ከመቐለ ማረምያ ቤት(በኣብረሃ ደስታ)

ከሑመራና አከባቢው ተይዘው በመቐለ ማረምያቤት ታስረው የሚገኙ የወልቃይት ተወላጆች ግፍ እየተፈፀመባቸው ነው። 30 የሚሆኑ የወልቃይት ተወላጆች ተለይተው ከሰኔ 17, 2009 ዓም ጀምሮ እስካሁን ድረስ በካቴና ታስረው ይውላሉ፤ ያድራሉ። ሻወር የሚወስዱና ልብስ የሚቀይሩ በሳምንት አንዴ እሁድ ቀን ብቻ ነው። ከወልቃይት ተወላጆቹ ስድስቱ ከማረምያቤት በፀጥታ ሓይሎች ተወስደው የት እንዳሉ አይታወቅም። ልጆቹ ተረሽነው ወይም underground cell ታስረው ይሆናል ብለው ያስባሉ። ሰኔ 17, 2009 ዓም ሲወሰዱ ንብረታቸው አልያዙም። የተወሰዱት ልጆች በሙሉ የወልቃይት ተወላጆች ናቸው። በካቴና ታስረው የሚውሉና የሚያድሩም የወልቃይት ተወላጆች ብቻ ናቸው። ለምን ተለይተውበካቴና እንደታሰሩ የተነገራቸው ምክንያት የለም።

ከዚህ በላይ አድልዎና ግፍ ምን አለ? ሰዎች ተለይተው ሲታሰሩ! ምንም ጥፋት ሳያጠፋ በማረምያቤት ያለ ሰው በካቴና ማሰር ህገ ወጥ ነው።ፍትሕ ቢሮ የታለ? እምባ ጠባቂስ? የሚመለከታቸው የሰብአዊ መብት ተማጓቾችስ? ደግሞ ትግራይና ወልቃይት ለማለያየት ፅፈሃል በሉ። ህወሓት ነው የትግራይና የወልቃይት ሰው በሚል እየለያየ የወልቃይት ተወላጆችን ለይቶ በካቴና እያሰረ ያለው። ከዚህ በላይ ግፍ የለም።
ሰብአዊ መብት ይከበር። እኩልነት ይስፈን። ፍትሕ ለወልቃይት ተወላጆች! It is so!!!

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *