ዓመታዊ ስብሰባው፥ በደመናማው የአ/አበባ ረፋድ፣በጥብቅ ጸጥታዊ ቁጥጥር ተከፈተ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ አጠቃላይ ዓመታዊ ሪፖርታቸውን፣ በንባብ እያሰሙ ነው ከታላቁ አጠቃላይ ጉባኤ፣“ሰላማዊ ዓላማ እና ሰላማዊ ሐሳብ” እንደሚጠበቅ አሳሰቡ ከኅትመት የተቆረጠውን የማኅበሩን የሥራ ክንውን፣ በሪፖርታቸው አካትተው አሰሙ! የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች፣ በየአንቀጹ ድጋፋቸውን በጋለ ጭብጨባ ገልጸዋል! አህጉረ ስብከትም፣የብፁዕነታቸውን አርኣያ ተከትለው ዘገባውን እንዲያሰሙ ይጠበቃል የማኅበሩ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የተቆረጠበት፣“ዐዋጅ […]

via በፓትርያርኩ ሕገ ወጥ ትእዛዝ የተቆረጠው የማኅበረ ቅዱሳን የ2009 ዓ.ም. ሪፖርት ለአጠቃላይ ጉባኤው ቀረበ፤ 36ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ተጀመረ — ሐራ ዘተዋሕዶ

 • ዓመታዊ ስብሰባው፥ በደመናማው የአ/አበባ ረፋድ፣በጥብቅ ጸጥታዊ ቁጥጥር ተከፈተ
 • ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ አጠቃላይ ዓመታዊ ሪፖርታቸውን፣ በንባብ እያሰሙ ነው
 • ከታላቁ አጠቃላይ ጉባኤ፣“ሰላማዊ ዓላማ እና ሰላማዊ ሐሳብ” እንደሚጠበቅ አሳሰቡ
 • ከኅትመት የተቆረጠውን የማኅበሩን የሥራ ክንውን፣ በሪፖርታቸው አካትተው አሰሙ!
 • የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች፣ በየአንቀጹ ድጋፋቸውን በጋለ ጭብጨባ ገልጸዋል!
 • አህጉረ ስብከትም፣የብፁዕነታቸውን አርኣያ ተከትለው ዘገባውን እንዲያሰሙ ይጠበቃል
 • የማኅበሩ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የተቆረጠበት፣“ዐዋጅ ነጋሪ” መጽሔት፣ ተሠራጭቷል
 • ፓትርያርኩ፥ ስለካህናት ምግብና፣ ስለ ሉዓላዊት ቤ/ያን አንድነት መጠበቅ ቢናገሩም…
 • .ኹነኛ ዳታና ትንተና በሚሻው“የምእመናን ፍልሰት”ያልተጠነቀቀ ገለጻቸውን ደገሙት፤

†††

በፓትርያርኩ ሕገ ወጥ ትእዛዝ እንዳይታተም በታገደው የማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት፥ በ2009 ዓ.ም. የአገልግሎት ዓመት፡-

 • 23ሺሕ 156 ሐዲሳን አማንያን በልጅነት ጥምቀት መጨመራቸውን፤
 • በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት፣187 ጉባኤያት መካሔዳቸውን፤
 • ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ለአብነት ትምህርት ቤቶች ድጎማ መደረጉን፤
 • በ2.4 ሚ.ብር፣ የካህናት ማሠልጠኛና የአብነት ት/ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች፤
 • 1.35 ሚ. ብር ግምት ያላቸው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ዲዛየኖችና ፕሮጀክቶች፤
 • የማኅበሩ ሒሳብ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ቁጥጥር መምሪያ ተመርምሯል፤
 • 29.4 ሚሊዮን ብር ከአባላት ተሰብስቦ 26.5 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል፤
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

†††

ከ“ዐዋጅ ነጋሪ” መጽሔት አላግባብ ተቆርጦ የወጣውን የማኅበሩን የ2009 ዓ.ም. የተጨመቀ ሪፖርት ከዚህ በታች ይመልከቱ፤

ዚህ ዓመት ማኅበረ ቅዱሳን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያችን ሰጥቷል፡፡

 • ከአኅጉረ ስብከት ጋር በመተባበር 23,156 ሐዲሳን አማንያን የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
 • በሐገር ውስጥ 173 በውጭ 14 የሕዝብ ጉባዔያት ተካሂደዋል፡፡ በወላይትኛ፣ በጋሞኛ እንዲሁም በጉራግኛ ቋንቋ የመዝሙር እና የስብከት ቪሲዲዎች ተዘጋጅተው ለምእመናን በነጻ ተከፋፍለዋል፡፡ በአማርኛ 119 እና በአፋን ኦሮሞ 50 ጽሑፎች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ተዘጋጅተው በማኅበሩ በድረ ገጽ  ተለቅቀዋል፡፡ “ዳንጋ ሉቡ” በሚል ርዕስ በአፋን ኦሮሞ የሚታተመው መጽሔት 20 ሺህ ኮፒ ለሥርጭት በቅቷል፡፡ ከ280 ሺህ በላይ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል፡፡
 • ለአብነት መምህራንና የአብነት ተማሪዎች 3,501,978.00 /ሦስት ሚሊየን አምስት መቶ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ ስምንት ብር/ ድጎማ ተደርጓል፡፡ ለ1410 የአብነት ተማሪዎች የመሠረታዊ ፍላጎት ማሟያ ድጋፍ ተደርጓል።
 • በነገሌ ቦረና ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤትና የስብከተ ወንጌል ማሰልጠኛ ፕሮጀክት አሜሪካ ከሚገኘው በዓለ ወልድ ማኅበር ጋር በመተባበር በ2.4 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተሠራ ይገኛል። በሴቲት ሁመራ ሀገረ ስብከት የሁመራ የአብነት ት/ቤት ግንባታ የካህናት ማሰልጠኛ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል። በባሌ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤትና የካህናት ማሰልጠኛ ግንባታ ፕሮጀክት እየተጠናቀቀ ይገኛል። በዛራ ቅዱስ ሚካኤል የቅኔ ጉባኤ ቤትና የመምህሩ መኖሪያ ቤት ተጠናቅቆ ርክክብ ተደርጓል።
 • በደቡብ ትግራይ ሀገረ ስብከት መካነ ሕይወት አርባዕቱ እንስሳና አቡነ ኪሮሰ አንድነት ገዳም የወፍጮ ፕሮጀክት በብር 240,000 ተጠናቅቆ ርክክብ ተደርጓል፡፡ በማእከላዊ ትግራይ የደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት በብር 900,000 ተጠናቅቆ ርክክብ ተደርጓል። በከሚሴ ሀገረ ስብከት የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በብር 844,280.77 ተጠናቅቆ ርክክብ ተደርጓል።
 • ለ120 አብያተ ክርስቲያናት የንዋያተ ቅዱሳት ድጋፍ ሲደረግ በሦስት የአብነት ትምህርት ቤቶችና በ1 ገዳም ደግሞ የሕክምና ድጋፍ ተደርጓል። ለጨጎዴ ሐና የቅኔና የመፃሕፍት ምስክር ትምህርት ቤት በደረሰው ቃጠሎ ምክንያት የገንዘብ እና አልባሳት ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በዋልድባ አብረንታት ገዳም በደረሰው የጎርፍ አደጋ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
 • አጠቃላይ ግምታቸው 1.35 ሚሊዮን ብር ሊያስከፍሉ የሚችሉ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ዲዛይኖች እና ፕሮጀክቶች በነፃ ተሠርተው ተሰጥተዋል፡፡
 • የ2007 እና 2008 ዓ.ም የማኅበሩ ሒሳብ በጠቅላይ በቤተ ክህነት የቁጥጥር መመሪያ ተመርምሯል፡፡
 • የ24 ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ እትም 84,000 ሺህ ኮፒ እና የ12 ሐመር መጽሔት እትም 186,000 ሺህ ለሥርጭት በቅተዋል፡፡ በዓይነት ብዛት 92 መጻሕፍት በአጠቃላይ 550 ሺህ ቅጅዎች አሳትሞ አሠራጭቷል፡፡ በኦሮምኛ የ10 መጻሕፍት 43,000 ቅጂ ተሠራጭቷል፡፡
Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

ማኅበሩ የተጠቀሱትን ተግባራት ለማከናወን በበጀት ዓመቱ ከአባላቱ ብር 29,366,828.71 አሰባስቧል፤ ከዚህ ውስጥ ብር 26,497,937.42 ያህሉን ወጭ ያደረገ ሲሆን፣ ከወጭ ቀሪ ብር 2,868,891.29 ነው፡፡

የአጠቃላይ ጉባኤው 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ የማጠቃለያ መርሐ ግብር በከፊል፤

በአጠቃላይ ጉባኤው 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ፣ የማኅበረ ቅዱሳን “ዝክረ አበው” የመታሰቢያ ራት ዝግጅት የተካተተበት የቀድሞው መርሐ ግብር ክፍል(ከላይ) እና የመታሰቢያ ዝግጅቱ፣ በፓትርያርኩ ሕገ ወጥ ትእዛዝ እንዳይካሔድ ከተከለከለ በኋላ ለጉባኤተኞች የተሠራጨው መርሐ ግብር ክፍል(ከታች)፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *