Skip to content

ለገቢ ንግድ የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ አስመጪዎች እጅ ለማላቀቅ 215 የክልል አስመጪዎች ተመለመሉ

via – reporter amharic – ለገቢ ንግድ የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ አስመጪዎች እጅ ለማላቀቅ 215 የክልል አስመጪዎች ተመለመሉ

መንግሥት ለገቢ ንግድ በየዓመቱ የሚፈቅደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ የአዲስ አበባ አስመጪዎች እጅ ውስጥ ለማስለቀቅ፣ 215 የክልል አስመጪዎችን መመልመሉ ተሰማ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት አስመጪዎቹ የተመለመሉት ከመቐለ፣ ከባህር ዳር፣ ከጅማና ከሐዋሳ ከተሞች ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የአስመጪነት ንግድ በተወሰኑ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ውስጥ በመውደቁና ይህም የጎንዮሽ የዋጋ አሻጥር መፍጠር እንዲችሉ እንዳደረጋቸው፣ የአገሪቱን ውስን የውጭ ምንዛሪም በብቸኝነት እንዲቀራመቱ እንዳስቻላቸው የንግድ ሚኒስቴር የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍና አዲስ አበባ ላይ የተወሰነውን የአስመጪነት ንግድ ለመበተን ሲባል፣ ከተመረጡ የክልል ከተሞች ባለሀብቶችን በመመልመልና በማሠልጠን መንግሥት በ2010 ዓ.ም. ወደ ትግበራ እንደሚገባ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ባለሀብቶችን ለመምረጥ የንግድ ሚኒስቴር የተለያዩ መሥፈርቶችን የተጠቀመ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ዋነኞቹ በሕገወጥ ንግድ ያልተሳተፈና ካፒታሉ ተዓማኒነት ያለው የሚሉ ናቸው፡፡

ለሙከራ ትግበራው ከተመለመሉት 215 ባለሀብቶች ውስጥ የተመረጡት ከተሞች እያንዳንዳቸው 15 ባለሀብቶችን እንዲወክሉ መደረጉንም ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከብሔራዊ ባንክ ጋር ንግግር እየተደረገ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ በክልሎች ቅርንጫፍ የሌለው በመሆኑ ውክልና ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስጠት በሚቻልበት ወይም ሌላ አማራጮችን ለማየት ንግግር እየተደረገ መሆኑንም ምንጮች አክለዋል፡፡

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Copyright - zaggolenews. All rights reserved.

0Shares
0
Read previous post:
የቤቶች ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተከሰሱ

Via reporter Amharic - የቤቶች ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተከሰሱ   በሁለቱ ተቋማት ከ74.9 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት...

Close