ኢ/ር ግዛቸው ሸፈራው በሀብታሙ መፅሃፍ ውስጥ ሰሜ ተነሳ ብሎ ሰባት ገፅ ያለው አዚቡርዚውን ከትቦ ማን መሆኑን የሚያሳይ ፅሁፍ አቅርቦልናል፡፡ እኔ በግሌ የሀብታሙ አያሌው መፅኃፍ ለምን ተተቸ የሚል ነገር የለኝም፡፡ ይልቁንም ባይተች ነው ቅር የሚለኝ፡፡ ነገር ግን በግል ቂም ተነሳስቶ እራስን በሚያሳንስ መንገድ ሲሆን ግን ቅር ያሰኛል፡፡ ለትዝብትም ይዳርጋል፡፡ በተለይ ደግሞ በኢንጂነሪንግ መስክ ብዙ ሂሣብና ሎጂክ ከሚያውቅ ሰው ሲሆን ጉዳዮን ከበድ ያደርገዋል፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ሀብታሙ ለመሳደብ አርባና አምሳ ዓመት ወደ ኋላ ሄዶ ዘጠነኛ ክፍል አስተማሪውን አሰታውሶ የልጅ ልጁን ለማሳነስ የሄደበት መንገድ ምን ያህል መንገድ ጠፍቶት እየባዘነ  እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ በረከት ሰምኦን ሰሙን ጠርቶ በመፅኃፉ ሲያዋርደው መልስ ያልሰጠው ግዛቸው አሁን ግን ለሀብታሙ መልስ ለምስጠት የቅል ተረት ያነሳው ምን አልባትም ሀብታሙ አሜሪካ ስለሆነ እሩቅ ነው ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ የኢ/ር ገዛቸው ስም ግን ወደደም ጠላ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ለዘላለም ሲጠራ ይኖራል፡፡ ይህን በበጎም ሆነ በክፉ እንዲጠራ ያደረገው ደግሞ እራሱ ግዛቸው ነው፡፡ ልጆቹም ቢሆን በዚህ ጉዳይ ሰሙ ሲነሳ ሊኮሩበት የፈለጉትን ያህል ሊያፍሩበት የሚያስችል ስራ የሰራው እራሱ ግዛቸው መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡ በእኔ ግምገማ ግዛቸው በአንድነት ላይ ያደረገውን ግለኝነት ሳያደርግ ቢሞት ለልጆቹ ክብር ነበር፡፡ አሁን ግን ምንም በማያወላውል ሁኔታ ማፈሪያ ሆኖዋል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሰለ ሀበብታሙ ከፃፈው ሰባት ገፅ ውስጥ የመጀመሪያው ሁለት ገፆች የሚያወሩት ሰለ ሀብታመ የስልጣን ጥመኝነት ሲሆን ይህም የተገለፀው በተሰጡት ሃላፊነቶች ነው፡፡ ይህ ሊተች የሚችለው እውነት ወይም ውሸት ተብሎ ይህን ሃላፊነት አልነበረህም በሚል እንጂ ዝም ብሎ በደፈናው የስልጣን ሱስ በሚል መሆን የለበትም፡፡ ሀብታሙ አንድነተት ውስጥ የገባው ለእነ ሰዬ በተከፈተው መንገድ ነው የሚለው ደግሞ በፍፁም የተሳሳተ ነው፣ ሀብታሙ አንድነት ሲገባ ግዛቸው እራሱ እንኳን አስገቢ ሊሆን አንድነት ውስጥ እራሱ ለመግባት ደጅ የሚጠናበት ወቅት ነበር፡፡ ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው አንድነትን ወድቋል ብሎ ጥሎ ከሄዶ በኋላ ሞቅ ሲል አለሁበት ለማለት መምጣቱን ሰው የሚያውቅ ያለ አይመስለውም፡፡ የሚሊዮኖችን ድመፅ የእርሱ ፕሮጀክት አድርጎ ሲያቀርብም አያፍርም፡፡

ሀብታሙን ለመክስስ የተጠቀመበት ከስብሃት ነጋ ጋር ስለነበረው ግንኙነት በተመለከት ግንኙነቱ እራሱ የተጀመረው እኔ እና ስብሃት ነጋ በጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ባደረግነው ንግግር መነሻ  ሲሆን በዚህ መነሻ በተደረገው ግንኙነት ውይይቱ ቢጀመርም በተለያየ ምክንያት ሊቀጥል አልቻለም፡፡ ግዛቸው እንደሚለው በሰራ አስፈፃሚ ተነጋግረን ግርማ መሳተፍ የለበትም አልን ያለውም ውሸት ነው፡፡ እንድሳተፍ ተጠይቄ ፈቃደኛ ያልሆንኩት እኔ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ከግዛቸው ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ስለአልነበርኪ ነው፡፡

ኢ./ር ግዛቸው ሸፈራው አንድነትን ለመታደግ ስልጣኔን የለቀቅሁት በፈቃዴ ነው በል መግለጫ ሰጥ ለዚህ የሚገባህን ክብረ እንስጥህ ስንለው እንቢ ብሎ በአንድነት ውስጥ እንደ ውሻ ቀዳዳ ቀዶ ጅብ ማስገባቱን ረስቶ አሁን ደግሞ ሀቀኛ መስሎ እረሱን ሊከላክል ብቅ ማለቱ ያሳዝናል፡፡ ይህን ሰባት ገፅ ለመፃፍ ያወጣውን ጉልበቱን አንድነትን ለማዳን አንድ ገፅ ወይም ሁለት መስመር ለመፃፍ ቢጠቀምበት አንድነት በፖለቲካ ውሳኔ ሲፈረስ መዋጮ ባያዋጣ ይችል ነበር፡፡ አልፎ ተርፎ ከሳሽ ሆኖ ፋና ላይ ቀርቦ ሲከሰን እንዳልነበር አሁን ደግሞ ሀብታሙን ሊከስ ሲመጣ ያሳፍራል ያናድዳልም፡፡ ለማነኛውም ግዛቸው ያነሳቸው ሶሰት ነጥቦች አንደኛ ለፕሬዝዳንትነት የመጣሁት ተለምኜ ነው የሚለው ቅጥፈት መሆኑን ብዙ ሰው አልተረዳውም;; አውነት ነው ለማኝ አደረጅቶ በተለመደ የሴራ መስመር መምጣቱን በእርግጥ እንደ ተክሌ በቀለ ተሳስተው የተከተሉት መኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም፣ አውነቱ ግን የራሱ የስልጣን ፍላጎት ነው፡፡ በምንም ዓይነት ተለምኖ ሳይሆን ለምኖ መምጣቱ ግልፅ መሆን አለበት፡፡ ሁለተኛ በሸዋ ፖለቲካ በሚል ያቀረበው መከላከያ የሚያሳፍር ሲሆን እኔን ለማሸነፍ በሸዋ ብቻ ሳይሆን ሲሰፋ በአማራ.፣ በእድሜ፣ በኢኮኖሚ፣ ወዘተ ከፋፍሎ ሴራ መስራቱን አውቃለሁ፡፡ በዚህ ዓይነት ሴራ መወዳደር ባለመፈለጌ መሸነፌን አምኜ ተቅብያለሁ፡፡ ሃላፊነቱን ደግሞ ለተለየ ጥቅም ሰለማልፈልግ አውቄ መተዌን ግዛቸው የተረዳው አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም በዝረራ አሸነፍኩት ብሎ መፎከር ቁም ነገር አድርጎታል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ቀደም ሲል የነበርን አመራሮች የጀመርነውን የድርድር እና ከጥላቻ ነፃ የሆነ ፖለቲካ ያለ ባሕሪው የራሱ ማድረጉ ነው የሚያስገርመው፡፡ እርግጥ ነው በመጨረሻ አካባቢ ፍርሃት ይዞት ድርድር ድርድር ማለት ጀምሮ ነበር፡፡ ለዚህም ነበር ፈሪ ለድርድር አይሆንም ብለው ከስራ አስፈፃሚነት የለቀቁት፡፡ ለማነኛውም ግዛቸው ሸፈራው እንደምንም አምጦ በረከት ሰምኦን በመፅሃፉ ሲያዋርደው መልስ ስጥ ብለን ስንለምነው አንቢ ብሎ ለሀብታሙ የዚህ ዓይነት የወረደ ፅሁፍ መፃፉ አሳዝኖኛል፡፡ ለማነኛውም የእኔ ደግሞ ከቻለ አንብቦ ምን እንደሚል እጠብቃለሁ፡፡ መቼም እኔን በስልጣን ጥመኝነት ያመኝ ይሆን?

ግርማ ሰይፉ ማሩ

የሃብታሙ አያሌው ቅጥፈትና የባዶ ቅል ጥሬ መንኳኳት ተምሳሌት – ግዛቸው ሽፈራው (ኢንጂነር) የኢንጂነር ግዛቸው ጽሁፍ እዚህ ላይ ያንብቡ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *