ባለፉት ሶስት አመታት በተደጋጋሚ እንዳሳሰብነዉ የጎንደር ህዝብ በአንድነት ቆሞ በዉስጥም በዉጭም ያለዉ ኢትዮጵዮያዊ ሁሉ ተባብሮ የጠላትን ሴራ ለማክሸፍ ብቃት እንዳለዉ በሙሉ ልብ አስገንዝበን ነበር። አሁንም የዛሬዉ ጽሁፋችን የሚያተኩረዉ ወያኔ መልሶ መላልሶ የሚያመጣዉን የመከፋፈል አጀንዳ አደገኛነቱን ለማሳሰብ ነዉ።
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር አዲስ አበባ ከገባ ጀምሮ አገራዊ ታሪክን የማበላሸት አባዜ የተጠናወተዉ በድርጊት ለመተግበር ያልቆፈረዉ ጉድጓድ የለም። ዳር ድንበር ቆርሶ አገር አፍርሶ የታላቋን ትጋራይ የበላይነት ለዘመናት እዉን የማድረግ ዘመቻ ህዝባችን በትግስትና አስተዋይነት የተጸነሰዉን ሤራ በኢትዮጵያዊያን ጸንቶ የኖረ ትብብር እየተመታ አብዛኛዉን ህዝብ አክሽፎታል።

Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ

በርግጥም በታሪኩና በደሙ አንድ የሆነዉ ህዝባችን ተባብሮ እያካሄደ ያለዉ የአመጽ የትግል ማዕበል የወያኔን የስልጣን መንደርተኞች እያሽበረ መሆኑን ስናይ እጅግ የሚያኮራ ነዉ። ፋሽሽቱ ቡድን ፍጹም ከማይወጣዉ አረንቋ መዘፈቁንም በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። የህዝባችን ትብብር እና ታሪካዊ ጀግንነቱ ከምንጊዜዉም በበለጠ ገሃድ እየሆነ ፤ወያኔን እያርበደበደ የሴረኛዉን እቅድ ሁሉ አሟጦ እንዳቧራ አጭሶታል ። በአሁኑ ሰዓት በብልጣብልጥነት የተገነባው ትቢት ተንዶ የህዝብ ድጋፍ ጭራሽ አቶ እቅዱ ሁሉ የማይጨበጥ ንፋስ ሁኖ የዉሸትና የዉድቀት ዲስኩር እየደሰኮረ እርቃኑን ቁሞ ይገኛል።

Related stories   “ጣልያኖችም ሆኑ እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ህዝቡን በዘር መከፋፈልን እንደ አንድ ስልት ይጠቀሙ ነበር” -አቶ ታቦር ገረሱ ዱኪ

ሙሉውን እዚህ ላይ ያንብቡ ጎንደር ህብረት መግለጫ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *