Via – BBC Amharic ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት የተለያዩ ለቁማር የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በግብፅ ነበሩ። የዋስትና ሰጪ ድርጅቶችም ከዛን ጊዜ ጀምሮ እንደነበሩ ይታሰባል።

የአሁኗ ኢራቅ ባቢሎን በምትባልበት ዘመን የነበረው የሐሙራቢ ሕግ፤ ቦቶምሪ ስለሚባል ዋስትና የተለያዩ አንቀጾችን የያዘ ሲሆን እሱም ለመርከቦች ጉዞ የሚሰጥ ዋስትናን ከንግድ ብድር ጋር ያጣመረ ነበር።

በዚህም አንድ ነጋዴ የመርከብ ጉዞውን ለማከናወን የሚያስፈለገውን ገንዘብ ይበደራል፤ ነገር ግን መርከቡ ቢሰምጥ ግን ገንዘቡ መከፈል አይኖርበትም።

እ.አ.አ በ1863 መርከበኞችና ነጋዴዎች በሎይድ ቡና ቤትImage copyrightGETTY IMAGESአጭር የምስል መግለጫእ.አ.አ በ1863 መርከበኞችና ነጋዴዎች በሎይድ ቡና ቤት

ከአስር ዓመታት በፊት እንግሊዝ አገር ወደሚገኝ ታዋቂ ቁማር ቤት ጎራ በማለት በዓመት ጊዜ ውስጥ እንደምሞት በገንዘብ ለመወራረድ ሞከርኩ። ቢቀበሉኝ ጥሩ ነበር ምክንያቱም እሰካሁን በሕይወት አለሁ።

ምክንያቱም በሕይወት ወይንም በሞት ዙሪያ ቁማር ብሎ ነገር የለም። ከዚህ አንፃር የሕይወት ዋስትና (ኢንሹራንስ) የሚሰጡ ድርጅቶች ግን በሌላ መልኩም ቢሆን ከዚህ የተለየ ሥራ አይሠሩም።

ከባሕልም ሆነ ከሕግ እይታ በቁማር እና በዋስትና ሰጪ ድርጅቶች መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት እንዳለ አያጠራጥርም።

ከኢኮኖሚ እይታ አንፃር ግን ልዩነታቸው እምብዛም አያስታውቅም።

ምክንያቱም ቁማርተኛም ሆነ የዋስትና ሰጪ ድርጅቶች ወደፊት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለዉ በሚታሰቡ እርግጠኛ ባልሆኑ ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ የገንዘብ ልውውጥ ለማድረግ ይስማማሉ።

**

ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት የተለያዩ ለቁማር የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በግብፅ ነበሩ። የዋስትና ሰጪ ድርጅቶችም ከዛን ጊዜ ጀምሮ እንደነበሩ ይታሰባል።

የአሁኗ ኢራቅ ባቢሎን በምትባልበት ዘመን የነበረው የሐሙራቢ ሕግ፤ ቦቶምሪ ስለሚባል ዋስትና የተለያዩ አንቀጾችን የያዘ ሲሆን እሱም ለመርከቦች ጉዞ የሚሰጥ ዋስትናን ከንግድ ብድር ጋር ያጣመረ ነበር።

በዚህም አንድ ነጋዴ የመርከብ ጉዞውን ለማከናወን የሚያስፈለገውን ገንዘብ ይበደራል፤ ነገር ግን መርከቡ ቢሰምጥ ግን ገንዘቡ መከፈል አይኖርበትም።

ይህ ድንጋይ ላይ ተቀርጾ የምንመለከተው በሐሞራቢያን ዘመን ነበረው ንግድና የመድሕን ምሳሌ ነውImage copyrightALAMYአጭር የምስል መግለጫይህ ድንጋይ ላይ ተቀርጾ የምንመለከተው በሐሞራቢያን ዘመን ነበረው ንግድና የመድሕን ምሳሌ ነው

በዚያው ዘመን ቻይናውያን በባሕር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመቀነስ ዕቃዎቻቸውን በተለያዩ መርከቦች ላይ ከፋፍለው ይጭኑ ነበር። ስለዚህ የትኛውም መርከብ ቢሰምጥ ከተለያዩ ነጋዴዎቸ የተለያዩ እቃዎችን የያዘ ስለሚሆን ጉዳቱ የአንድ ሰው አይሆንም ማለት ነው።

ነገር ግን ይህን ሁሉ ማድረግ ደግሞ አድካሚ ነው። ስለዚህ ይህን በዋስትና መልኩ በውል ላይ ማስቀመጡ ይቀል ስለነበር ሮማውያንም ከሺህ ዓመታት በኋላ መፈራረም ጀመሩ። ከዚያም ጄኖዋና ቬኒስ በመባል የሚታወቁት የኢጣልያ ከተሞች ለሜዲቴራንያ መርከቦች ዋስትና የተሻሉና የላቁ መፍትሔዎችን አመነጩ።

ለወሬ መሞት

ኤድዋርድ ሎይድ የተሰኙ ግለሰብ እ.አ.አ በ1687 ዓ.ም በለንደን ወደብ አካባቢ ታወር ስትሪት የተባለ ቡና ቤት ከፈቱ። ቡና ቤቱም ሰፊና ምቾት ያለው በመሆኑ ንግድ ተጧጧፈ። በእሳት ዙሪያ ቡናና ሻይ እየተጠጣ የሚወራው ብዙ ባለሀብቶችን ለመሳብ ቻለ። በጊዜው ስለነበረው የለንደን ወረርሽኝ፣ ስለ ታላቁ እሳት፣ ስለ ዳች መርከበኞችና ንጉሱን ስለገለበጠው አብዮት ይወራ ነበር።

ከሁሉም በላይ ግን የመርከብ ወሬዎች ይበዙ ነበር። ለምሳሌ የትኞቹ መርከቦች ምን ዓይነት ጭነት ይዘው እንደሚመጡ፤ በሰላም መድረስ አለመድረሳቸው የወሬ ርዕሶች ነበሩ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ለውርርድ አጋጣሚዎች ይፈጠሩ ነበር።

በሎይድ ቡና ቤት ይመጡ የነበሩት ተጠቃሚዎች እ.አ.አ በ1757 በተገደለው አድሚራል ጆን ቢንግ ሕይወት ያስይዙ ነበርImage copyrightGETTY IMAGESአጭር የምስል መግለጫበሎይድ ቡና ቤት ይመጡ የነበሩት ተጠቃሚዎች እ.አ.አ በ1757 በተገደለው አድሚራል ጆን ቢንግ ሕይወት ያስይዙ ነበር

ከተወራረዱባቸው ነገሮች አንዱ የነበረው አድሚራል ጆን ቢንግ የተባለው መርከበኛ ከፈረንሳይ ጋር በተካሄደው የባህር ላይ ጦርነት ብቃት ስለሌለው ይገደላል ወይስ አይገደልም የሚል ነበር። በውጤቱም አድሚራሉ ተገድሏል።

ወደዚያች ቡና ቤት ይሄዱ የነበሩትም ሰዎች በራሳቸው ሕይወት ላይም ከመወራረድ ወደኋላ አይሉም ነበር።

ኤድዋርድ ሎይድም ተጠቃሚዎቹ ለቡና ብቻ ሳይሆን ለወሬና ለመረጃም የተጠሙ እንደነበሩ ስለተረዳ በጉዞ ላይ ስላሉ መርከቦች፣ ስለወደቦችና ስለማዕበል መረጃ አሰባስበው ጋዜጣ የሚያዘጋጁ ሰዎችን አሰማራ። ይህም ጋዜጣ ‘የሎይድ ሊስት’ በመባል ይታወቃል።

የሎይድ ጋዜጣ በየቀኑ እ.አ.አ እስከ 2013 ድረስ ይታተም ነበርImage copyrightGETTY IMAGESአጭር የምስል መግለጫየሎይድ ጋዜጣ በየቀኑ እ.አ.አ እስከ 2013 ድረስ ይታተም ነበር

የኤድዋርድ ቡና ቤት የመርከብ ጨረታዎችንና የመረከበኞችን ታሪኮች ታስተናግድ ጀመር። የመርከብ ዋስትና መግዛት የሚፈልግም ቢኖር ይችል ነበር። ውሉም ተዘጋጅቶ በዋስትና ሰጪው ይፈረምበታል። በዚህም ምክንያት የቡና ቤት ውስጥ ቁማር መቼ እንደቆመና መደበኛው የዋስትና አገልግሎት መቼ እንደጀመረ ለማወቅ ይከብዳል።

የኤድዋርድ ቡና ቤት ከተከፈተ ከሰማኒያ ዓመታት በኋላ እዚያው ይሰበሰቡ የነበሩ ዋስትና ሰጪዎች ‘ሶሳይቲ ኦፍ ሎይድስ’ የተሰኘ ማህበር አቋቋሙ። ባለንበት ዘመንም በዋስትና መስጠት ንግድ ሥራ ‘የሎይድስ ለንደን’ ስም ከታዋቂዎቹ አንዱ ነው።

ሎይድ የመድሕን ድርጅት አይደለም ለተለያዩ ባለሚያዎች የመገበያያ ቦታ እንጂImage copyrightGETTY IMAGESአጭር የምስል መግለጫሎይድ የመድሕን ድርጅት አይደለም ለተለያዩ ባለሚያዎች የመገበያያ ቦታ እንጂ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን የሁሉም ዘመናዊ ዋስትና የመስጠት ሥራ አነሳስ ከቁማር ጋር የተያያዘ ነው ማለት አይደለም። ሌላኛው ዓይነት የዋስትና አገልግሎት ደግሞ የጀመረው በወደቦች አካባቢ ሳይሆን በተራሮች ላይ ነበረ።

ይህም የአልፓይን ገበሬዎች ላም ወይንም ልጅ ሲታመምባቸው በጋራ የሚንከባከቡበትን ማህበር እ.አ.አ በ16ኛው ክፍለ ዘመን መስርተው ነበረ።

የሎይድ ዋስትና ሰጪዎች አደጋን የሚያስቡበትና ለግብይት የሚያቀርቡት ሲሆን ለአልፓይን ገበሬዎቹ ደግሞ አደጋ ሁሉም የሚከፋለው ነገር ነበር።

እነዚህም የአልፓይን ገበሬዎችም ከተራራዎቹ ወደ ዙሪክና ምዩኒክ ከተሞች በማምራት የዓለምን ታላላቅ የዋስትና ሰጪ ድርጅቶች መሠረቱ።

የማይታዩት የአደጋ ገጽታዎች

በአሁኑ ወቅት አደጋንና የአደጋ ሥጋትን ለመጋራትና ድጋፍ ለማድረግ ከሚሰሩ ተቋማት መካከል መንግሥታት በግዙፍ የገንዘብ አቅማቸውና አደረጃጀታቸው ቀዳሚዎቹ ናቸው።

በመጀመሪያ ላይ መንግሥታት ዋስትና ወደ መስጠት ሥራ ላይ የተሰማሩት እ.አ.አ በ1600ዎቹና 1700ዎቹ አውሮፓ በጦርነት በምትታመስበት ጊዜ ትርፍ ለመሰብሰብና ሰራዊታቸውን ለመደጎም በማሰብ ነበረ።

በዚህ ወቅት በመደበኛው የክፍያ ሂደት ማለቅ ያለባቸውን የተለመዱ የዋስትና ሰነዶችን ከመሸጥ ይልቅ መንግሥታት ከፍተኛ ፈላጊ ያላቸውንና ለአቅርቦትም ቀላል የሆኑትን አክሲዮኖችን መሸጥ ጀመሩ። እነዚህ አክሲዮኖች ከዋስትና ዓይነቶች መካከል ሲሆኑ፤ ግለሰቦች ረጅም ዓመታት የሚኖሩ ከሆነ ያላቸውን ገንዘብ በሙሉ እንዳይጨርሰው ችግር እንዳይገጥማቸው መተማመኛ ይሆናቸዋል።

ከጊዜ በኋላ መንግሥታት የዋስትና አገልግሎትን በመስጠት ትርፍ መሰብሰብን ትተው ዜጎቻቸው እንደ ሥራ አጥነት፣ በሽታ፣ የአካል ጉዳትና እርጅናን የመሳሰሉትን ሲገጥማቸው ዋነኛ የድጋፍ ምንጭ አድርገውታል።

የሀብታም ሃገራት ነዋሪዎች እነዚህን የመሳሰሉ የዋስትና አገልግሎቶችን ከመንግሥታት የሚያገኙ ሲሆን፤ በደሃ ሃገራት የሚኖሩት ግን እንደ ግብርና ምርት መታጣት ወይም በሽታን በመሳሰሉ ሕይወትን የሚቀይሩ ክስተቶች የሚገጥማቸው ጊዜ ድጋፍ ለማግኘት አይችሉም። የግል ዋስትና ሰጪ ድርጅቶችም በእነዚህ ሃገራት ውስጥ ለመሥራት ፍላጎታቸው ዝቅተኛ ነው።

የቀይ መስቀል ድርጅት የሌሶቶን ድርቅ የዘመናችን በጣም መጥፎ ድርቅ በማለት ሰይመውታልImage copyrightGETTY IMAGESአጭር የምስል መግለጫየቀይ መስቀል ድርጅት የሌሶቶን ድርቅ የዘመናችን በጣም መጥፎ ድርቅ በማለት ሰይመውታል

ኣሳሳች እውነታዎች

ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች የሕሊና ሰላም ከመስጠት በተጨማሪ ለአንድ ሃገር የምጣኔ ሃብት ጤናማነት ደግሞ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ መሆን ይችላሉ።

በቅርቡ ሌሶቶ ውስጥ የተካሄደ ጥናት እንዳመለከተው ገበሬዎች ድርቅን በመስጋት ውጤታማ የሚሆኑባቸው ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩና ሥራቸውን እንዲያስፋፉ እንቅፋት ከሆኑባቸው ነገሮች መካከል የዋስትና ሠጪ ተቋማት አገልግሎት አለማግኘታቸው አንዱ ነው።

ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች የራሳቸውን ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች በመክፈት የግብርና ምርት ዋስትና መስጠት ሲጀምሩ አርሶ አደሮቹ የሥራቸውን ዘርፍ ማስፋት ጀመሩ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *