ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ድባብ አሳስቦናል አሉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ድባብ እንዳሳሰባቸውና አለመቻቻልና ከፋፋይ ፖለቲካ እየተባባሰ መምጣቱ ለሀገሪቱ አደጋ ነው አሉ።

ባራክ ኦባማና ጆርጅ ቡሽ የወቅቱን ፕሬዝዳንት ስም ሳይጠቅሱ አሁን ያለው አስተዳደር እየፈጠረ ያለው የከፋፋይና የማስፈራራት ፖለቲካ በሀገሪቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል። ባራክ ኦባማና ጆርጅ ቡሽ በተለያየ ወቅት በተለያየ መድረክ ላይ ስለወቅቱ የሀገራቸው ጉዳይ ንግግር አድርገዋል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ንግግር ባደረጉበት ወቅትም የፕሬዝዳንት ትራምፕን ስም ባይጠቅሱም አስተዳደሩ እየፈጠረ ያለው የከፋፋይና የማስፈራራት ፖለቲካ በሀገሪቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የዶናልድ ትራምፕን ስም ሳይጠቅሱ ሀገሪቱ እየተመራች ያለችበትን አካሄድ ነቅፈዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች በዘልማድ ተከታዮቻቸውን ከመንቀፍ የሚቆጠቡ ቢሆንም ባራክ ኦባማ የረጅም ጊዜ ዝምታቸውን በመስበር ንግግር አድርገዋል።

ኦባማ በተለይ የትራምፕ አስተዳደር ኦባማ ኬር በመባል የሚታወቀውን ብሎም በእሳቸው የአስተዳደር ዘመን የጸደቀውንና አሜሪካኖች ክፍያው ተመጣጣኝ የሆነ የጤና ኢንሹራንስ እንዲያገኙ የሚያደርገውን ሕግ ለመሻር መንቀሳቀሳቸውን ነቅፈዋል። እንዲሁም ከሙስሊም ሀገራት ወደ አሜሪካ በሚመጡ ተጓዞች ላይ የጣሉት ማዕቀብን አስመልክተው ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

አሜሪካኖች የመከፋፈልና የፍራቻ ፖለቲካን እንደማንቀበልና እንደምንቃወምም ለአለም በግልጽ ማሳወቅ ይገባናል ሲሉ ኒውጀርሲ ውስጥ በምትገኘው ኒው ዋርክ ከተማ ውስጥ በተካሄደ የዲሞክራቲክ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

አክለውም ለዘመናት የቆየና ያረጀ ከፋፋይ ፖለቲካ አሁን መልሶ ሲመጣ ልንቀበለው አይገባም ብለዋል። ከ50 አመት በፊት መፍትሄ የተሰጠው የከፋፋይ ፖለቲካ አካሄድን መልሶ ለማምጣት እየተሞከረ ነው።- አሁን ግን 21ኛው ክፍለ ዘመን እንጂ 19ኛው ክፍለ ዘመን አይደለም ብለዋል።

ከባራክ ኦባማ ቀደም ብለው በኒዮርክ በሌላ መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት ጆርጅ ቡሽ ግትርነትና የሌላውን የተለየ የፖለቲካ እምነትና አመለካከት ያለመቀበል ባህል እየተስፋፋ መምጣቱንና ፖለቲካችን ለፈጠራ ወሬዎች፣ለሴራና አሻጥር እየተጋለጠ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መቻቻል፣ልዩነትን መቀበልና መግባባት ለዘመናት በአሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ዋጋ የምንሰጠው ሕሴታችን ነው ሲሉ መናገራቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

Ethiopia seeking foreign wheat

Ethiopia recently announced a tender for 400,000 tonnes of milling wheat for use in humanitarian assistance programs throughout the country. Bids are due Oct. 24, with delivery expected by February 2018, according to an Oct. 13 Global Agricultural Information Network (GAIN) report filed by the Foreign Agricultural Service of the U.S. Department of Agriculture (USDA).

The USDA indicated that the tendered amount will be divided into three tranches, totaling 200,000 tonnes, 125,000 tonnes and 75,000 tonnes.

The primary source for the wheat is expected to be the Black Sea region, the USDA said, noting that the region “is generally one of the least expensive options.”

“With the exception of food aid, nearly all wheat coming into the country in 2016 came from the Black Sea region, with Romania, Ukraine and Russia as the top three suppliers,” the USDA said.

As of early September, Ethiopia had imported nearly 630,000 tonnes of milling wheat in 2017, the USDA said. The total included approximately 120,000 tonnes of U.S. wheat food aid, valued at about $23 million.

In August, the government of Ethiopia tendered for 70,000 tonnes of wheat to be used in the country’s productive safety net project. Earlier in the year the government awarded contracts to three international grain suppliers to deliver 400,000 tonnes of milling wheat for the country’s subsidized bread production program, the USDA said.

world-grain

44 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተያዘ  FBC

የምንዛሪ መጠኑ ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተያዘየምንዛሪ መጠኑ ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል መያዙን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስቶ በሀረር ባቢሌ መግቢያ ቶጎ ጫሌ ኬላ አካባቢ ድምሩ 1 ሚሊየን 625 ሺህ 100 የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተይዟል፡፡

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

ዶላሩ ከሃረር ከተማ በሚኒባስ ሲጓጓዝ የነበረ ሲሆን፥ ከሃረር እስከ ቶጎ ጫሌ ድረስ በተለምዶ ኮስትር ተብሎ በሚጠራው ተሽከርካሪ ከተጓጓዘ በኋላ በህብረተሰቡ ጥቆማ ቶጎ ጫሌ ኬላ ላይ ተይዟል፡፡  ተጠርጣሪዎቹም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን፥ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የትምህርት እና ኮሙዩኒኬሽን ቡድን አስተባባሪ አቶ ፍስሃ አብርሃም ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም 580 ሺህ 509 የሳዑዲ ሪያል፣ 32 ሺህ 750 የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ገንዘብ፣ 1 ሺህ 851 የኳታር ገንዘብ እንዲሁም በተጨማሪነት 31 ሺህ 164 የአሜሪካ ዶላር ቶጎ ጫሌ ኬላ ላይ መያዙንም ጠቅሰዋል።

ብአዴን የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ ማካሄድ ጀመረ FBC

ብሔረ አማራ ዴሞከራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ከክልል ውጪ በከፍተኛና መካከለኛ ኮር አመራሮች የጥልቅ ተሃድሶ አፈጻጸም ግምገማና በ2010 ዓ.ም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ። የድርጅቱን ጥልቅ ተሃድሶ አፈጻጻም በሚያሳየው ሰነድ ላይ ትናንት የቡድን ውይይት የተካሔደ ሲሆን፥ ዛሬ የተጀመረው የጋራ ጉባኤ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2010 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

በቡድን ውይይቱ ወቅት ከተሳታፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች ላይም ውይይት ተደርጓል። በድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ይህ ጉባኤ ከጥልቅ ተሃድሶው በኋላ በታዩ ለውጦችና ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ መፍትሄ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የድርጅቱን የ2010 ዓ.ም ቀጣይ አቅጣጫዎች አስመልክቶም ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል። በጉባዔው ከአማራ ክልል ውጪ ያሉና ከሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች የመጡ አንድ ሺህ የሚሆኑ የድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ ኮር አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የጋራ ጉባዔው ዛሬ ሲከፈት በትግሉ የተሰው ሰማዕታት በህሊና ጸሎት ታስበዋል።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ዳሽን ቢራ ፋብሪካ በጎንደር ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ህብረተሰቡ እንዳይካፈል ተጠየቀ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) በፋሲል ከነማ የክለብ አርማ ስም ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ጃኖ የሚል ቢራ ለማስተዋወቅ ነገ በጎንደር ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ህብረተሰቡ እንዳይካፈል የአካባቢው ወጣቶች አስጠነቀቁ።

ባላገሩ በሚል ይዞ የመጣው ቢራ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለኪሳራ የተዳረገው ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አሁን ደግሞ ጃኖ በሚል አዲስ ቢራ ለማስተዋወቅ መዘጋጀቱ ከንቱ ሙከራ ነው ሲሉ ወጣቶቹ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። ኮንሰርቱ የኦሮሞ ወገኖቻችን እየተገደሉ ባሉበት መዘጋጀቱና ከጃኖ ቢራ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ የጦር መሳሪያ እንዲገዛም አንፈቅድም ብለዋል የጎንደር ወጣቶች።

ከዳሽን ቢራ የሚገኝ ብር ለገዳዮቻችን የጥይት መግዣ እንዲሆን አንፈቅድም በሚል የጎንደር ወጣቶች ጃኖ በሚል ቢራ ስም የተዘጋጀውን ኮንሰርት ተቃውመዋል። ይህ አዲሱ ጃኖ ቢራ ባላገሩ በሚል ሊሸጥ ታስቦ የነበረው ምርት በባህርዳር ወጣቶች ከከሸፈ በኋላ ሕዝብን ለማታለል የተፈጠረ መሆኑን ወጣቶቹ ይናገራሉ።

ጃኖ ቢራን ሆን ብሎ በሕዝብ ዘንድ ከሚወደደው ፋሲል ከነማ ጋር ለማስተሳሰር መሞከሩም አገዛዙ ምን ያህል መሰሪና አጭበርባሪ መሆኑን ያሳያል ሲሉ ወጣቶቹ ተናግረዋል። በዚሁ ቢራ ስም ነገ መስከረም 11/2010 የተዘጋጀውን የሙዚቃ ኮንሰርትም ተቃውመዋል።

በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ወገኖቻችን በሕወሃት አጋዚ ሃይሎች እየተገደሉ ባሉበት ጊዜም የሙዚቃ ኮንሰርት በጎንደር መዘጋጀቱንም አጥብቀን እንቃወማለን ነው ያሉት። እናም የጎንደርና የአካባቢው ሕዝብ በኮንሰርቱ እንዳይሳተፍ ወጣቶቹ ጥሪ አቅርበዋል። በኮንሰርቱ ለመሳተፍ በሕወሃት አባላት የሚታገዙ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ነን የሚሉ ሁሉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ወጣቶቹ አስጠንቅቀዋል።

በኮንሰርቱ 3 ወጣት ድምጻውያን ዝግጅታቸውን እንደሚያቀርቡ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የማስታወቂያ ፖስተር ይገልጻል። እነሱም ያሬድ ደጉ፣ሳሚ ደንና ብስራት ሱራፌል የተባሉ ሙዚቀኞች ናቸው። ወጣቶቹ በሕዝብ ደም ላይ ለመዝፈን ያቀዱትን ሙዚቀኞች በመቃወም ሕብረተሰቡ በኮንሰርቱ እንዳይሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

 

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *