“Our true nationality is mankind.”H.G.

አቶ በረከት የ ” በቃኝ ” ጥያቄ አቀረቡ፤ አሁን ባላቸው ሃላፊነት ደስተኛ አልነበሩም

Related imageአሁን ባላቸው ሃላፊነት ደስተኛ እንዳልሆኑ የተነገረላቸው አቶ በረከት ስምዖን የስራ መልቀቂያ ያስገቡት ከሁለት ሳምንት በፊት ነው። ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንደተደመጠው አቶ በረከት የስራ መለቀቂያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስገብተዋል።
ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል አቶ በረከት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ በስራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም። እንደ ዘገባው አቶ በረከት በሚኒስትር ማዕረግ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሆነው ሲሰሩ የሚያቀርቡት አገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በአቶ ሃይለማሪያምና በኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም።
አቶ መለስ በድንገት ሲያልፉ በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ሳይወሰን የአቶ ሃይለማሪያምን ሹመት ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ በህወሃት ሰዎች ወቀሳ የተሰነዘረባቸው አቶ በረከት፣ ከአቶ ሃይለማሪያም በቂ ድጋፍና ምላሽ አላደረገም መባሉ ዜናውን ተከትሎ ብዥታ ፈጥሯል።
አቶ መለስ እያሉ አራጊና ፈጣሪ የነበሩት አቶ በረከት ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ተገፍተው ጥናት ላይ በሚያተኩር ስራ እንዲመደቡ መደረጉ አላስደሰታቸውም የሚለው ግን አብዛኞችን የሚያስማማ ጉዳይ ሆኗል። በተጨማሪም አቶ በረከትና አቶ ሃይለማሪያም ቀደም ሲል የነበራቸው ግንኙነት ህወሃት ውስጥ ባለው አዲሱ የሃይል አሰላለፍ የተነሳ መላላቱን ያሳያል። አቶ ሃይለማሪያምም በአዲሱ አሰላለፍ መዳፍ ስር መውደቃቸውን ያመላክታል።
በ1997 ምርጫ የህዝብ ግንኙነቱን ስራ ሲሰሩ የነበሩት አቶ በረከት በምርጫ ክርክር ወቅት ወጣቱን ” ቦዘኔ ለውጥ አያመጣም” ማለታቸውና በክርከሩ ወቅት ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ መወዳደር አለመቻሉ አቶ መለስ አቶ በረከትን ከነበራቸው ሃላፊነት እንዲገፏቸው ምክንያት ሆኗል። በውቅቱ አቶ በረከትን የተኩት አቶ ደሳለኝ እንደ ነበሩ የሚታወስ ነው።

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

አቶ አባ ዱላ ገመዳ ደስተኛ አለመሆናቸውን፣ ዘግይቶም ቢሆን ” መናቃቸውን” በመጥቀስ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው፣ የኢህአዴግ ነባር አመራሮችን የማጽዳቱ ጉዳይ የተገፋበት መሆኑንን ያሳያል የሚሉ ወገኖች፣ በተመሳሳይ በቋፍ ያሉና የተገፉ እንዳሉ የህወሃት ነባር አመራሮች ወደ አመራር ለመመለስ ያደረጉት ሙከራ መከሸፉን እንደማሳያ ይጠቁማሉ።

ለየት ያለ አቋም የሚያራምዱ እንደሚሉት አቶ በረከት ጨርሰዋል። ከጨረሱም ቆይተዋል። የጤናም ጉዳይ አሳሳቢ በመሆኑ መልቀቂያ አስገቡ መባሉ አይስገርምም።
ቢቢሲ የሚከተለውን ዘግቧል።
በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሪ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።
ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት አቶ በረከት የሥራ መልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስገብተዋል።
አቶ በረከት ስምኦን ለበርካታ ዓመታት በቦርድ ሰብሳቢነት ሲመሩት ከነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ሊለቁ እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ተነግሯል።
አቶ በረከት ባለፈው ሳምንት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስገባታቸው የተነገረ ሲሆን፤ ለመጨረሻ ጊዜ በቢሮአቸው ተገኝተው የነበሩት ሀሙስ ዕለት ነበር።
አቶ በረከት በተመሳሳይ ጊዜ ከሁለት የሃላፊነት ቦታቸው የተነሱ ሲሆን ለሥራ መልቀቃቸው ግልፅ ያለ ምክንያት አልቀረበም።
ነገር ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ብዙም ደስታኛ እንዳልነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።
በተለይ ማዕከሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚያቀርባቸው ሃገር አቀፍ የፖሊሲና የአስተዳደር ጥናቶች በጠቅላይ ሚኒስትሩና በመንግሥት ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ብዙም ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ አለመደረጋቸው ለቅሬታቸው ምክንያት እንደሆነ ይነገራል።
ቢሆንም ግን በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል ያላቸውን ሃላፊነት ለመልቀቅ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት እንዳላቸው ማረጋገጥ አልተቻለም።
የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ምርምር ማዕከል በአቶ አባይ ፀሐዬ ዋና ዳይሬክተርነት የሚመራ ተቋም ነው።
አቶ በረከት ስምኦን ከቀደምት የኢህአዴግ አመራሮች መካከል የሚመደቡ ሲሆን የገዢው ፓርቲ አንድ አካል የሆነው የብአዴን አመራር አባል ናቸው።
አቶ በረከት ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ሃላፊነቶች ላይ የቆዩ ሲሆን፤ የማስታወቂያ ሚኒስትርና የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

0Shares
0