ባሰሜን ጎንደር 30 የሚሆኑ ሽፍቶች ብቻ ጫካ ውስጥ እንዳሉና በ2010 መስከረም ውር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ እቀድ መያዙ ተሰማ። ዜናው ጫካ ያሉትን ቁጥር ለይቶ፣ የሚደመሰሱበትን ቀን የቀረበ ሲሆን ” ሽፍታ” በሚባሉት ወገኖች ያደረሱትን ጉዳት አላካተተም። መረጃውን የሰጡት ሃላፊ ተገደሉ ያሉትን፣ የተያዙትንና የተማረከ መሳሪያ ሲዘረዝሩ ከራሳቸው ወገን የደረሰውን ኪሳራ በዝምታ ማለፋቸው የዜናው ሌላ ዜና ሆኗል።

ሃላፊው ይህንን ቢሉም፣ በአማራና በብአዴን መካከል ያለው ግንኙነት ሊታረቅ የማይችል መሆኑ በተደጋጋሚ በተለያዩ መድረኮች እየተገለጸ ነው። ያለመታረቃቸው ብቻ ሳይሆን “እመራዋለሁ” የሚለውን ሕዝብ ጥቅምና ማንነት አሳለፎ የሚሰጥ የዘመኑ ” ይሁዳ” ሲሉ ይፈርጁታል። በየፊናው አማራውን ወክለነዋል የሚሉት ክፍሎች የቀን ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ብአዴንም ሆነ ኢህአዴግ ከአማራው ህዝብ ጋር ያላቸው ውል እንደተበጠሰ አበከረው ይናገራሉ። በህዝቡ ዘንድ ያለው ስሜት ይህ ሆኖ ሳለ 597 ታጣቂዎች በያዝነው ዓመት መገደላቸውን ክልሉ ይፋ አርጓል።

ከአማራ ክልል ተለይቶ የጎንደርና የጎጃም የተለያዩ ክፍሎች የጥቃቱ ሰለባ እንደሆኑ ነው ዜና የሚያስረዳው። ሪፖርተር የጠቀሳቸው የሰሜን ጎንደር ዞን የጸጥታ ሃላፊ የተጠቀሰውን ያህል ታጣቂዎች መገደላቸውን ሲያስታውቁ ከእነሱ ወገን ስለተገደሉትም ሆነ ሰለደረሰው ቀውስ  ያሉት ነገር የለም። በተለያዩ ወቅቶች እስር ቤት መሰበሩን፣ በጦር ተሽከርካሪዎች ላይ ተሳፍረው በሚሄዱ የሰራዊቱ ክፍሎች ላይ አደጋ መጣሉ፤ የአስተዳደር ቢሮዎች ላይ እርምጃ ስለመወሰዱ፣ በተለያዩ አውዶች ስለተገደሉ የመንግስት ታጣቂዎች ወይም የመከላከያ ሰራዊት፣ ከድተው ወደ ኤርትራ ስለገቡ የመከላከያ ሰራዊት እና በተመሳሳይ በገዢው ፓርቲ ላይ ደርሷል ተብሎ ስለተዘገበው ዘገባ ሃላፊው አልተጠየቁም፤

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

ከጎንደርና ከባህርዳር በተለይ የሚወጡት መረጃዎች ሕዝቡ ማምረሩን ነው። በየጊዜው የሚታሰሩትን ጨምሮና በራሱ በብአዴን ውስጥ ያለው ድርጅታዊ መላላት የክልሉን ሰላም ስጋት ላይ የጣለ መሆኑንን ነው። ይኁን እንጂ ሃላፊው ለሪፖርተር እንደተናገሩት ከተያዙትና ከተገደሉት ውጪ በድመሩ 30 ሽፍቶች ብቻ እነደቀሩ፣ እነሱም በቅርቡ እንደሚደመሰሱ ወይም በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ሃላፊው ቃል ገብተዋል። የሪፖርተር ዘገባ እንዲህ ይነበባል።

  • ከ700 በላይ ደግሞ ትጥቅ መፍታታቸው ተገልጿል

በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ዞን በ2009 ዓ.ም. ጫካ ገብተው ከነበሩ የታጠቁ ኃይሎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 597 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡

የዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ መምርያ ኃላፊ አቶ ዳኘው በለጠ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኤርትራ በመሄድ ከግንቦት ሰባትና አርበኞች ግንባር ጋር ተቀላቅለው በመሠልጠን በዞኑ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ እንግልት ሲያደርሱና ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩ በአጠቃላይ 708 ታጣቂዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከልም 111 በሕይወት መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በአሁኑ ወቅት የዞኑ ፀጥታ በአንፃራዊነት ጥሩ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የመምርያው ኃላፊ፣ የሻዕቢያ መንግሥት እነዚህን ኃይሎች በገንዘብና በሎጂስቲክስ እገዛ ያደርግላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ‹‹እነዚህ የታጠቁ ኃይሎች በሕዝቡ ውስጥ ሰፊ የሆነ ግፍ ሲፈጽሙ የነበሩና ሕፃናትንና ከብቶችን በመዝረፍ ሰቆቃ ሲያደርሱ የነበሩ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡

አሁንም ቢሆን ከኤርትራ ሠልጥነው የመጡና በየቦታው እየተንቀሳቀሱ በሕዝቡና በመንግሥት ንብረት ላይ ጉዳት ለማድረስ ያለሙ ሰባት ግለሰቦች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ በቀላል ወንጀል የታሰሩና ሰው ገድለው የሸሹ 23 ያህል ሽፍቶች በዞኑ ውስጥ ባሉ ጫካዎችና በሱዳን ድንበር አካባቢ እንዳሉም አስረድተዋል፡፡ የዞኑ የፀጥታ ኃይልና አስተዳደር በ2010 ዓ.ም. መስከረም ወር እነዚህን ኃይሎች ለማጥፋት አቅዶ እየሠራ እንደሆነም አቶ ዳኘው ተናግረዋል፡፡ እስካሁን በተደረገው ዘመቻም ከ500 በላይ የጦር መሣሪያዎች መማረክ ተችሏል ብለዋል፡፡

በሰሜን ዞን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቅማንት ሕዝብ አንስቶት የነበረውን የማንነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል በ12 ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በጭልጋ ወረዳ ያሉ አራት ቀበሌዎች በሕዝበ ውሳኔው ላይ ቅሬታ ማንሳታቸውን አቶ ዳኘው ገልጸዋል፡፡ እንደ አቶ ዳኘው ገለጻ፣ ጭልጋ ወረዳ ሕዝበ ውሳኔው ከሚካሄድባቸው 12 ቀበሌዎች መካከል ስድስቱ የሚገኙበት ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አራቱ ማለትም ገለድባ፣ አንከራደዛ፣ ሹምየና አውርደርዳ ቀበሌዎች ውስጥ ከነዋሪዎች ቅሬታ ቀርቧል፡፡

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

በእነዚህ ቀበሌዎች የሚኖረው ሕዝብ ዋነኛ ጥያቄም፣ ‹‹ቅማንቶች ከ20 በመቶ በታች ሆነውና በቁጥር ደረጃ እኛ አማራዎች በልጠን ሳለ ሕዝበ ውሳኔው ለምን አስፈለገ የሚል ነው፤›› ብለዋል፡፡

መንግሥት ለቅሬታው በሰጠው ምላሽ እንደተባለው የአማራዎች ቁጥር የሚበልጥ ከሆነ በድምፅ መስጠት ሒደት የሚረጋገጥ እንደሚሆን፣ መጭበርበር እንዳይኖር ተብሎም ታዛቢዎች የሚመጡት ከሌላ ክልል እንደሆነም እንደተገለጸ ጠቅሰዋል፡፡ እንደ አቶ ዳኘው ማብራርያ፣ ሕዝበ ውሳኔ ከሚካሄድባቸው 12 ቀበሌዎች መካከል ሁለቱ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሲገኙ፣ አራቱ ደግሞ መተማ ውስጥ የሚገኙ ቀበሌዎች ናቸው፡፡

የቅማንትና የአማራ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ከተነሳባቸው መካከል በ12 ቀበሌዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔውን መስከረም 7 ቀን 2009 ዓ.ም. ለማድረግ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *