ለቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና መከበር የቆሙት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፡- የፓትርያርኩ የእግድ መመሪያ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያልወሰነበት ኢ- ሕጋዊ መኾኑን ገለጹ በ36ኛው አጠቃላይ ጉባኤ የሚቀርበው ሪፖርታቸው፣ የማኅበሩንም ማካተቱን አስታወቁ የ“ዐዋጅ ነጋሪ” መጽሔትም፣ የአህጉረ ስብከቱን የማኅበር ዘገባ ጭምር ይዞ ተዘጋጅቷል ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት፣ ፓትርያርኩ ለቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲገዙ መከሩ ብፁዓን አባቶች፣ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሓርበኝነት ድጋፋቸውን እየገለጹላቸው […]
ለቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና መከበር የቆሙት ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፡-
- የፓትርያርኩ የእግድ መመሪያ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያልወሰነበት ኢ- ሕጋዊ መኾኑን ገለጹ
- በ36ኛው አጠቃላይ ጉባኤ የሚቀርበው ሪፖርታቸው፣ የማኅበሩንም ማካተቱን አስታወቁ
- የ“ዐዋጅ ነጋሪ” መጽሔትም፣ የአህጉረ ስብከቱን የማኅበር ዘገባ ጭምር ይዞ ተዘጋጅቷል
- ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት፣ ፓትርያርኩ ለቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ እንዲገዙ መከሩ
- ብፁዓን አባቶች፣ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሓርበኝነት ድጋፋቸውን እየገለጹላቸው ነው
Related stories መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል
Powered by Inline Related Posts
†††
በኢ- ሲኖዶሳዊነት የቀጠሉት ሕግ አፍራሹ ፓትርያርክ፡-
- ስለማኅበሩ ቲቪ ሥርጭትና የጉባኤ ተሳትፎ፣በወር ለ3ኛ ጊዜ የእገዳ መመሪያ ጽፈዋል
- በዋና ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት የተካተተው የማኅበሩ ዘገባ እንዳይወጣ ዳግመኛ አዘዋል
- በአጠቃላይ ጉባኤው ፍጻሜ የሚዘጋጀው የማኅበሩ“ዝክረ አበው” እንዳይካሔድም ከለከሉ
- በቅ/ሲኖዶስ የጸደቀ ደንብ ያለውን ማኅበር፣ “የሕግ አግባብና ድጋፍ የለውም፤” ብለዋል
- “ሕዝቡ ከእኔጋ ነው፤” በሚል ሐሳዊነት፣ በአባቶች ላይ ጫና እየፈጠሩና እያስፈራሩ ነው