የትግራይን የመሬት መልሶ ማልማት ዓለም አቀፋዊ ሽልማት ተከትሎ ኢቢሲ ያሰራጨው የዜና ማስደገፊያ ካርታ ” ምን እየተደገሰ ነው?” የሚለውን የኖረ ጥያቄ ወለል አድርጎ አሳይቶታል። ተቃውሞውን ተንተርሶ ኢቢሲ ከኢንተርኔት የተወሰደ ካርታ መሆኑንን ጠቁሞ ይቅርታ ቢጠይቅም፣ ይቅርታው ሰሚ ያገኘ አይመስልም። ዓለምነህ ሚዛን የሚደፋ ዘገባ አቅርቧል።

ከላይ በምስሉ የሚታየው ከእድሜ ጠገብ ደኖች መካክል አንዱ  ነው። በጋምቤላ ፣ በኦሮሚያ በጅማ፣ ኢሉባቡር፣ ባሌ… እድሜ ጠገብ ዛፎች ወድመዋል። በኢንቨስትመንት ስም ተቸብችበዋል። ዛሬ ድርቅ የማያውቃቸው አካባቢዎች ተራቁተዋል። ክልላቸውን የሚመሩ ድርጅቶች ይህንን ሲያዩ ሞትን በራሳቸው ማወጅ ሲገባቸው ዛሬም ህዝባቸውን ያስራሉ፤ ይገላሉ፣ ያንገላታሉ። የትግራይን ህዝብ የሚመራው ህወሃት ክልሉን ሲጠቅምና ሲያሳድግ ሌሎች የህዝባቸውን ደም ይጠጣሉ። አብረው ያጣጣሉ። ድንበር ያስቆርሳሉ፤ ህዝባቸውን የሚቆራርጥና የሚያፈራርስ ተግባር ሲፈጸም ያጨበጭባሉ።

https://youtu.be/dqhZCk27VEc

 

 

Related stories   ቆሼ ሰፈር - ልካችንን አሳየን፤ መሪዎቻችንም እኛም አላፈርንም፣ ከቆሼ ሰፈር ልጆች የተፃፈ መልዕክት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *