “አጭር ልብወለድ”፣ “ከኪነጥበባት አካባቢ”) አስጀምሮ  ነበር።

ስለዚህ ከመጀመሪያው ልብወለዱ ኅትመት በፊት በአሉ ቢያንስ ለአስር አመታት ያህል ኪነጥበባዊ ጽሑፎችን ሲያነብ፣ ሲጽፍና ሲያዘጋጅ የከረመ ደራሲ ነበር። እናም የበኩር መጽሐፉ እምብዛም የጀማሪ ድርሰት የጀማሪ ድርሰት ባይሸት ብዙ ሊያስደንቀን አይገባም።

ከአድማስ ባሻገር” ታሪኩ በግርድፉ የሚከተለውን ይመስላል። እድሜውን በዘመናዊ ትምህርት ያሳለፈ አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት (አበራ) የምርጫ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በአንድ ወገን፣ ብዙም ስሜት በማይሰጠው ሥራ በመትጋት ንብረትና ልጆች እንዲያፈራ ወንድሙ (‘ጋሽ’ አባተ) ቤተሰባዊ ግዴታውን ያስታውሱታል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ “ጥሪውን” በመስማት ሥራውን ለቆ ሙሉ ሕይወቱን በሰአሊነት እንዲያሳልፍ አብሮ አደጉ (ሀይለማርያም) እና አዲሲቷ ፍቅረኛው (ሉሊት) ይገፋፉታል። አበራ ግን የሚፈልገውን የሚያውቅ አይመስልምና መምረጥ ይቸግረዋል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

የአበራም ወላዋይነት በራሱ፣ በቤተሰቡ፣ በጓደኛውና በፍቅረኛው ሕይወት ውስጥ የሚያስከትሉትን ለውጦችና መዘዞች ድርሰቱ በጥልቀት ይተርካል። እግረመንገዱንም፣ ደራሲው የዛሬ ሀምሳ አመት ግድም በነበረው የአዲስ አበባ ማኅበረሰብ ውስጥ ይፋጩ የነበሩትን “ባህላዊነት” እና “ዘመናዊነት”፣ “ሀላፊነት” እና “ጥሪ”፣ “መተማመን” እና “ቅናት” በገጸባሕርያቱ በኩል ያሳየናል።

ይህ ልብወለድ ከ50 በላይ ገጸባሕርያትን አቅፎ ይዟል። ከእነዚህም አራቱ ዋና ገጸባሕርያት (አበራ፣ ሀይለማርያም፣ ሉሊት፣ ‘ጋሽ’ አባተ)፥ ሰባቱ ጭፍራ (‘እሜቴ ባፈና፣ ሰናይት ‘ሱቅ በደረቴ’ …)፥ ሃያዎቹ አዳማቂ (ሱዛን ሮስ፣ ትርንጐ፣ ሚኒስትሩ …)፥ እና ከሃያ በላይ ደግሞ ስውር ገጸባሕርያት (ወፍራም ዝንብ፣ ባይከዳኝ …) ናቸው።

‘ዋና’ ገጸባሕርያትን እንደድርሰቱ አጥንት፣ ‘ጭፍራ’ ገጸባሕርያትን ደግሞ እንደትረካው ሥጋ ልናያቸው እንችላለን። ያለኒህ አስር ግድም ገጸባሕርያት “ከአድማስ ባሻገር”ን አንብቦ ለመረዳት በጣም ያስቸግራል (አንድ ተማሪ “መጽሐፉን ወደ ተውኔት ለውጠህ ጻፍ” ወይም “ልብወለዱን ላናበቡ ጓደኞችህ በአጭሩ ተርክ” ቢባል እኒህኑ ዋና እና ጭፍራ ገጸባሕርያት መጠቀሙ አይቀርም)። በተመሳሳይ መልኩ “አዳማቂ” ገጸባሕርያትን እንደ ክት አልባሳት ብናያቸው ያስኬዳል፤ እጅጉን ባያስፈልጉም ድርሰቱን በሚገባ ያስጌጡታልና።

ታዲያ የደራሲውን ጥበብ ለመረዳት አንዱ መንገድ የፈጠራቸውን ገጸባሕርያት በምን መልኩ ተንከባክቦ እንዳሳደጋቸው ለመረዳት መሞከር ነው። በመቀጠልም፣ “ከአድማስ ባሻገር” ውስጥ ወሳኝ ባይሆንም ጠቃሚ ሚና ከሚጫወቱት ሃያ “አዳማቂ” ገጸባሕርያት አምስቱን መርጬ እንዴት አድርጎ በአሉ ግርማ እንደሳላቸው ለማሳየት እሞክራለሁ።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

እኒህንም አዳማቂ ገጸባሕርያት የመረጥኩበት ምክንያት እንደሚከተለው ነው። አብዛኛውን ጊዜ ደራሲዎች የዋና እና ጭፍራ ገጸባሕርያት አሳሳል ላይ ልዩ አትኩሮት (እንዲሁም በርካታ ገጾችን) ይሰጣሉ። በዚህም ምክንያት፣ የገጸባሕሪ አሳሳል ችሎታቸውን በሚገባ ለመመዘን ያስቸግረናል … ብዙም ባልተካነ ደራሲ እጅ እንኳን የዋና ገጸባሕርያት አሳሳል የስኬት ሚዛን ሊደፋ ይችላልና።

በአንጻሩ፣ በልብወለዱ ወሳኝ ሚና የማይጫወቱትን “አዳማቂ” ገጸባሕርያትን ለመሳል ደራሲው በአማካይ ከአንድ ገጽ በላይ ቀለም አያጠፋም። እኛም እንደ አንባቢነታችን እኒህን መስመሮች በቅርበት በማስተዋል “ደራሲው ባለው ውስን እድል ገጸባሕሪውን በሚገባ አዳብሮታልን?”፣ “የገጸባሕሪው ልዩ የሆነ ምስል በምናባችን ሊሳል ተችሏልን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ መሞከር እንችላለን። በሌላ አነጋገር፣ ማንኛውም ደራሲ በበርካታ ገጾች ገለጻ እና ንግግር አንድን ገጸባሕሪ በጉልበት ምናባችን ውስጥ ቢያስገባውም፣ ጥበበኛ ደራሲ ግን በአንዲት አንቀጽ ብቻ አይረሴ ምስል በአእምሯችን ሊቀርፅ ይችላል።

እናም የዚህ መጣጥፍ ጥያቄ፤ “በገጸባሕርያት አሳሳል ረገድ በአሉ ግርማ ምን አይነት ደራሲ ነው?” የሚል ይሆናል። read more on የበአሉ ግርማ ገጸባሕርያት — አንድምታ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *