ለኢትዮጵያ ኳስ ሰው ቡድን ለይቶ ሲጫረስ ማየትና መስማት ያሳፍራል። ሚዲያውም ደርቢ ምናምን እያለ እያራገበ ኳሱ ካለበት ደረጃ በላይ ሙቀት ሲሰጠው መስማትም ያማል። በኢትዮጵያ ኳሱ ብቻ ሳይሆነ ፣ ሚዲያውም፣ ባለሙያውም ሁሉም የከሸፉ መሆናቸው ሃዘኑን ድርብ ያደርገዋል።

የኢትዮጵያ ቡድን አፍሪካ ዋናጫ አለፈ በሎ የሚያራግብ ሚዲያ ከተራው የኳስ ተመልካች በምን ይሻላል? እንደ እወነቱ ቢሆን ኖሮ ሚዲያው ማለት የነበረበት ” በድንገት ነውና ያለፍነው ካፍን ይቅርታ ጠይቀን ከውድድሩ እንውጣ ” ነበር። የአፍሪካው ሳያንሰን ዓለም ዋንጫ ለመግባት ቋፍ ላይ ነን በሚል ስብከቱ ተጋጋለ። አፍሪካ ዋንጫ የሄደው ቡድን እንኳን መጫወት በአግባቡ ጥፋት መስራት የማይችል፣ ዳኛ እየከበቡ ዱላ የሚቃጣቸው፣ ” ከየት ነው የመጡት” እስኪባል አሳፍረውን ውድድሩ አለቀ።

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

ይህንን ቡድን ይዘን ዓለም ዋንጫ ለመግባት ነጥብ የሚያሰላ “ሙያተኛ” ያስገርማል። አንዱ የፌስ ቡክ አልጋጭ ” ዓለም ዋንጫ ያለማጣሪያ ግቡ ብንባል እንኳን፣ ለምነን አቅማችን አይፈቅድም ማለት ነው የሚገባን” ማለቱን አስታውሳለሁ። እገረመንገዱን ይህን አልን እንጂ ዛሬ አዲስ አበባ የታየው አስነዋሪና ትርጉም የለሽ መጫረስ አሳፋሪና አሳዛኝ መሆኑንን ለማመላከት ነው።

አሁን ጊዮርጊስ አሸነፈ፣ ቡና እርስ በርስ መዘናጠልን ምን ዓመጣው? አብዛኛውን ጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም የዳኝነት መወላገድ፣ አንድን ክለብ መጥቀም፣ መጥቀም ብቻ ሳይሆን አመራሩ ሳይቀር የአንድ ከለብ አጎብዳጅ ሲሆን ማየት የተለመደና በርካታ መረጃዎች ያሉት እውነት ነው። በርካታ ፍርደ ገምድልነት ስንታዘብ ነው የኖርነው። ከዚያም በላይ ” ለምን” የሚሉ የክለብ አመራሮችን መፈረጅ፣ ማስፈረጅ፣ የፖለቲካው ሰለባ ለማስደረግ መሯሯጥና ብር መርጨትም ነበር። የዚህ ሰለባ ሆነው የተሸማቀቁ አሉ። አንድ ቀን ጊዜ እስኪገልጠው መታገስ ነው።  የዛሬው መነሻው ምን እንደሆነ በውል ባይገለጽም በምስል እንደታየው የደረሰው ጉዳት ያማል።  በባዶ ኳስ መጫረስ!!

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ፎቶ ኢትዮ ዴይሊ ፖስት

Image may contain: 3 people, people standing

Image may contain: one or more people

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *