birtukan

Image- Ethiopia frees opposition leader Birtukan Mideksa | World news | The Guardian

ብርቱካን ሚደቅሳ ለትግሉ ብዙ ዋጋ የከፈለች እህት ናት። በወህኒ ብዙ ጉዳት ደርሶባታል። የአካልና የስነ-ልቦና። በአክብሮት ለኢትዮጵያ ህዝብ ደብዳቤ ጽፋ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ፖለቲካው እንደማትገባ አሳውቃ ነው ኑሮዋን በዉጭ አገር ያደረገችው። ሕዝብን ደጋፊዎች አላምታታችም። አልዋሸችም። አላጭበረበረችም። አንዳንዶች እንዳደረጉት።፡

ይች እህት መድረክ፣ ክብር ፣ ዝናን ፣ ጥቅምን የምትፈልግ ቢሆን ኖሮ እመኑኝ በየቦታው እናገኛት ነበር። ግን ልጅቷ ትልቅ ሰው ናት። ጨዋ ናት። የማታደረገውን ባዶ ተስፋ ለሕዝብ መስጠት የማትፈለግ ናት። ባዶ ፕሮፖጋንዳ የማይመቻት ናት። ልታይ፣ ልታይ የማትል ናት።

በጭካኔ ነበር ሕወሃቶች በወህኒ ሲያሰቃዩአት የነበረው። ለስድስት ወራት ጨለማ ቤት ውስጥ አስቀምጠው የስነ ልቦና ቶርቸር ፈጽመዉባታል። ይሄን ሁሉ ያደረሰቡታ ሰዎች መሪ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሲሞት ግን፣ “እንኳን እግዚአብሄር ደፋው” አላለችም። በዚያ እድሜው በማለፉ ሐዘኗን ነው የገለጸችው። እርሱ ልክ እንደ ሌሎች የሕወሃት ጎዶቹ ጨካኝ የነበረ ቢሆንም እርሷ ግን ለጭካኔ የሰጠጭው መልስ ርህራሄ ሐዘኔታን የተሞላ ነበር።

Related stories   እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!

ብርቱካን ሚደቅሳ ከደረሰባት ጉዳት እያገገመች፣ በእውቀት በትምህርት ራሱን እያሳደገች ፣ ልጇን እያሳደገች እንዳለ እንሰማለን። ጠንክራ፣ በአካልም በመንፈስም ዝግጁ ሆና፣ የመፍትሄ ሐሳቦችን ይዛ ፣ በፊት ከነበራት ብስለት፣ ወኔ፣ ጥበብ ሁለት ሶስት እጥፍ ጨምራ ብትመጣ ምንም ጥርጥር የለኝም የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ፈረንሳዮች ጆን ኦፍ አርክን እንደተከተሉ ይከተላት ነበር።

የብርቱካን ሚደቅሳ ፖለቲካ የፍቅር፣ የአንድነት የዘመነ ፖለቲካ ነው። ለአገራችን ብቻ ሳይሆን ለአፈሪካም ሁሉ የሚያስፈልገው ይሄው ነው።

ብርቱካን ወደ ፖለቲካው ትመለሳለች ወይ ለሚለው በርግጠኝነት መልሴ አዎን ነው ። ለምን “እየተማራች እንደሆነ፣ አገሯንና ሕዝቧ እንደምታገለግል” ሃረቫርድ ተማሪ የነበረች ጊዘ ነገራኝም ስለነበረ። ሌላው ትልቁ ጥያቄ “መቼ ነው የምትመለሰው ? ” የሚለው ነው። ያንን ደግሞ እርሷ በሂደት የምትወስነው ይሆናል።

Related stories   አለቃ አጽመ ጊዮርጊስ – የተሳሳተውን የውጫሌ ውል የመረመሩ ጀግና ኢትዮጵያዊ

ሆኖም ግን ተያይዞ ሌላ ጥያቄ መጠየቅ አለበት ባይ ነኝ። “ለብርቱካን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የኢትዮጵያዊነት ፖለቲካ ኢትዮጵያዉያን ልባችን የተከፈተ ነው ወይ ?” የሚለው ነው። ምን አልባት ብርቱካን ዳር ይዛ የቆመችው፣ እርሷ የምታምንበት የፍቅር ፖለቲካን ማራመድ በኢትዮጵያ ውስጥ አስቸጋሪ ሆኖ ተሰምቷውትም ይሆናል። አሁን ሁሉም ነገር ትግሬ፣አማራ፣ ኦሮሞ በሚባለበትና የዘር ፖለቲክ በከረረበት ወቅት፣ በሰው ውስጥ እልህና bitterness በጨመረበት ወቅት የፍቅርን እና የአንድነትን ፖለቲካ የሚያራግቡ የሚተርፋቸው ስድብና ዉግዘት በሆነበት ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አስቸጋሪ ነው የሚሆነው።

ሌላ ደግሞ የፖለቲክ ክህደቱ ፣ “ከማን ጋር ነ የምንታጋለው?” የሚያስብል ነው። ብዙ አሉ ለጥቅምና ለገንዘብ ብለው ወደ ፖለቲካው የሚጠጉ። ለጥቅም ብለው የፓርቲያቸውን የአገርንና የሕዝብ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ። “ከሃላፊነታችን ከተነሳን፣ ሌሎች ስራዉን እስከሰሩ ድረስ ችግር የለዉም” የማይሉ፣ ከሃላፊነታቸው በመነሳታቸው “ጥቅም ይቀርብናል፡፤ ለምን መሪ አልሆንም” ብለው የሚካሰሱ፣ በጎን አንጃ የሚፈጥሩ፣ ፓርቲን የሚከፍሉ የሚረብሹ የፖለቲካ ወሮበሎች ብዙ ናቸው። ይሄን=ም አንዳንዴ ትሩ ሰዎችን የሚያርቅ ነው።

Related stories   ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

ለማንኛውም ግን እንደዚያም ቢሆን፣ ጥሩ ሰው መቼ ቢሆን ተስፋ ቆርጦ ዝም ማለት የለንበትም። ለወሮበላውናለጫርበርባሪው መጫወቻና መቀለጃ የሚኮነው እኮ integrity ያላቸው ጥሩ ሰዎች ፖለቲካው በመሸሻቸው ነው።

እህት ብርቱካን የፍቅር ፖለቲካዋን ይዛ ትመጣ ዘንድ አበረታታለሁ። ከመጣች ሌላው ቢቀር እኔ ብቻዬን እከተላታለሁ። አንድ፣ ሁለት እያልን ፍቅርንም አንድነትን ኢትዮጵያዊነትን እየሰበክን፣ አገራችንን ለማዳን የድርሻችንን እንወጣለን።

# ግርማ_ካሳ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *