የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ / ህወሃት ሲያካሂድ ቆይቶ አጠናከኩት ባለው ጉባኤ ወጣቶች ደስተኛ አለመሆናቸውን፣ ድርጀቱ ሕዝባዊ ድጋፉን ማጣቱንና “በውስጣችን ያለው የዛገ ነገር መቀየር አለበት” ቢሉም ምንም የተለወጠ ነገር እንደሌላቸው ተዘገበ። ለራሳቸው መቀመጫ እንጂ ለሕዝብና ለአገሪቱ እንደማያስቡና አሁን ያለውን የፖለቲካ ቀውስ የሳቱ እንደሆኑም ተዘገበ፤ በቀጣይ ህወሃት የመሪነት ሚናውን በኦህዴድ ሊነጠቅ እንደሚችልም ግምት ተሰጠ።
ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አነጋግሮ እንደዘገበው፣ ህወሓት አገራዊ ሚናውንም እየተወጣ አይደለም የሚለው ፤ የመሪነት ቁመናውን በሌሎች ምናልባትም በኦህዴድ ሊወሰድ ይችላል። አብዛኞቹ ተናጋሪዎች እንዳሉት ወጣቶች በድርጅቱ ተስፋ ቆርጠዋል። የድርጅቱ የማርክሲዝም ሌኒንዚም ፍልስፍና እስካልተቀየረ ድረስ ለውጥ ይመጣል ተብሎ እንደማይጠበቅም በዜናው ተመልክቷል።
የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህር እና ሌሎች እንዳሉት ስብሰባው ድብቅ ነበር። ስለምን እንኳን እንደተወያዩ አይታወቅም። የፓርቲውን ልሳን ወይን መፅሔት፤ ሐምሌ-ነሐሴ በወጣው እትም ላይ “ከአሁን በኋላ ፓርቲያችንን ከአደጋ ለመታደግ ሰፊ ጊዜና ዕድል የለንም” ማለቱን ያስታወሰው ዘገባ፣ ፓርቲው አብዮታዊ መገለጫዎቹን ሊያጣ እንደሚችልና የትግራይ ህዝብ በተለይም ደግሞ ወጣቱ ተስፋ ሊቆርጥበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎቹን ጠቅሶ አመልክቷል። ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ
ህወሓትና የትግራይ ወጣቶች፡ ሆድና ጀርባ?
Image copyrightGIRMAY GEBRU አጭር የምስል መግለጫከህወሓት 12ኛ ጉባኤ ላይ የተወሰደ ፎቶ
“ከአሁን በኋላ ማን መጣ፤ ማንስ ሄደ የሚለው አያስጨንቀኝም። ጭራሽ መርሳት ነው ያለብን” ይላል ለውጥ እንደማይመጣ ተስፋ በመቁረጥ።
“ነገሩ የወንበራቸው ጉዳይ ይመስለኛል። የውስጣቸው አጀንዳ እንጂ የህዝብ ጉዳይ እያስጨነቃቸው አይመስልም።”
ፓርቲውን በመተቸት የሚታወቀው መሓሪ “ድርጅቱ ምን አጀንዳ ላይ ይወያይ እንደነበር አላወቅኩም” ይላል። ለማወቅም ብዙ ጉጉት እንደሌለውም ይናገራል።
“ውጤቱም የርዕዮተ-ዓለም ጉዳይ አይደለም፤ በተግባር እየተጀመረ ያለ የጥፋት መንገድ ነው” በማለት ያስቀምጣል።
Image copyright አጭር የምስል መግለጫከህወሓት 12ኛ ጉባኤ ላይ የተወሰደ ፎቶ
አሉላ ስብሰባው የወጣቱን ትኩረት ያልሳበበት ምክንያት የመረጃ እጥረት በመኖሩ ነው ይበል እንጂ፤ ናሑሰናይ ግን ዋናው ምክንያት ሌላ እንደሆነ ይሞግታል።
“በመጨረሻም እንደወትሮው ነው የሆነው። ትልቅ ያመለጠ ዕድል አድርጌ እቆጥረዋለሁ” ይላል።
ህወሓት አገራዊ ሚናውንም በዚያው ልክ እየተወጣ አይደለም የሚለው ናሁሰናይ፤ የመሪነት ቁመናውን በሌሎች ምናልባትም በኦህዴድ ሊወሰድ እንደሚችል ይገምታል።
በእርግጥ ድርጅቱም “በውስጣችን ያለው የዛገ ነገር መቀየር አለበት” በማለት በልሳኑ ላይ አምኗል።
አሉላ እንደሚለው፤ ህወሓት እንደ ሌሎች እህት ድርጅቶች የመተካካትና አዲስ አመራር የመፍጠር ሥራ አልሰራም የሚል ስሜት ወጣቱ እንዳለው ይቀበላል።