“Our true nationality is mankind.”H.G.

ቅዱስ ሲኖዶስ የምትሉት አካል እኮ ቅድስተ ማርያም ግቢ ውስጥ የለም!

Image result for አቦይ ማትያስአቦይ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳን በአሌፍ ቴሌቪዥን (ምርዓየ ኩነት) የሚያስተላልፈውን መርሐ ግብር ሥርጭት ከቅዱስ ሲኖዶስ ነኝ ከሚለው አካል ዕውቅና ስምምነትና ይሁንታ ውጭ ገና ከመጀመሩ ያለ አንዳች ሊያሳግድ የሚችል ሕጋዊ ምክንያት እንዲታገድ አደረጉ፡፡ ይታያቹህ! በገዛ ገንዘቡ ለሚያስተላልፈው ስርጭት ነው እኮ! ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን በከፈተችው የቴሌቪዥን (የምርዓየ ኩነት) መርሐ ግብር ስርጭት መጠቀም ሲኖርበት “አይሆንም!” ተብሎ ተከልክሎ ነው ወደ ግል ጣቢያዎች ፊቱን ለማዞር የተገደደው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ነኝ የሚል አካል ቅድስተ ማርያም ግቢ ውስጥ ቢኖር ኖሮ ከቤተክርስቲያን የውሳኔ አሰጣጥ ሕግና ሥርዓት ውጭ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ነኝ ባዩ አካል ፈቃድ ስምምነትና ይሁንታ ቀደም ሲል አቦይ ጳውሎስ አሁን ደግሞ አቦይ ማትያስ የቅድስት ቤተክርስቲያንን ጥቅም የሚጎዳና የሚጻረር ውሳኔና ትዕዛዝ እያስተላለፉ ሲያስፈጽሙ ጸጥ ብሎ ያይ ነበረ ወይ???

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ቤተክርስቲያን እንዲህ ዓይነት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጭ ቤተክርስቲያንን የግል ንብረቱ አድርጎ እንዳሻው የሚፋንን የአላውያንና የመናፍቃን ቅጥረኛ ወንበዴ በሚያጋጥም ጊዜ የመጨረሻውን ሥልጣን የያዘው ቅዱስ ሲኖዶስ ግለሰቡን ሥርዓት የሚያስይዝበትን ካልሆነም ደግሞ የሚያስወግድበትን ሕግ ሥርዓትና ቀኖና ሠርታ አስቀምጣ ነበረ፡፡

የመጨረሻው የሥልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ነኝ የሚለው አካል ግን ለተጣለበት አምላካዊ ኃላፊነትና አደራ ታማኝ ሆኖ ይሄንን ሥልጣኑን ባለመጠቀሙና ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕግ ሥርዓት ቀኖናዋ ተሽሮባታል፣ አስተምህሮዋ ተቆነጻጽሎባታል፣ መንጋዋ በገፍ ተበልቶባታል፣ ጥቅሞቿን እንድታጣና እጅግ እንድትጎዳ ተደርጋለች ወዘተረፈ.

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

በመሆኑም ለዚህ ሁሉ የቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳት፣ ኪሳራ፣ ሕማም፣ ስቃይ፣ ስብራትና ሰቆቃ ዋነኛ ተጠያቂው ሲኖዶስ ነኝ በሚለው የጳጳሳት ቡድን ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ምንደኛ፣ አስመሳይ፣ አድርባይና ሥጋዊነት የሠለጠነባቸው አደራ በላዎች ጳጳሳት ነን ባይ ግለሰቦች ናቸው!!!

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ!” ሐዋ. 20፥28 ተብለው ነበረ ምን ዋጋ አለው እነሱ ግን ከእግዚአብሔር ይልቅ ወያኔና ሥጋዊ ጥቅም በለጠባቸው እንጅ፡፡

Related stories   አሳሳቢው የእስራኤልና ፍልስጤም ግጭት

ድልና ትንሣኤ ለቅድስት ቤተክርስቲያንና ለቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ!!! ውድቀትና ሽንፈት ለአጋንንቱ መንጋ ለወያኔ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0