የ 2017 ተጠባቂው የባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ የ 32ቱ ቡድኖች ምድብ ድልድል ባሳለፍነው ሀሙስ ምሽት በሞናኮ ፈረንሳይ በተደረገ ልዩ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ይፋ ሆኗል። እኛም በአርቡ የቅድመ ትንታኔም ክፍል አንድ ጥንቅራችን ከ 32 ቱ የአውሮፓ ሀያላን የ 16ቱን ቡድኖች ወይም የመጀመሪያ አራት ምድቦች ቅድመ ትንታኔ እንዳስመለከትናችሁ አይረሳም። ቀጣዩ የክፍል ሁለት ዝግጅት ደግሞ ቀሪዎቹን አራት ምድቦች […]

via የትንታኔ ጥንቅር (ክፍል ሁለት) / የቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ቅድመ ቅኝት — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የ 2017 ተጠባቂው የባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ የ 32ቱ ቡድኖች ምድብ ድልድል ባሳለፍነው ሀሙስ ምሽት በሞናኮ ፈረንሳይ በተደረገ ልዩ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ይፋ ሆኗል። እኛም በአርቡ የቅድመ ትንታኔም ክፍል አንድ ጥንቅራችን ከ 32 ቱ የአውሮፓ ሀያላን የ 16ቱን ቡድኖች ወይም የመጀመሪያ አራት ምድቦች ቅድመ ትንታኔ 


ምድብ ሀ

ቤኔፊካ፣ ባሴል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሲኤስኬ ሞስኮ

ጆሴ ሞውሪንሆ ያለምንም ጥርጥር የፈለጉትን አይነት የምድብ ድልድል አግኝተዋል። ዩናይትድ በዚህ ክረምት ሮሜሉ ሉካኩን በፊት መስመር ላይ ዳግም ካመጣው ዝላታን ጋር አጣምሮ ይዟል። የቡድኑን አማካኝ መስመር ለማጠንከርም ማቲች ኦልትራፎርድ ደርሷል።

በሌላ በኩል ኤደርሰን፣ ቪክተር ሊንድሎፍ እና ሌንሰን ሴሜዶን በዚህ ክረምት የሸጠው ቤኔፊካ የውድድሩ ምርጥ የፖርቹጋል ተወካይ ነው። በቤኔፊካ ቤት ብሩኖ ቫሬላ ለኤደርሰን በጣም ጥሩው ተተኪው ሲሆን ፒዚና አሌክስ ግሪማልዶን ማቆየታቸው ደግሞ ለቀጣይ ዋስትና ይሆናቸዋል።

ሲኤስኬ በበኩሉ ከሌሎቹ አንፃር ደካማ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ባለፉት ሳምንታት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። የሩሲያው ተወካይ በአዲሱ አሰልጣኙ ኢጎር አክኒፌቭ ስር ለ 11 አመታት በቻምፒዮንስ ሊግ ሁሌም ጎል እየተቆጠረበት የሚወጣበትን ታሪክ ከሰሞኑ መቀየር ችሏል።

ሌላኛው የምድቡ አራተኛ ቡድን ባሴል በበኩሉ ዝነኛውን ተጫዋቹን ማቲያስ ዴልጋዶን ያሰናበተ ሲሆን የምድቡን ግርጌ ይዞ እንደሚያጠናቅቅም ተገምቷል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ማንችስተር ዩናይትድ 2 ቤኔፊካ 3 ሲኤስኬ ሞስኮ 4 ባሴል

ምድብ ለ

ባየር ሙኒክ፣ አንደርሌክት፣ ፒኤስጂ እና ሴልቲክ

በዚህ ምድብ ሁሉም አይኖች በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ደረጃ የሚያስቀምጠኝን የኔይማርን ዝውውር ፈፅሜያለሁ ብሎ በተኩራራው ፒኤስጂ ላይ ማረፋቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ዣቪ አሎንሶንና ፊሊፕ ለሀምን የሸኘው ባየር ሙኒክ የአምና ጥንካሬው ላይ መገኘቱ የሚያጠራጥር ነው።

ሴልቲክ በበኩሉ ከአንደርሌክት ሶስተኛ ደረጃን እንደሚነጥቅና በሜዳው ባየርንና ፒኤስጂን ሊያስቸግር እንደሚችል የሚጠበቅ ነው። ነገርግን ምድብ ለ ትልቅ የአቅም አለመመጣጠን ችግር ያለው ምድብ መሆኑ የማያጠራጥር ነው።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ባየር ሙኒክ 2 ፒኤስጂ 3 ሴልቲክ 4 አንደርሌክት

ምድብ ሐ

ቼልሲ፣ ሮማ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ካራባጅ

አትሌቲኮ ባለፉት አራት አመታት በውድድሩ ላይ ለሁለት ጊዜያት ለፍፃሜ የመድረሱን ስኬት ከተመለከትን የስፔኑ ክለብ የምድቡ በላይ ሆኖ እንደሚጨርስ ይገመታል። አትሌቲኮዎች በተወሰነባቸው የዝውውር እገዳ ከሲቪያ የገዙትን ቪቲሎን ጭምር በውሰት ለመስጠት ቢገደዱም ግሪዝማን በክለቡ መቆየቱ አንድ ጥሩ ነገር ነው።

ቼልሲ በበኩሉ ከበርንሌይ ጋር በነበረው ጨዋታ ከቅርፅ ውጪ ሆኖ ቢታይም በጥብቅ መከላከል ቶትነሀምን 2-1 በመርታት ማንሰራራቱን ያሳየ ቢሆንም ኮንቴ ከዚህ ቀደም በጁቬንቱስ በ 2012/13 ቡድናቸው ከሩብ ፍፃሜው ማለፍ ሲሳነው በቀጣዩ አመት ምድቡን መሸጋገር በራሱ አቅቶት እንደነበር አይረሳም።

ሮማ በበኩሉ በአዲሱ የስፖርት ዳይሬክተሩ ሞኑቺ አማካኝነት መሀመድ ሳላ፣ አንቶኒ ሩዲገርን የመሰሉ ኮከቦችን ሲሸጥ መተኪያ የሌለውን ፍራንሲስኮ ቶቲን በጡረታ አጥቷል። ነገርግን በተቃራኒው 10 ተጫዋቾችን መቀላቀሉ ለሶስተኛነት እንኳን እንዲገመት ያደርገዋል።

ካራባጅ በበኩሉ አዘርባጃንን በምድቡ የወከለ የመጀመሪያው ቡድን ሲሆን አሰልጣኙ ጉርባን ጉርባኖቭ ከ 2008 አንስቶ በክለቡ አሰልጣኝነት የቆዩና የደቡብ አፍሪካውን ዲኖ ድሎቩን ቀዳሚ ማረፊያ በማድረግ በሶስት አጥቂ መጫወትን ይመርጣሉ።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት  :  1 አትሌቲኮ ማድሪድ፣ 2 ቼልሲ 3 ሮማ 4 ካራባጅ

ምድብ መ

ጁቬንቱስ፣ ኦሎምፒያኮስ፣ ባርሴሎና፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን

ባሳለፍነው አመት በሩብ ፍፃሜው ባርሴሎናን ያሰናበተው ጁቬንቱስ ከስፔኑ ክለብ ዳግም የሚፋጠጥበት ከባድ ምድብ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በዚህ ክረምት ዋነኛ ተጫዋቾቻቸው የሆኑት ሊኦናርዶ ቦኑቺ ሳይጠበቅ ሚላንን ሲቀላቀል ኔይማር በበኩሉ ኒውካምፕን ለቆ ወደ ፓሪስ አምርቷል።

ጁቬ በጣሊያን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ከላዚዮ ጋር በነበረው ትንቅንቅ በመከላከል ላይ ምን ያህል መድከሙ የታየ ቢሆንም የቱሪኑ ክለብ ምርጥ ስብስብ ያለውና ፌደሪኮ በርናንዲሽን በ 35.7  ሚሊዮን ፓውንድ ከፊዮረንቲና በማስፈረም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በሌላ በኩል በባርሴሎና ቤት ማርኮ ቬራቲ አለመፈረሙና በምትኩ የቀድሞው የስፐርስ አማካኝ መምጣቱ በባርሴሎና ደጋፊዎች ዘንድ ሀዘን ቢፈጥርም የካታላኑ ክለብ ስብስቡን ለማጠናከር ፊሊፔ ኩቲንሆንና ኦስማን ዴምቤሌን ለማስፈረም እየተጋ ይገኛል።

በአዲሱ አሰልጣኙ ቤስኒክ ሀሲ ራሱን እያደሰ የሚገኘውና በዝውውር መስኮቱ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣው ኦሎምፒያኮስ በበኩሉ ምድቡን በሶስተኛነት እንደሚያጠናቅቅ ግምት ያገኘ ሲሆን አማካኙን ዊሊያም ካርቫልሆን የሸጠው ስፖርቲንግ ደግሞ ከሁሉም ያነሰ ግምት ተሰጥቶታል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት  :  1 ጁቬንቱስ 2 ባርሴሎና 3 ኦሎምፒያኮስ 4 ስፖርቲንግ

ምድብ ሠ

ስፖርታክ ሞስኮ፣ ሊቨርፑል፣ ሲቪላ እና ማሪቦር

በዚህ ተመጣጣኝ ቡድኖችን በያዘው ምድብ ሊቨርፑል ባለፉት ሶስት አመታት ሶስት የተለያዩ አሰልጣኞች ከቀያየረው ሲቪላ ቀድሞ ምድቡን ከላይ ሆኖ እንደሚያጠናቅቅ ትልቅ ግምት አግኝቷል።

በሌላ በኩል ግን ኤድዋርዶ ቤሪዞ የሚመራው የስፔኑ ክለብ ቪቶሎን ለአትሌቲኮ ሸጦ በምትኩ ኤቨር ባኔጋ፣ ጂሰስ ናቫስ እና ኖሊቶን ማስፈረሙ ከፊት መስመር ላይ የሚያስፈራውን ነገርግን የኋላ መስመሩ የሳሳውን የየርገን ክሎፕ ስብስብ ለመፈተን መጠነኛ አቅም እንደሚፈጥርለት መጠርጠር ይገባል።

የሩሲያው ስፖርታክ በበኩሉ ባሳለፍነው አመት ከ 2001 በኋላ የመጀመሪያ የሊግ ድሉን ከአስደናቂ ብቃት ጋር ቢያሳይም ዘንድሮ 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ እና የአንቶኒዮ ኮንቴ ምክትል የነበሩት የክለቡ አለቃ ማሲሞ ካሬራ ቡድናቸው እያሳየ ባለው ደካማ አቋም የስንብት እጣ ሊደርሳቸው የሚችልበት እድል ሊኖር የሚችል ሲሆን የቡድኑ ሆላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኪዊንስ ፕሮምስ ግን የቡድኑ ያልተነገረለት ከባድ የጥቃት ሀይል ነው።

በመጨረሻም የምድቡ አራተኛው ተፋላሚ ማሪቦር እስካሁን በታሪኩ ካደረገው 12 የቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ አንድ ብቻ ያሸነፈ ደካማ ስብስብ ሲሆን የአጥቂ አማካኙን ዴር ቭርስኪን ማጣቱ ሲታከልበት በምድቡ ከባድ ፈተና እንደሚጥቀው የሚታመን ነው።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ሊቨርፑል 2 ሲቪያ 3 ስፖርታክ ሞስኮ 4 ማሪቦር

ምድብ ረ

ሻክታር ዶኔስክ፣ ናፖሊ፣ ማንችስተር ሲቲ እና ፌይኖርድ

በክረምት የዝውውር መስኮት ከ 220 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ዋጋ ላወጣው የፔፕ ጋርዲዮላ ስብስብ ምንም አይነት ምህረት አይኖርም። ከዚህ ጋር በተያያዘም የስፔናዊው አለቃ ስብስብ ምድቡን ዘና ብሎ ከላይ ሆኖ የመጨረስ ግዴታ ያለበት ሲሆን ምድቡ አስደናቂውን የማውሪዚዮ ሳሪን ስብስብ ናፖሊ መያዙ እና ሲቲ አሁንም ያለበት የኋላ መስመር መሳሳት በምድቡ የበላይ ሆኖ ለማጠናቀቅ ፈተና ሊጠብቀው እንደሚችል ይነግረናል።

ድሬስ ሜርትንስ፣ ጆሴ ካሌጆን፣ ሎሬንዞ ኢንሲግን፣ አርካዲሁዝ ሚሊክ እና ማርክ ሀምሲክን የያዘውና ከየትኛውም ቦታ ጎል ማስቆጠር የሚችለው ናፖሊ እውነትም አስፈሪ ነው። በሌላ በኩል አምና የዩክሬን ሊግን ክብር በሰፊ የነጥብ ብልጫ የወሰደውና በቅርብ ጊዜ አሌክስ ቴክሴራ እና ዱጋላስ ኮስታ አይነት ኮከቦቹን ያጣው ሻክታር ብዙም ተገማችነት አላገኘም።

በመጨረሻ ደግሞ ከ 18 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቫን ብራንክሆረስት እየተመራ የሆላንድ ሊግን ያነሳው ፌይኖርድ ዲርክ ኳይትን በጡረታ፣ ትሬንስ ኮንጎሉን እና ሪክ ካርስዱርብ የተሰኙ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ደግሞ በሽያጭ ማጣቱ የቡድኑን የምድብ ተፎካካሪነት ይበልጥ እንደሚያወርድበት ይጠበቃል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ማንችስተር ሲቲ 2 ናፖሊ 3 ሻክታር ዶኔስክ 4 ፌይኖርድ

ምድብ ሰ

ሞናኮ፣ ቤሽኪሽታሽ፣ ፖርቶ እና ሊፕዚግ

ከሁሉም ምድቦች በጣም ተቀራራቢ ቡድኖች የተሰባሰቡበት እና ሁሉም እኩል የማለፍ እድል ያለው ፍትሀዊ ምድብ የተባለለትን ምድብ ሞናኮ በርናንዶ ሲልቫ፣ ቤንጃሚን ሜንዲ እና ቲሞ ባካዮኮ የመሳሰሉ ኮከቦቹን ቢያጣም በቀዳሚነት እንደሚያጠናቅቀው ይገመታል።

የፖርቹጋሉ ተወካይ ፖርቶ በበኩሉ አንድሬ ሲልቫን ለሚላን አሳልፎ ቢሰጥም በቲኪኖ ሶአሬዝ ጠንክሮ እንደሚመለስና በአዲሱ አሰልጣኙ ሰርጂዮ ኮንሲካኦ እየተመራ ምድቡን በማለፍ በስኬት እንደሚያጠናቅቅ ሲጠበቅ የውድድሩ አዲስ ተካፋይ የጀርመኑ ሊፕዚግ በበኩሉ የውድድሩ ልምድ አልባነቱ ምድቡ እንዲከብደው ሊያደርግ እንደሚችል ይታሰባል።

በመጨረሻም የክረምት የዝውውር መስኮት ቀንደኛ ተሳታፊ የነበረው ቤሽኪሽታሽ በበኩሉ ፔፔ፣ ጀርሜን ሌንስ እና ጋሪ ሜድል የመሰሉ ተጫዋቾችን ማግኘቱ ተፎካካሪነቱን እንደሚጨምረው ቢጠበቅም የምድቡ ዝቅተኛ ተገማች ነው።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ሞናኮ 2 ፖርቶ 3 አርቢ ሊፕዚግ 4 ቤሽኪስታሽ

ምድብ ሸ

ሪያል ማድሪድ፣ ቶትነሀም፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና አፖል ኒኮሲያ

የአምናው ሻምፒዮና ማድሪድ ዘንድሮም ቀዳሚ ተገማች ሲሆን ከ 1974-76 የባየር ሙኒክ ገድል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የበርናባው ስብስብ ሶስተኛ ተከታታይ የቻምፒዮንስ ሊግ ድሉን እንደሚያስመዘግብ ተጠብቋል።

የስፔኑ ክለብ ትልልቅ ኮከቦቹን በቡድኑ ማቆየት ችሎና ማቲኦ ኮቫቺች፣ ማርኮ አሳንሲዮስ እና ዳኒ ሴባሎስን በመሰሉ ወጣቶች ይበልጥ ገዝፎ የውድድሩን ምድብ ድልድል መጀመር ሲጠብቅ ኦስማን ዴምቤሌን ለባርሴሎና አሳልፎ የሰጠው ዶርትሙንድ በፒተር ቦዝ አሰልጣኝነት ስር ፒዬር ኤምሪክ ኦቦምያንግን በቡድኑ ማቆየት ችሎ እና ጁሊያን ዊግል የመሰለ ኮከቡ ዳግም ብቁ ሆኖለት ይህን የምድብ ድልድሉን ደረጃ ሁለት የሞት ምድብ ከማድሪድ በመቀጠል በሁለተኛነት ሾልኮ እንደሚያልፈው ተጠብቋል።

የምድቡ ሌላኛው ተወካይ ቶትነሀም በበኩሉ በምድቡ ያገኘው ግምት ከስፔንና ጀርመን አቻዎቹ ያነሰ ሲሆን የምድብ እንቅፋቱን በጣጥሶ ለማለፍም በቀጣይ አመት ወደ አዲሱ ስታዲየሙ እስኪዘዋወር ድረስ ዘንድሮ በጊዜያዊነት በሚጠቀምበት ዌብሌይ ያለበትን መጥፎ ገድ ማስወገድ እንዳለበት እየተነገረለት ይገኛል።

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ኮከብ ጎል አስቆጣሪውን ፒሮስ ሶትሪዩን ያጣው አፖል በበኩሉ የምድቡን ግርጌ ታኮ እንደሚቀመጥ ተገምቷል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ሪያል ማድሪድ 2 ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 3 ቶትነሀም 4 አፖል

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *