ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

አዲስ አድማ ተጠራ፤ አዲሱ የቁቤ መጽሃፍ ታገደ

ato adisu aregaአዲሱ የኦሮምኛ ማስተማሪያ መጽሃፍ ስራ ላይ እንዳይውል ተወሰነ። ውሳኔው ይፋ የሆነው በኦሮሞ ቄሮዎች የተጠራውን የአምስት ቀን ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማ ተከትሎ መሆኑ ቢጠቆምም የክልሉ መንግስት ግን መጽሃፉ ችግር እንዳለበት በጥናት በመታመኑ መሆኑንን አስታውቋል። በሌላ በኩል  የኦሮሚያ ክልል ለአምስት ቀን ተጠራ ስለተባለው አድማና ተቃውሞ እስካሁን ያለው ነበር የለም።

ቄሮ በሚል ስያሜ ራሳቸውን በህቡዕ ያደራጁት የኦሮሞ ወጣቶች አሰራጩት በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች የተቀባበሉት ጽሁፍ እንደሚያስረዳው ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማው የሚጀመረው ከነሃሴ 17 ጀምሮ እስከ 21 / 2009 ድረስ ነው። በተለያዩ የኦሮሞ ደጋፊ ሚዲያዎችም ቢሆኑ ያረጋገጡት ይህንኑ ነው። እንዲያውም ይህ ተቃውሞ በሌሎች ክልሎችም ድጋፍ እንዲያገኝ ጥሪ መቅረቡን ነው ሚዲያዎች ይፋ ያደረጉት።

ይህ እስከታተመ ድረስ የኦሮሚያ ክልላዊም ሆነ የፌደራሉ መንግስት የተጠራውን አድማ ተከትሎ በይፋ ያሉት ነገር የለም። ይልቁኑም የልክልሉ መንግስት በዩኤስ አይዲ ድጋፍ የታተመው አዲሱ የአንደኛ ደረጃ ማስተማሪያ የቁቤ መጽሃፍ ስራ ላይ እንዳይውል መታገዱን ነው። ፋና የክልሉ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱን ጠቅሶ እንደገለጸው ከሆነ አዲስ የታተመው የማስተማሪያ መጽፍሃፍ ችግሮች አሉበት። ችግር እንዳለው የተረጋገጠው በባለሙያዎች ጥናት ተደርጎበት ነው።

Related stories   የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዲስ የአደረጃጀት ሰነድ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀረበ

ቄሮዎች አሰራጩት የተባለው ጥሪ አድማውን ሊያደናቅፉ የሚሞክሩ ክፍሎችን አስጥንቅቋል። ከማስጠንቀቂያም በላይ በየአካባቢው ያሉ አደረጃጀቶች ርምጃ እንዲወስዱ ሙሉ ሃላፊነት ሰትቷል። ይሁን እንጂ ርምጃው ምን እንደሆነ አልተበራራም። በጥቅሉ ግን ከዚሁ ርምጃ ጋር ተያይዞ ለሚወድም ንብረት ጠጠያቂዎቹ አድማውን በመታስ ለምንቀሳቀስ የሞከሩ ባለንበቶች መሆናቸውን አመልክቷል።ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች የጤና ተቋማት ግን ይሄ በቄሮ የተጠራው አድማ እንደማይመለከታቸው ተመልክቷል።

ይኸው ምንጩ ይፋ ያልሆነና በህቡዕ የሚሰራው ስራ ስጋት ላይ እንደጣለው የተገለጸለት መንግስት ስጋት እንደገባውም ይሁን በሌላ መልኩ አድማውን አስመልክቶ ማሳሰቢያም ሆነ ማስተንቀቂያ አላሰማም። እንዲያውም ዝምታን ነው የመረጠው። ቀደም ሲል የአዲሱን የገቢ ግብር ተመን ተከትሎ ሱቆችን የመዝጋት አድማ በኦሮሚያ ከተሞች ተደርጎ እንደነር ያታወሳል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ አዲሱ የገቢ ግብር ትመና አርባ ከመቶ ችግር ያለበት እንደሆነ በማመን በሰጡት መግለጫ ” የመርጃና የግንዛቤ ችግር፣ ሌብነት መንግስታችንን አስቸግሯል” ሲሉ ተደምጠዋል። ይኽው የንግድ ቤቶችን የመዝጋት አድማ በአማራ ክልልም በስፋት የተስተዋለ ነበር። በተለይም በባህር ዳር ችግሩ አሳሳቢ በሚባል መልኩ ተከስቶ እንደነበር እማኞች ለገለልተኛ ሚዲያዎች ተናገረው ነበር።

Related stories   አየር ሃይል " ትዕግስትም ልክ አለው" ሲል ለሱዳን ምክረ ሃሳብ ሰጠ

በማንነት ጥያቄ፣ በድንብበር ውዝግብ፣ በመልካም አስተዳደር ጥያቄና በተለያዩ ፖለቲካዊ አለመግባባቶች በኢትዮጵያ ታይቶ ያልታወቀ ተቃውሞ ተነስቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ አይዘነጋም። በቅርቡ የአዋጁን መነሳት ተከትሎ የታዩት የተቃውሞ አካሄዶች መድረሻቸው ባይታወቅም መደጋገማቸው ስጋት እንደሆነ ገለልተኛ ወገኖች ይናገራሉ። መንግስት በበኩሉ በየክልሉ በአዲስ መለክ በመቶ ሺህ የሚቆተሩ ሚሊሻዎች ማደራጀቱን፣ እንዲሁም የድርጅት አባላት ክለሳ ማካሄዱን በመጥቀስ ካሁን በሁዋላ ተመሳሳይ ረብሻ ሊነሳ እንደማይችል የአስቸኳይ ጌ አዋጁን ሲያነሳ አስታውቋል።

ፋና የታገደውን አዲሱን መጽሃፍ አስመልክቶ የሚከተለውን ዘግቧል። አዲሱ የ1ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት የአፋን ኦሮሞ ማስተማሪያ መጽሃፍ ጥቅም ላይ እንዳይውል መከልከሉን የክልሉ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። አዲሱ የማስተማሪያ መጽሃፍ ላይ በተደረገ ጥናት ችግር እንዳለበት በመለየቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል መከልከሉን የቢሮው ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።

 

“ምሁራን በመጽሃፉ ላይ ባደረጉት ጥናት መጽሃፉ ላይ በርካታ ችግሮች እንዳሉበት ተለይቷል” ያሉት አቶ አዲሱ፥ የክልሉ መንግስት ካቢኔም የጥናቱን ውጤት ሙሉ በሙሉ በመቀበል አዲሱ የአፋን ኦሮሞ ማስተማሪያ መጽሃፍ ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል ብለዋል። በ1ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት ከሶስት ዓመት በፊት በስራ ላይ የነበረውን መጽሃፍ ወደ ስራ በመመለስ የመማር ማስተማሩ ሂደት ሳይስተጓጎል እንደሚቀጥልም ሃላፊው ተናግረዋል።

Related stories   "የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎችን ላለመላክ የወሰነው የማይታዘዝና የማያጎበድድ መንግሥት ይመጣል የሚል ስጋት ነው"አንዳርጋቸው ፅጌ

አዲሱ መጽሃፍ የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የአፋን ኦሮሞ “ቁቤን” (LAGIM…) ከሚል ጀምሮ እንዲማሩ የሚያደርግ ነበር። ይህ መጽሃፍ ጥቅም ላይ እንዳይውል መደረጉን ተከትሎም የ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች የአፋን ኦሮሞ ቁቤን ከዚህ በፊት እንደነበረው (ABCD…) ከሚለው በመጀመር እንዲማሩ የሚደረግ ይሆናል ተብሏል። አቶ አዲሱ አረጋ በፌስ ቡክ ገጻቸው ሰበር ሲሉ የሚከተለውን አስፈረዋል።  #Breaking

Bu’aan qorannoo hayyootaa Kitaabotni Afaan Oromoo haaraan rakkoo hedduu akka qabu mirkaneessee jira.Kaaabineen Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa bu’aa qorannoo kanaa guutummaatti fudhachuun kitaabotni haaraan Afaan Oromoo (LAGIM…) faayidaa irra akka hinoolle murteessee jira.

Barattoonni sadarkaa 1ffaa Kitaabota waggoota sadiin dura hojiirra turan (ABCD…) hojiitti deebisuun sirni baruu fi barsiisuu rakkoo tokko malee akka itti fufu murtaa’eera.

Hayyoota Oromoo halkanii fi guyyaa hojjetaanii rakkoo jiru karaa saayinsaawaa ta’een qorannoo gaggeessuun yaada murtii beekumsa irratti hundaa’ee nuuf dhiyeessaniif galata guddaa qabna.