“Our true nationality is mankind.”H.G.

‘ ቄሮ ‘ አድማው በቃ – ” የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስካልተቻለ ድረስ ትግሉ ይቀጥላል”

” ቄሮ ” የሚባሉት የኦሮሚያ የህቡዕ የለውጥ አደራጆች በኦሮሚያ የታወጀው የአምስት ቀን በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ እንዲቆም ማደረጉን መረጃውን በመቀበል የሚያሰራጩት ወገኖች አስታውቀዋል። አድማው የቆመው ደግሞ በሶስቱ ቀናት አድማ ከተጠበቀው በላይ ድል በመመዝገቡ ነው። የክልሉ መንግስት በበኩሉ በግድ አድማው በ29 ወረዳዎችና በአምስት የዞን ከተሞች መካሄዱን አምኖ የዜጎችን መብት ከማስጠበቅ አኳያ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል። ኦህዴድ አመራሩ በከፍተኛ ደረጃ የመከረ ሲሆን ግምገማ እንደሚኖርም ተመልክቷል።

ዜናውን አስቀደመው ያሰራጩት ክፍሎች በማህበራዊ ገጾቻቸው እንዳሉትና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ዎርክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሐመድ እንዳረጋገጡት አድማው በይፋ ቆሟል። በሶስቱ ቀናት ተመዘገበ የተባለውን ስኬትና ግብ በተሰራጨው መርጃ ተብራርቷል።

የራስን በራስ እድል መወሰን የሚለው የኦሮሞ ትግል ግቡን ሳይመታ ከትግሉ ገሸሽ ማለት እንደማይቻል ይህ የአሁኑ የአድማ ጥሪ ሁነኛ መልዕክት ማስተላለፉ፣ የሰዎችን የእለት ኑሮ በማይነካ መልኩ ኢኮኖሚው እንዲቀዛቀዝ በማድረገ ስርዓቱ እንዲኮታኮት ማድረግ፣ ፣ የኦሮሞ ህዝብ በአንድ ጊዜ መነሳት እንደሚችልና የኦሮሞን ብሄርተኛነት ሕዝባዊ መሰረት ማረጋገጡ እና እምቢተኛነቱ ወደ ተቀናጀ የድል ምዕራፍ መሸጋገሩን አመላካች መሆኑ የአድማው መሰረታዊ ድል ተብለው የተዘረዘሩ ነጥቦች ናቸው።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

በዚሁ ግምገማ መሰረት አድማው በተጀመረ በሶስተኛው ቀን የተገኘውና የታየው ውጤት በአምስተኛው ቀን ከሚጠበቀው በላይ ሆኖ መገኘቱን ይኸው በማህበራዊ ገጾች የተሰራጨው መረጃ ያስረዳል። ከዚሁም ጋር መርሃ ግብሩን መከለስ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም ተጠቁሟል። እናም የአድማው አስተባባሪ ተብለው የሚገለጹት ” ቄሮዎች ” በአስተባባሪዎቻቸው አማካይነት አድማው እንዲቆም መወሰናቸው ተመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አድማ ማድረግ፣ ሱቅ አለመክፈት፣ በንግድ ስራ አለመሳተፍ መብት ቢሆንም ሌሎችን በሃይል በማስፈራራትና በማስገደድ የተደረገ ያሉት አመጽ ወደ ነበረበት ሰላማዊ ገጽታው መመለሱን ተናግረዋል። እሳቸው እንዳሉት በሰላም መነገድና መስራት የሚፈልጉ ዜጎችን ሰላም ማስጠበቅ የመንግስት ተግባር በመሆኑ አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አመላክተዋል።

በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ያመለከቱት አቶ አዲሱ በሶስቱ ቀናት አድማ በክልሉም ሆነ በአጠቃላይ አገሪቱ ላይ የተከሰተውን ጫና አላብራሩም። ለቪኦኤ መረጃ የሰጡት አቶ አዲሱ ምን ያህል ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አላብራሩም። ይሁን እንጂ ባልተለመደ ሁኔታ የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማው የተከሰተባቸውን ቦታዎች ዝርዝረዋል።

Related stories   ይናገር ደሴ "እየተዶለተብንና እየተቀመመልን ያለው ኢትዮጵያን የመበተን ሴራ ጉዳይ ለእኛ ኢትዮጵያውያን አዲስ ነገር አይደለም"

አዲሡን የቀን ገቢ ግምት አስመልክቶም የቅሬታ ማቅረቢያ መዋቅርና አሰራር መኖሩን፣ በርካታ ቅሬታ አቅራቢዎች በዚሁ መስመር መዳኘታቸውን፣ ውሳኔ አግኝተው ግብር የከፈሉ መኖራቸውን ያብራሩት ሃላፊው ” የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን የማስፈታት አቅም የለንም” ብለዋል።

እየከረረ የመጣውና ከሌሎች ተመሳሳይ መስመር ከሚከተሉ የኦሮሞ ድርጅቶች ጋር ግናባር አልፈጥርም በሚል ከፍተኛ የአድቮኬሲ ስራ እየሰሩ የሚገኙት እነ አቶ ጃዋር ኦሮሚያ የራስዋን እድል እንድትወስን የተፈለገው ሁሉ መስዋዕትነት እንደሚከፈል በተደጋጋሚ መግለሳቸው አይዘነጋም። ይህ አስተሳሰብ በክልሉ ተወልደው ያደጉና ከሁለት ወይም ከዛ በላይ ብሄረሰብ ደም ባላቸው አብዛኞች ዘንድ ቅሬታን የሚፈጥር አስተሳሰብ እንደሆነ ተደርጎ ትችት ሲቀርበበትና እየቀረበበት ያለ ጉዳይ ነው።

አሁን ተጠርቶ ከነበረውና ቀደም ሲል ጀምሮ ሲነሳ ከነበረው አድማ ጋር በተያያዘ የሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ሚና በግልጽ አልታወቀም። ከሌሎች ህብረብሄር፣ የብሄር ድርጅቶችና ንቅናቄዎች ጋር አብረው ለመስራት በውጭ አገር የሚነቀሳቀሱ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶችም ቢሆኑ በዚህ አድማ ላይ ስላላቸው ሚና በይፋ የተባለ ነገር የለም። አቶ በያን ግን ትግሉ አገር አቀፍ መሰረት እንዲይዝ ጥሪ ሲያቀርቡ በኢሳት በኩል ተደምተዋል።

Related stories   ማዕድን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉሮሮ - "የሕዝብ ሃብት ለሚያባክኑ ዝምታ የለም" ታከለ ኡማ

ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ የአስቸኳይ አውጁ ሲነሳ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የጸጥታ ሃይሎችን አስተመሮና አስታጥቆ በክልሉ ማሰማራቱን መንግስት ቢገልጽም ይህንን አድማ ሊያስቆሙ አለመቻላቸው አሁንም በኦህዴድ መዋቅር ላይ ጥያቄ አስነስቷል። ከፍተኛ መነጋገሪያ ጉዳይም ህኗል። ዋዜማ ምንጮቹ እንደነገሩት ጠቅሶ “ኦህዴድ ይህ አድማ እንዲሳካ ተባብሯል በሚል እየተወቀሰ ነው” ሲል ማስነበቡ ሃሳቡን የሚያጠናክር ሆኗል።

በዚሁ መነሻ ኦህዴድ ድጋሚ ግምገማ ሊቀመጥ እንደሚችል የጠቆሙት ክፍሎች ” አድማው ከተጀመረ አንስቶ አመራሩ በስብሰባ ተወጥሮ መሰነበቱን፣ አሁን ድረስ ጉዳዩን ከስረ መሰረቱ ለማጥራት በሚል ከአለቆቻቸው ጋር ንግግር ላይ ናቸው” ብለዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0