በህይወት አጋጣሚ የሚከሰቱ እንደ ልጅ ሞት፣ ፍቺና ከስራ መባረር ያሉ ውጥረት የተሞላባቸው አጋጣሚዎች አዕምሮን ቢያንስ በአራት ዓመታት ያስረጃሉ ይላል- በአሜሪካ የተደረገ ጥናት።

አጥኚዎቹ ለናሙና በ50ዎቹ እድሜ ላይ ያሉ 1300 ሰዎችን የማሰብና የማስታወስ ችሎታ መዝነዋል።

ሌሎች ባለሙያዎች ግን ጥናቱ የማሰብም ሆነ የማስታወስ ችሎታን የሚያሳጣው በሽታ ችግሩን ምን ያህል እንደሚያባብሰው ስላላሳየ የችግሩን ሌሎች መንስኤዎች ዘንግቷል በሚል ይተቻሉ።

ጥናቱ ምንም እንኳ በመርሳት በሽታና በጭንቀት መካከል ያለውን ቀጥተኛ ግንኙነት ባይመለከትም አስጨናቂ አጋጣሚዎች በአዕምሮ አቅም ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ እንደሚችሉና በሂደትም ወደ መርሳት በሽታ ሊቀየሩ እንደሚችሉ ይታወቃል።

ዝቅተኛ ትውስታ

ጽንሰ ኃሳቡ ጭንቀት በአዕምሮ ላይ የሚፈጥረው የማቃጠልና የማሳበጥ ጉዳት ወደ ዝቅተኛ ትውስታና የማሰብ አቅም ማጣት ሊቀይረው ይችላል የሚል ነው።

አሁን ደግሞ በተግባር ለማረጋገጥ ጉዳዩ በሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት ነው።

በዊስኮንሲን ዩኒቨርሲቲ የጤና ትምህርት ክፍል የተጠናው ጥናት ግን አፍሪካ አሜሪካውያን ከሌሎች በተለየ ለጭንቀት ተጋላጭ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ምክኒያቱም ለጥናቱ ናሙና ከተወሰዱት የተለያየ ዘር ካላቸው ቡድኖች ሁሉ አነሰተኛ የማስታወስ ችሎታ የተመዘገበባቸውና በድሃ መንደሮች የሚኖሩት እነርሱ ስለነበሩ ነው።

ሁሉም ተጠያቂዎች አስጨናቂ ክስተቶች በሚል የገለጹት ከትምህርት ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶችን ፣ የገንዘብ እጥረትን፣ የጤና ችግር እና ስነልቦናዊ ቀውሶችን የሚያካትቱ ጉዳዮችን ነው።

በለንደን በተካሄደው አልዚመር ላይ ባተኮረ ዓለማቀፍ ጉባኤ ላይ የቀረቡ ሌሎች ጥናቶችም በቀድሞ ህይወታቸው አስጨናቂ ነገር የገጠማቸው ሰዎች የአዕምሮ አለማገናዘብ በሽታ ስጋት ላይ እንደሚወድቁ የሚያረጋግጡ ናቸው ።

የአልዚመር ማህበር ጥናትና ልማት ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዶውግ ብራዉን የጭንቀትን ሚና መረዳት በጣም ውስብስ ነበር ይላሉ።

“ጭንቀትን ለበሽታው ሊያጋልጡ ከሚችሉ እንደ ድንጋጤና መደበት ያሉ ችግሮችመለየት ከባድ ነበረ፤ ያም ሆነ ይህ ግኝቶቹ የሚያመለክቱት በውጥረት ለተሞላ ሕይወት የተጋለጡ ሰዎችን ለመርዳት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ነው።

በብሪታኒያ 850 ሺህ ሰዎች የእዕምሮ አለማጋነዘብ በሽታ(ዲሜንሺያ) ህሙማን ናቸው።

የአዕምሮ ምስልImage copyrightSCIENCE PHOTO LIBRARYአጭር የምስል መግለጫበግራ በኩል ያለው በበሽታው የተያዙት አዕምሮ ሲሆን በቀኝ ያለው ደግሞ የጤነኛ ሰዎች ነው

የመያዝ እድሉ ከእድሜ ጋር እየጨመረ ስለሚሄድ በሽተኞቹ በአብዛኛው ከ65 ዓመት በላይ ቢሆኑም 42 ሺህ የሚሆኑት ከዚህ እድሜ በታች ያሉ ናቸው።

የአልዚመር ጥናት ዳይሬክተሯ ዶክተር ካሮል ሮትሌጅ እንደሚሉት በጨንቀትና በትውስታ ማጣት ግንኙነት መካከል ሌሎች ወሳኝ ሁኔታዎችም ሊኖሩ ይችላሉ፤ በእርግጥም አዕምሮን ማጥናት በጣም አስቸጋሪ ነው

“አሁን ብዙዎች እየተረዱት ያለው ሀቅ በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ክስተቶችና ተሞክሮዎች በአዕምሮ ላይ ከአስርት ዓመታትም በኋላ ተጽእኖ ሊፈጥሩ መቻላቸውን ነው። እጥኚዎችም ቢሆኑ የአዕምሮ ጤናን ይበልጥ ለመረዳት ሙሉ የህይወት ዘመናቸውን የሚዳስሱበትን ዘዴ መፈለግ አለባቸው”

በአዕምሮ አለማገናዘብ በሽታ የመያዝ ስጋትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

  1. በሳምንት ለአምሰት ቀናት፣ በቀን ለ 30 ደቂቃዎች እንቅስቃሴ ያድርጉ
  2. አለማጨስ ፤ የሚያጨሱ ከሆነ ደግሞ ያቁሙ
  3. እንደ አሳ፣ ፍራፍሬና አትክልት ያሉ ጤናማና የተመጣጠኑ ምግቦችን ይመገቡ። የቀይ ስጋና የስኳር ፍጆታዎን ይቀንሱ
  4. በሳምንት ቢበዛ ከ 14 ጠርሙስ በላይ የአልኮል መጠጥ አይውሰዱ።
  5. እንደደም ግፊት፣ ከፍተኛ ኮልስትሮልና፣ ስኳር ያሉ በሽታዎችን ይቆጣጠሩ።
  6. በስኳር ፣ በልብ ወይም በደም ዝውውር ማቆም በሽታ የመያዝ እድሎ እንዲቀንስ ጤናማ ክብደት ይኑሮት።
  7. በየእለቱ የተለያዩ ጥያቄዎችን በመመለስ ፣ እንቆቅልሽ በመፍታትና አዳዲስ ነገሮችን በመማር ለአዕምሮ የማሰቢያ ጊዜ ይስጡ።
  8. ጥሩ ማህበራዊ ግንኙነትን ይፍጠሩ

ቢቢሲ አማርኛ 

 

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *