“Our true nationality is mankind.”H.G.

ህወሃት የግጨውን ስምምነት አደነቀ፣ በሶማሊና በኦሮሚያ ለደረሰው ሰባዊ ቀውስ ሃዘኑን ገለጸ፣ መልኩን እየቀያየረየሚነሳውን ችግር ለመታገል ወሰነ

የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ሲያጠናቅቅ በወጣው መግለጫ ግጨውን ማዕከል አድርጎ በጸገዴና በጠገኔ የተደረሰውን ስምምነት አደነቀ። ስምምነቱ የሁለቱን ህዝብ ትሥር በሚያጠናክር መልኩ የተከናወነ እንደሆነ አመልክቷል። በሌላ በኩልም በሶማሊና በኦሮሚያ መካከል በተፈጠረ ግጭት በደረሰው አገጋ ከልብ ማዘኑን አመልክቷል።

ግንባሩ መልኩን በመቀያየር እየተከሰተ ያለውን የትምክህት እና ጥበት አደጋ ለመመከትም፥ ህወሃት ከእህት ድርጅቶቹ ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ ማዕከላዊ ኮሚቴው አስታውቋል። በመግለጫው ባይገለጽም ትምክህተኛ የሚባሉት የአማራ ክልል ተቀናቃኞች ሲሆኑ፣ ጠባብ የሚባሉት ህወሃትን የማይደገፉ የኦሮሞ ክልል ተወላጆችን መሆኑ ከልምድ የሚታወቅ ነው። መግለጫው እንዲህ ይነበባል።

Related stories   ኤፒ ለቅጥፈቱ ይቅርታ አልጠየቀም – ምርጫ ተራዘመ፤ለምን?

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ባለፈው አመት በተጀመረው የጥልቅ ተሀድሶ ግምገማ በህዝብ ተደግፎ ውጤት እያሳየ መሆኑን የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ገለጸ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 28 ቀን ያካሄደውን ስብሰባ አጠናቋል። በቆይታውም በ2009 ዓ.ም የነበረውን የመንግስትና የድርጅቱን የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።
ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አስተዳደር ለማስፈን በተካሄደው ጥልቅ ተሀድሶ ህዝቡ ያሳየው ተሳትፎና ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማዕከላዊ ኮሚቴው አሳስቧል። በአማራ እና ትግራይ ክልል ፀገዴ እና ጠገዴ አካባቢ ግጨውን ማዕከል አድርጎ የተከሰተው ግጭት የሁለቱን ክልል ህዝቦች ትስስር በሚያጠናክር መልኩ መፈታቱን ማዕከላዊ ኮሚቴው አድንቋል።
በኦሮሚያ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት፥ በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ህውሃት፣ የክልሉ መንግስት እና ህዝቡ የተሰማቸውን ሀዘንም ገልጸዋል ብሏል በመግለጫው። ማዕከላዊ ኮሚቴው ችግሩን ከሌሎች እህት ድርጅቶች ጋር በመሆን፥ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን እንደሚወጣም ጠቁሟል። ህገ መንግስታዊ የፌደራል ስርዓቱን ለማፍረስ መልኩን እየቀያየረ እየተከሰተ ያለውን የትምክህት እና ጥበት አደጋ ለመመከትም፥ ህወሃት ከእህት ድርጅቶቹ ጋር ተባብሮ ይሰራልም ብሏል ኮሚቴው።

0Shares
0