ማሳሰቢያ – ስለኢትዮጵያ ድንበር መፍረስ፤ መገሰስና መጠገን በተደረጉበት ዘመናት ሁሉ የነበረች አሁንም ታፍና በመታዘብ ላይ ያለች፤ ወደፊትም የምትኖር ይህች ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤ አሁን ህዝቧ ስለሚነጋገርበት ስለ ድንበር ምን ትላለች? ቀሲስ-አስተርአየ-ጽጌየሚለውን ለመዳሰስ ይህችን ጦማር ሳዘጋጅ በውስጧ የተሸከመቻቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ አቅርቤያቸዋለሁ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘረውን አፈና ለመከላከል የጠቀስኳቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ በማቅረቤ (ግእዙን ግን ትርጉሜዋለሁ) ይቅርታ በመጠየቅ ያጎደልኩትን እየሞላችሁ፤ የተሳሳትኩትን እያረማችሁ ታነቧት ዘንድ በታላቅ ትህትና አቀረብኩላችሁ።

መግቢያ – “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ሙሉውን ፒዲኤፍ እዚህ ላይ ያንብቡ ድንበር-ሲፈርስ፤-መሐሉ-ዳር-ይሆናል

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *