ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ03/01/2017 ይህንን ጽፎ ነበር። በእርግጥ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል የት ገባ? ምን ሆነ? የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል እንዲህ ሲፈነጭ፣ ኦሮሚያ ምን ነካው? እንዴትስ ህዝቡን መከላከል አቃተው?

“ግጭቱ የህዝብ ለህዝብ አልያም የመንግስት ለመንግስት አይደለም፤ ከግላቸው ጥገኛ ፍላጎት በመነሳት ግጭቱን የሚያነሳሱ፣ በግጭቱ የሚሳተፉ የመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ በግጭት ሂደት ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ አካላት እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል”  የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ።  ለፋና ከተናገሩት፤

oromiya-police
ዛጎል ዜና- ህወሃት ያቋቋመው ኦህዴድ በራሱ ክልል፣ ራሱ የሚያስተዳድረው ስልሳ ሺህ ሰራዊት ገንብቶ እንደነበር የሚናገሩት አንድ ስርዓቱን የተለዩ የቀድሞ ባለስልጣን ናቸው። እኚህ ባለስልጣን እንደሚሉት ይህ ሃይል የተገነባው በአቶ ጁነዲን የስልጣን ዘመን በጀነራል ከማል ገልቾ አመራር ነበር።
የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በፌደራል ፖሊስ ቅርጽ የተደራጀና ክልሉን ሙሉ በሙሉ የመከላከል አቅም ነበረው። በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከመቀጣጠሉ በፊት ይህ ሃይል ማንኛውንም ችግርና የድንበር ውዝግብ ያለ አንዳች የፌደራሉ ሃይል እገዛ ማስታገስና ማስቆምና አይከብደውም ነበር። በተለይም ከሶማሌ ክልል ጋር ያለውን የተለመደ የድንበርና የግጦሽ መሬት ውዝግብ መቆጣጠር ለኦሮሚያ ልዩ ሃይል ትልቅ የቤት ስራ ሆኖ እንደማያውቅ ለስራው ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። Image result for oromia police
ታዲያ ይህ ሃይል እያለ ከሶማሌ ክልል የነሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ይህንን ያህል የከፋና የተደጋገመ ጥቃት እንዴት ሊያደረሱ ቻሉ? አዲሱ የክልሉ ካቢኔ እንዳለው በሁለቱ ክልሎች አጎራባች ቀበሌዎችና ድንበሮች ላይ የሚካሄደው ጥቃት በክልሉ ባለስልጣናት መመሪያ የሚሰጥበት እንደሆነ እስከመግልጽ ደርሰዋል። በይፋ መግለጫም አውጥተዋል።
የተለያዩ መገናኛዎች የኦሮሚያን ባለስልጣናት ጠቅሰው እንደሚሉት ከሆነ በአንድ አካባቢ ብቻ ከሰላሳ በላይ ሰዎች ሞተዋል። ንብረት ወድሟል። በቀላሉ ሊገመት የማይችል ኪሳራ ደርሷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ የሚመሩት ኦህዴድ የሚመራውን ክልል ህዝብ እንዴት ከጥቃት መከላከል አቃተው? ጥቃቱ እየተደራረበ መሆኑና ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ እንዳስታወቁት በአካባቢው በሰላም መቶ መግባት አስጊ ደራጃ መድረሱ ሲጠቁሙ ኦህዴድ ምን እየሰራ ነው?
የቀደሞ ባለስልጣን እንደሚሉት ትልቁ ችግር የተፈጠረው በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ዓመጽ ተከትሎ የክልሉ ልዩ ሃይል ሙሉ በሙሉ በኮማንድ ፓስቱ እዝ ስር መውደቁ፣ ይህንኑ ተከትሎ ክልሉ ከጸትታና ከወታደራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መመሪያ የመስጥት ስልጣኑ ስለሌለው ነው።
በኦሮሚያ ተቀጣጥሎ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ ልዩ ሃይልና ፖሊስ በይፋ ለተቃውሞው ድጋፍ እንደሰጠ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ እንደነበር የሚታወስ ነው። በዚሁም ይሁን በሌላ ኦሮሚያ የገናባችው 60 ሺህ የልዩ ሃይል በኮማንድ ፓስት እዝ ስር መውደቁ ከሶማሌ ክልል በሚነሱ ሃይሎች የሚሰነዘረውን ተደጋጋሚ ጥቃት ክልሉ ሊያስቆም አለመቻሉ መነጋገሪያ ሆኗል። የኮማንድ ፖስቱም ቢሆን በራሱ የእዝ እርከን ይህንን ተደጋጋሚ ግጭት መላ ሊለው አለመቻሉ ግርታን ፈጥሯል።
አዋራማ ሪንጀር የሚለብሱት የኦሮሚያ ልዩ ሃይል በእርግጥም 60 ሺህ ያህል ሰራዊት እንዳለው አሁን በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉ የኦህዴድ ሰዎችም ያምናሉ። ዛጎል ያናገራቸውና ለጊዜው ስማቸው እንዳይተቀስ የጠየቁ ዲፕሎማት ይህ ሃይል በኮማንድ ፖስት የእዝ ሰንሰለት ውስጥ እንደገባ ይናገራሉ። እኚሁ ዲፕሎማት እንደሚሉት ወደፊትም ቢሆን ክልሎች የራሳቸውን ሃይል የመገናብታቸው ጉዳይ በዚሁ ሊያከትምለት እንደሚችል ግምታቸውን ሰጥተዋል።………
የጀርመን ሬድዮ በ28.02.17 ዘገባው የሚከተለውን አስነብቧል።
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን የሚያዋስኑ የኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች ከታህሳስ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ አለመረጋጋት ዉስጥ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል። «ልዩ ፖሊስ» በመባል የሚጠራዉና የሶማሌ ክልል ታጣቂ ኃይል መሆኑ የሚነገረዉ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙት 14 አዋሳኝ ወረዳዎች ዉስጥ ሰርጎ በመግባት በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እየፈጸመ እንደሚገኝ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከዚሁ ከሶማሌ ክልል ተነሱ የሚባሉት «የታጠቁ ኃይሎች» በእነዚህ ወረዳዎች የሚፈፅሙት ጥቃት ምን ዓላማ አንግቦ ነዉ? ለሚለው ጥያቄ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፍ የሆኑት አቶ አዲሱ አራጋ ”ይህ ጥቃት የወሰንና የንብረት ዓላማ ያለው ነው” ባይ ናቸው።
በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ቁምቢ ወረዳ ጥቃቱ እንደተጀመረና ከዛም በኋላ ወደ ጭናግሳን፣ ምዳጋ ቶላ፣ ጉርሱም፣ ማዩ ሙሉቄና ባቢሌ ወረዳዎች መስፋፋቱን አቶ አዲሱ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። በዚህ ጥቃት በሰዎች ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አቶ አዲሱ አስረድተዋል። “ለጊዜዉ ግን ምን ያህል ሰዉ እንደተጎዳ በቁጥር መረጃ የለኝም” ብለዋል።
ሰሞኑን በጉርሱም ወረዳ ግጭቱ መባባሱን የአከባቢዉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የጭናግሳን ወረዳ ነዋሪ የሆኑና ስማቸዉ ለግዜዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ ግለሰብ፣ ወረዳቸዉ ከጉርሱም ወረዳ ጋር እንደሚዋሰንና በሁለቱም ወረዳዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች “በጣም አሳሳቢ” ሲሉ ነው የገለጹት። ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በሁለቱም ወረዳዎች የመከላከያ ሰራዊት ሰፍሮ እንዳደሚገኝ የገለፁት እኚህ ነዋሪ “በየእለቱ ሰዉ ሳይሞት የቀረበት ቀን የለም” ሲሉም ያክላሉ።
” ወጥቶ መግባት አሁን አሰፈሪ ሆኗል። ተማሪዎችም ሆኑ አስተማሪዎች ለነፍሳቸዉ ስለሚፈሩ ብዙ ትምህርት ቤቶች የማስተማር ስራ አቁመዋል። ግጭቱ ከተባባሰ ከአንድ ወር ወዲህ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአከባብዉ ነዋሪዎች በዚህ ግጭት ህይወታቸዉን አጥተዋል”
“ለዚህ አሳሳቢ ግጭት መፍቴ ለመስጠት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ሆነ በእትዮጵያ ሶማሌ ክልል በኩል የተሰራ ስራ አለየሁም” የሚሉት የጭናግሳን ወረደ ነዋሪ፣ ” ጉዳዩ ኮማንድ ፖስትን ይመለከታል መባሉን ሰምቻለሁ” ብለዋል። አቶ አዲሱ ግን የክልል መንግስታት ሆኑ የፊደራል መንግስት ለዚህ ጉዳይ መፍቴ ለማምጣት ስምምነት አድርገዉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ብለዋል።

Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

Related image
ልዩ ፖሊስ የተሰኙት በሶማሌ ክልላዊ መንግስት እዉቅና እንደሚንቀሳቀሱና የክሉልም መንግስት ለዚህ ጥቃት ተጠያቂ መሆን አለበት ሲሉም ቅሬታቸዉን የሚያሰሙ አሉ። አቶ አዲሱ ይህን እንዴት ይመለከቱታል?
ይህ ግጭት በምዕራብ ሃራርጌ ዞን ቦርዶዴ ወረዳ፥ በባሌ ዞን ደግሞ በዳዌ ሰረር፣ በሳዌና፣ በማዳ ዋላቡና ራይቱ ወረዳዎች፥ በጉጅ ዞን ጉሚ፣ ኤሌሎና ሊዮን ወረዳዎች፥ እንዲሁም በቦራና ዞን ሞያሌ ወረዳ ዉስጥም እንደምታይ አቶ አዲሱ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት በኩል ማብራርያ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሰካም።
የጀርመን ድምጽ እንዳለው የሶማሌ ክልል ሃላፊዎች በዚህ ጉዳይ መልስ ለመስጠት ከተለያዩ መግናኛዎች ለሚቀርብላቸው ጥያቄዎች በአድራሻቸው አይገኙም። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በብሄር ብሄረሰቦች በአል ላይ ባደረጉት ንግግር ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም መመሪያ መስጥታቸውን ፋና የዘገበው ከወር በፊት ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *