“Our true nationality is mankind.”H.G.

አርሰናል – መጨረሻው የማይፈታ ቀውስ ሆነ – ባለቀ ሰዓት አብዮት? ሲቲ ስተርሊንን ማባበበያ አቀረበ፤

Football pundit Phil Neville“Now it seems like a crisis, a moment in the club’s history when you think something has to change, whether that’s the manager, the board, the players…There have to be big changes.”

” በክለቡ ታሪክ ያልታየ ቀውስ ነው አሁን እየታየ ያለው ። ዌንገር፣ ቦርዱ፣ ወይም ተጨዋቾች ሊቀየሩ ይገባል ፤ ለውጥ መኖር አለበ” ፒል ኔቭል

አርሰን ዌንገር አሁን የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው። ነባር ተጫዋቾች ማጽናኛና ወቀሳ እየላኩ ነው። ለመድፈኞች ያበረከቱትን ታላቅ ታሪካና ሽግግር ገደል ሲገባ እያዩት ነው። ዋንጫ አንስቼ እሰናበታለሁ በሚል ከርሳቸው ጋር የገቡት እልህ የቀደመውን ስብዕናቸውን እየበላው ነው። ቀደም ሲል የገነቡትን መልካም ስም እያከሰሙት ነው። ዌንገር ትዳራቸውን ያፈረሰው ይኽው ” አይበቃኝም ” የሚለው እልሃቸው ነው። ” በአምላክ ላይ እምነትና ኳስ በህይወቴ ትልቅ ቦታ አላቸው” የሚሉት ዌንገር አሁን ይህንን ፈተና ማለፍ የሚችሉ አይመስልም። እናም ወደ አምልኳቸው ቢያተኩሩ የሚሻል ይመስላል

Image result for arsenal manager in anger

” ታሪክህ አጠፋኸው ፤ ለቀቅ” የሚሉ ጠንካራ አስተያየቶች በስፋት እየተስተጋቡ ነው። ” ለውጥ ፣ አንድ የሆነ ለውጥ” እንደሚያስፈልግ ተጨዋቾች ተናግረዋል። የቀድሞ ተጫዋቾችና ተንታኞች ዌንገርን ከአሰላለፍ ምርጫ ጅምሮ በከረረ የትችት ቢላዋ እየበለቱዋቸው ነው። የክለቡ ደጋፊዎች የቁጣ ድምጽ እየመረረ ነው። አሁን ያላው የአርሰናል ውጥንቅጡ የወጣና የተዘባተለ አቋም እንዴት እንደሚቀጥልም ሆነ እንዴት እንደሚቀረፍ የታወቀ ነገር የለም።

Related stories   የሲኤንኤን ዘጋቢ ኒማ- በተወነችው ተውኔት ውስጥ ዳግም ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች

በኳስ ዓለም ” ውርጅብኝ” የሚባል እውነት አለ። ይህ የሚከሰተው በአንዳንድ አጋጣሚ ያልተጠበቁ ጎሎች ይቆጠራሉ። የተመቱ ኳሶች ምክንያት እየፈለጉ ጎል ይሆናሉ። እንዲህ ያለውን አጋጣሚ መቀበል ግድ ነው። የኳስም ተፈጥሮ ነው። የአሁኑን / የሊቨር ፑልን/ ሽንፈት መቀበል ግን በማንኛውም መስፈርት የሚቻል አይሆነም። በአርሰናል በኩል የመጫወት ፍላጎትና ተጋጣሚን የመፎካከር ስሜት የለም ነበር። በማለት ፒተር ቼክ ከጫወታው በሁዋላ ተናግሯል። በመልበሻ ክፍልም የከረረ እሰጥ አገባ ነበር።

የማንችስተሩ ጋሪ ኔቭል ” ክብረ ነክ” ሲል ነው የአርሰናል ተጫዋቾችን የዘለፈው። በተለይም ሳንዜዝ፣ ቼምበርሊን፣ ራምሴ፣ ቤረሊን፣ ኦዚልን ስም ጠቅሶ ለማሊያቸው የማይጫወቱ አሳፋሪዎች ብሏቸዋል። ለአስለጣኙ ሳይሆን ለራሳቸውና ለክለቡ ክብርና መለያ እንደሚጫወቱ ያልተረዱ መሆናቸው ከሽንፈቱ በላይ አሳዛኝ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ የሰላ ትችት አውርዶባቸዋል።

ኢያን ራይትስ በመልበሻ ቤት ያለው የተጨዋቾች ይሚታየው ሁኔታ፣ የክለቡ ታክቲክ፣ የተጨዋቾች ችሎታ፣ የአሰላለፍ ምርጫ … በጥቅሉ ከዌንገር ውጭ ሆኗል ወይም ተስኗቸዋል። ሶስት የክለቡ ወሳኝ የሚባሉ ተጫዋቾች የኮንትራት ሁኔታ በወጉና በጊዜው እልባት ሳይሰጠው እዚህ ደረጃ መድረሱ የአስተዳደር ችግር ነው። አሁን የተጨዋቾች ዝውውር ጊዜ ጫፍ በመሆኑ ለማስተካከልም ጊዜ አለመኖሩን ይናገራል። ሆኖም አሁን የሚፈለገው በማንኛውም መልኩ ተመልሶ ስለመጠናከር ሲሆን ይህም ከቦርዱ እንደሚጀመር ነው።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ "ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ" – መካ አደም አሊ

Sanchez exchanged a handshake with Arsene Wenger

አሁን እየተነሳ ያለው የአርሰናል ችግር ከዌንገር ክለቡ ውስጥ ረዥም ጊዜ መቆየት ጋር ተያየዞ የተደራረበ መሆኑ ነው። አርሰናል ካለው ስምና ዝና አንጻር የያዛቸው ተጫዋቾች መካከል ክለቡን የማይመጥኑ ይበዛሉ። አንዳንዶች በቲውተር ” ይህ ሽማግሌ ለቃሚ ሰብስቦ ከለቡን ገደለው” በማለት ሲዛለፉ፤ በተመሳሳይ ዌንገር አርሰናልን ትልቅ ክለብ ማድረጋቸው የማይካድ መህኖኑን ጠቁመው ነው እዲበቃቸው የሚጠይቁት።

የአሰላለፉን ስህተት ለማሳየት ምሳሌ ያሳየው ኮዌን እየሊቨርፑሉ ማኔን ፍጥነትና አስቸጋሪነት አርሰን ዌንገር ግንዛቤ ውስጥ እንደከተቱ ይጠራጠራል። ለዚህም ነው ” ልምድ የሌለውን ተከላካይ ሆልዲንግን ለተኩላዎች አሳልፈው ሰጡት” ያለው። እሱ ብቻ አይደለም። ቼምበርሊን በቀኝ መስመር ሲመላለስ ማኔን እየተመለሰ በማገድ፣ እንዲሁም ወደፊት ጫና በማብዛት ማኔን ወደሁዋላ የመመለስ ስራ መስራት ሲገባው ራሱንም ማሊያውንም ንቆ መታየቱንም ጸሃፊው ይተቸዋል። ከሁሉም በላይ መጫወት የማይፈልገውን ሳንቼዝን ማሰለፍና ፣ ቤላሪንን በግራ መስመር አድርጎ አዲሱን ኮላሲናክ ማሰቀመጥ ከላላካዜት አለምኖር ጋር ተዳምሮ የዌንገር አብይ ስህተት አድርጎ ይወሰደዋል።

Related stories   አሜሪካ ለጊዜው ሲባል የከረመ ሃሳብ ያካተተ መግለጫ አወጣች፤ ምርጫውን በተዘዋዋሪ ደግፋለች

አርሰናል የመሃል ሜዳ መሪ አልባ ቡድን ነው። አርሰናል በተሰበረ የመሃል ሜዳ ሲዳክር አስር ዓመት ሞልቶታል። ዌንገር እንደ አንድ ልምድ ያልው አሰልጣኝ ይህንን ክፍተት ሳይሞሉ ይህን ያህል ዓመታት የመቆየታቸው ሚስጢር ለማንም ግልጽ አይደለም። ታዳጊ ተጫዋች ማሳደገና ማዘጋጀት የሚቻልበትን የጊዜ ዘመን ከቪየራ በሁዋላ መችታ መርጠዋል። አርሰናል ጉድለት ያለብትን ቦታ ሳይደፍን ጊዜ እየተበላና በሽርፍራፊ ውጤት እየተድበሰበሰ ለዚህ ታሪካዊ ቀውስ መብቃቱ አስደንጋጭ ሆኗል።

ይህ በእንዲህ እያለ ማንችስተር ሲቲ ስተርሊንግን ማባበያ በማድረግ ሳንቼዝን የጋልቸው ለማድረግ ሙከራ እያደረጉ መሆኑ ተሰምቷል። ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሃሙስ ከሚዘጋው የዝውውር መስኮት ጋር የተያዘው ግብግብ በአረሰናል ቤት ውስጥ ምን እንደሚፈጥር አልታወቀም። ይሁን እንጂ የቼምበርሊን ወደ ቼልሲ መግባት ያለቀ መሆኑና ፤ አርሰናልም የኒሱን አማካይና ተከላካይ ሊያስፈርም እንደሚችል ወሬዎች አሉ።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0