“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኢህአዴግ ትጥቅ አስፈታለሁ ፤ ሚዲያዎችን ጨምሮ በግጭቱ እጃቸው ያለበት ሁሉ ይጠየቃሉ አለ፤ ይህ ሁሉ ቀውስ እስኪፈጠር የት እንደነበረ አላስታወቀም

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ላይ የደረሰውን ዘርን መሰረት ያደረገ ግጭት በአስር ሺህ የሚቆጠሩትን ካፈናቀለና በመቶዎች የሚቆጠሩትን ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ድምጽ አሰሙ። ግጭቶች በተነሱባቸው አካባቢዎች የተሽከርካሪ መንገዶች በፌደራል ሃይል ቁጥጥር ስር እንዲውሉና ትጥቅ የማስፈታት እንዲሁም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ባላቸው ማናቸውም አካላት ላይ ማናቸውም ዓይነት እምጃ እንደሚወሰድ ዛቱ። ዛቻው ሚዲያዎችንም ያካትታል።

ፋና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠቅሶ እንዳለው በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ አገር ሽማግሌዎችን፣ የሐይማኖት አባቶችንና አባ ገዳዎችን እንዲሁም የሁለትን ክልሎች ርዕሰ መስተዳደርችን ጋር ንግግር ተደርጓል።

ይህ ሁሉ እልቂት ሲደርስ ኢህአዴግ መረጃ እያለው ለምን ዝምታን እንደመረጠ ስለመጠየቃቸውም ይሁን ስለመናገራቸው በዜናው አልተካተተም። ይህ አሳዛኝ እልቂት በድፍን አገሪቱ መደናገጥን የፈጠረ፣ እምነትን ያሳጣና ዜጎች ዋስትና እንዳይሰማቸው ያደረገ  በመሆኑ ኢህአዴግ ለዚህ ሁሉ በቂ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባ ዜጎች እምነታቸውን ሲያስተጋቡ ነበር የሰነበቱት። በዚሁ መነሻ አቶ ሃይለማሪያም ይህንን ጉዳይ ሳያነሱ አልፈውታል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ፊት ዜጎች መቀጥቀጣቸውንና ፣ ” በፍቃዳችን ነው ክልሉን የለቀቅነው በሉ” ተብለው ሲገረፉ የመከላከያ ሰራዊት ቆሞ ያይ እንደነበር፣ በአወዳይ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲሰየፉ የክልሉ ታጣቂዎች ይመለከቱ እንደነበር ጠቅሰው ሰለባዎች ምስክርነት ሲሰጡ እንደነበር ያዳመጡ ወገኖች ” ኢህአዴግ ማን ላይ ነው እርምጃ የሚወስደው? ማንን ከማን ለይቶ ሊቀጣ ነው? ማን ማንን ሊቀጣ አቅም አለው?” የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ አድርጓቸዋል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

አቶ ሃይለ ማርያም ሚዲያዎች ላይም ዝተዋል። በአገር ውስጥ ባሉት ይሁኑ በየትኞቹ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ባይዘረዝሩም በጥቅሉ ቀውሱን በሚያራገቡና ህዝብ ከህዝብ ጋር እንዲጋጭ በሚሰሩት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቀዋል። አንዳንድ ገለልተኛ ወገኖች እንደሚሉት አሁን ብቻ ሳይሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሚዲያዎች ፈር ለቀዋል። በተለይም በማህበራዊ ገጾች የሚሰራጩ የቀጥታ ንግግሮችና እጅግ የወረዱና ለጆሮ የሚቀፉ “ብሄር ተኮር” ዘለፋዎች የሚስተናገዱባቸው ሆነዋል።

ከዚሁ ሁሉም የሚዲያ ባለቤት ከሆነበት የማህበራዊ አውድ ታስቦበትም ይሁን በድንገት ኢህአዴግ የከፈተው  የጥላቻው ዘር በደንብ ተራግቧል። ህሊናና ልብን በሚያደማ መልኩ የክፋት ዘር መዝራት ብቻ ሳይሆነ የተዘራውንም የሚኮተኩቱ የአረም እርሻዎች ቀላለ ቁጥር የላቸውም። አቶ ሃይለማሪያም የትኞቹን እንደሆነ ባይገልጹም በደፈናው ዝተዋል። ይህ ሁሉ ከሚሆን የችገሩን ዋና ምንጭ የዘር ፖለቲካ እንዴት ማምከን እንደሚቻል እንደ መሪም ሆነ እንደ ኢህአዴግ ፍንጭ አልሰጡም። በርካቶች አሁን እየተጋጋመና ፍሬው የበሰለውን የአቶ መለስ እርሻ ማምከን የሚቻለው ፖለቲካዊ መፍትሄ በመፈለግና እርቀን በአገሪቱ በማውጅ ብቻ ነው።

Related stories   ቻይና በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት የሚካሄደውን የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር እንደምትደግፍ ገለጸች

የፋና ዜና እንዲህ ይነበባል

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም በክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንዲቆም መንግሥት ሕገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ገለፁ

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም በክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት እንዲቆም መንግሥት ሕገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ ገለፁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ አገር ሽማግሌዎችን፣ የሐይማኖት አባቶችንና አባ ገዳዎችን እንዲሁም የሁለትን ክልሎች ርዕሰ መስተዳደርችን አነጋገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግጭቱ ሳቢያ የሰው ህይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን የገለጹ ሲሆን፥ ግጭቱ በአስቿይ እንዲቆም የፌዴራል መንግሥት ሕገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ አፋጣኝ እርምጃዎችን ይወስዳል ብለዋል።
የሐይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ሰላም የማስፋኑ ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ያደረጉት።

በዚህ መሠረት የአካባቢዎቹን ሰላምና ፀጥታ ወደነበረበት ለመመለስ በሁለቱ ክልሎች የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች በፌደራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ክትትል ሥር እንዲሆኑ፣ የፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች የሕዝቡን ሰላም የመጠበቅና የማረጋጋት ሥራ እንዲሰሩም፣ አካል በማጉደልና የሰው ሕይወት በማጥፋት የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር እንዲያውሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያመ አዘዋል።

Related stories   መካከለኛዉ ምሥራቅ ሌላ ዘመን ሌላ ጥፋት

ግጭቱ በተከሰተባቸው ድንበር አካባቢዎችና የግጭቱ ቀጠናዎች የፌዴራል መንግሥት ማንኛውንም የጦር መሣሪያ ወይም ትጥቅ የሚያስፈታ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሁለቱ ክልሎች መካከል የሰብዓዊ መብት በመጣስ የሰው ሕይወት ያጠፋ የፀጥታ ኃይልም ሆነ ማንኛውም አካል በሕግ አግባብ እርምጃ እንዲወሰድበት እንደሚደረግም አስታውቀዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

“የዜጎች ሠላም የማይዋጥላቸው ፀረ-ሠላም ኃይሎች ችግሩ ወደ ከፋ ሁኔታ እንዲሄድ በማድረጋቸው መንግሥት በሚያደርገው የማጣራት ሥራ ሁሉም ዜጋ ከመንግሥት ጎን በመቆም ትብብር ሊያደርግ ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሕዝቡን የሚያጋጭ መግለጫ በመስጠት ብጥብጡን በሚያባብሱና ከዚህ እኩይ ተግባራቸው በማይታቀቡት ላይ “መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል” ብለዋል።

ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰብአዊ መበት ጥሰትን እንደሚያጣራም ነው ያስታወቁት።

በሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ግጭት የሚያባብሱ የመገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ይህ የማይሆን ከሆነ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም አሳስበዋል።

በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ የትኛውም ግለሰብና የፀጥታ ኃይልም ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0