ከመርህና ማኒፌስቶ ማስረጃ፣ ከነባር አባላት ምስክርነት፣ በውል ከተመሰረተው ፌደራሊዝም፣ ከአንቀጽ 39 ጋር ሞቼ ልገኝ፣ ከሚሉትና መስለ አመላካች እወነታዎች በመነሳት ” ውሳኔው የትግራይ ሕዝብ አይደለም፤ ከሆነ ደግ” በሚል ዓመታትን የቆጠሩ መልስ እያገኙ ይመስላል። ቀደም ሲል የተሰጠው የ40 እና የ50 ዓመት የመደራጃ ጊዜ ቢሆንም አሁን ከየአቅጣጫው የገነፈለው የዘር ፖለቲካ ቀውስ ጊዜውን ያሳጠረው ይመስላል።

ይኸው ሲባል የኖረው ጉዳይ ዛሬ በዝግ ተመክሮበት ሕዝብ የመገንጠል ውሳኔውን እንዲቀበል ውስጥ ውስጡን እየተሰራ መሆኑን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ወገኖች በተለያዩ ማህበራዊ ገጾች ይፋ አድርገውታል። ከየትኛውም ኦፊሳል የድርጀት ሚዲያ በሚታወቁ ክፍሎች የታጀበ መረጃ ባይቀርብም በቅርቡ የተካሄደው የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይህ የመገንጠል ጉዳይ ” አንቀጽ 39ን ተግባራዊ እናድርግ” በሚል መነሳቱን አስገደ ተናገረዋል።

የኤርትራው መሪ ኢሳያስ ተጀንጅነው፣ የኤርትራ ሕዝብ ምልጃ ቀርቦለት ከትግራይ ጋር በመቀላቅል አንድ ታላቅ አገር በአፍሪቃ ቀንድ ለማደራጀት ነው ሃሳቡ። አቶ አሰገድ አሁን ባይሉትም ” ታላቅ ነበርን ታላቅ እንሆናለን” የሚለው የእነ መለስ መፈክር ሲተገበር ኢትዮጵያ ትፈርሳለች። ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይባላል። ኦሮሞና አማራ፣ ደቡብና ኦሮሞ፣ ኦሮሞና አፋሩ፣ ጋምቤላና አማራ፣ ቤኒሻንጉልና አማራ… እርስ በእርስ ሲጨፋጨፉ፤ አዲስ የምትመሰረተው ” ታላቋ አገር” የሌሎቹ ሲቃ ሙዚቃ ይሆንላታል። ሌሎች ሲሞሻለቁ አዲሷ አገር በሃሴት ትሰክራለች… ይህ ህልምም ሆነ የገሃድ ምኞት ሕዝብ የሚፈርደው ጉዳይ ይሆናል።

Related stories   ሰበር ዜና – ትህነግ በዲፕሎማሲ ዘመቻ ቀውስ ገጠመው፤ “ በሃሰት መረጃ አሳፈራችሁን ” የቅርብ አጋሮቻቸው

አንድ የፌስ ቡክ አምደኛ አስተያየት ሲሰጡ ” እኔን አይድርገኝ ቅጥረኞች” አሉ። እስካሁን በሜውጡ መረጃዎች የአጋር ድርጅቶች መጨረሻ አልታወቀም። የአቶ ሃይለማሪያም መድረሻም ይፋ አልሆነም። ለመገመትም አይሞከርም። ተቃዋሚ የሚባሉት አሁን ድረስ በጨነገፈ አመለካከታቸው እየዳከሩ ነው። ጨልማ በዋጠው አስተሳሰብ ተነክረው እርስ በእርስ እየተባሉ ነው። ደግነቱ ህዝቡ ከእነሱ የተሻለ ያስባልና ኢትዮጵያ የተደገሰላት ሁሉ አይደርስባትም። የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል። አምላክ ያያል። ምንም የማያውቁ ምስኪኖችን እርስ በርስ አናክሶ፣ እኔ እስክጠግብና ጊዜዬ እስኪደርስ ካልመራውህ በሎ አገርን ለማፍረስ ማሴር አንድ ቀን እውነት የሚገባቸው ተውልዶች ዋጋ ይጠይቁበታል። አሁንም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ መሃሪ ነውና ሰክኖ ለማሰብ ጊዜ አለ!! አስገደ ይህንን ጽሁፍ አሰራጭተዋል።

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

አስገደ ገብረስላሴ የቀድሞው የህወሀት አመራር

በሰሜኑ ክፍለሀገራችን እየተናፈሱ ያሉ በጠባብነት መርዝ የተነከሩ መረጃዎች አየሩን እየበከሉት ይገኛሉ ። በኣሁኑ ጊዜ ቀደም ሲል ኢሳያስ አፉወርቅ ካሁን በፊት ያልነበረው መለሳለስ እያሳየ ነው።” ከኣፍሪካ ቀንድ ካሉት ጎረቤት መንግስታት እና ሀገራት የነበረንን ሸካራ ግንኝነት በመሻሻል እንታረቃለን” ብሎ ሲናገር ተደምጧል ።

ኣሁን በቅርብ ደግሞ ከትግራይ ክልል የሚናፈሱ ያሉ አስደንጋጭ ወሬዎች ድሮውንም ቡዙ ሊሂቃን ዜጎች እንዲሁም የአገር ኣንድነት ወዳድ ህዝቦች በስጋት ይመለከቱት የነበረ ፣ ኣሁን ያተደብቆ የነበረ ኣገር በታኝ ጠባብነት ወደ በተግባር ለመፈጸም ፣ በኣንድ አንድ ፍጡራን ተብዬዎች ኣንቀጽ 39 ህገመንግስት መብታችን ፣ በመጠቀም ተገንጥለን ከኤርትራ ኣንድ በመሆን ጠንካራ የሰሜን ሃይል መሆን ኣይሻለንም ወይ በማለት መንደር ለመንደር እየተሽለኮለኩ መርዛቸውን እየረጩ ይገኛሉ ።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

በሌላ በኩል ተጀምሮ ተቋጭቶ ሳያልቅ ተንሳፍፎ የሚገኘው የህውሓት ማእከላይ ኮሚቴ ስብሰባም የኣንቀጽ 39 የመተግበር ጉዳይ ተነስቶ ኣጨቃጫቂ በመሆኑ በልዩነት እንደተበተኑ ከፕላኔት የተናፈሱ ምንጮች ይጠቁማሉ ። ይህ ኣደገኛ የሃገር ሉዓላውነታችን በመበታተን የባንዳዎች ተልእኮ ለመፈጸም የሚንቀሳቀሰው ያለው ቡዱን ኣመንጩ ማነው ለማለት ባይቻልም ፣ ሃቁ ግን ወላጆቻችን እንደዚህ ኣይነት ሲነገር ምንጩ ምንድነው ሲሉዋቸው እባካቹ ተውን ነገገሩ ስም ይወጣል ከቤት ይቀበላል ጎረቤት ይላሉ ።

ኣሁንም እንደዚሁ ነው ነገሮች በደፈናው ። በመሆኑ የኢትዮጱያ ህዝቦች ሙሁራኖች ይህ የጠባብነት ማእበል በንቃት መመልከቱ ። በተለይ የትግራይ ህዝብና ምሁራን ወላጆቻችን ከጥንት ጀምረው ለሁሉም ኢትዮጱያዊ ወንድሞቹ ግንባር ቀደምት ተሰልፎው የቀይባህርን ወራሪዎች በማንበርከክና መንኮታኮት ዘንት እለት እመከቱዋቸው ና እያጠቋቸው እንደመጡ ሁሉ ኣሁንም በባንዳዎች ሳንታለል ተጠንቅቀን ዘብ አንቁም !!!!!!!!!!! ከኣስገደ ገብረስላሴ ከመቀለ 11../02 / 2010

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *