ሃገራዊ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሃዝ አሻቀበ

 የነሃሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ 4 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ለጣቢያችን በላከው መግለጫ፥ ወርሃዊ የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ወር ከተመዘገበው የ9 ነጥብ 4 በመቶ የዋጋ ግሽበት በአንድ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በወሩ ምግብ ነክ በሆኑ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ለግሽበቱ መጨመር ምክንያት መሆኑን ኤጀንሲው በመግለጫው አመላክቷል። በወሩ የምግብ ነክ ሸቀጦች ግሽበት 13 ነጥብ 3 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፥ ይህም ባለፈው ወር ከተመዘገበው የ12 ነጥብ 5 በመቶ አንጻር የ0 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የተመዘገበው የ7 ነጥብ 1 በመቶ ግሽበት፥ ባለፈው ወር ከተመዘገበው 5 ነጥብ 9 በመቶ ግሽበት አንጻር የ1 ነጥብ 2 በመቶ ጭማሪ ታይቶበታል ነው ያለው ኤጀንሲው። ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበትም ከአንድ አመት በኋላ ተመዝግቧል፤ ለመጨረሻ ጊዜ ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት የተዘመገበው በጥር ወር 2008 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ሃገራዊ የዋጋ ግሽበቱ 10 ነጥብ 2 በመቶ ሆኖ ነበር የተመዘገበው።

ethio_inflation.jpg

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *