በኢሉባቦር በቡኖ በደሌ ዞን በጮራ እና ዴጋ ወረዳ ሰሞኑን በተካሄደ ዓመጽ የ11ሰው ህይወት መጥፋቱን አቶ አዲሱ አረጋ የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር መገናኛ ቢሮ ሃላፊ ዛሬ ይፋ ያደረጉ ሲሆን ከማቾቹ ውስጥ 8ቱ የኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸውንና 3ቱ ደግሞ የአማራ ተወላጆች መሆናቸውን ገልጸው ድርጊቱ የአማራን እና ኦሮሞን አንድነት ለማሻከር በሚፈልግ ሃይል ነው ሲሉ በጽኑ ኮንነዋል።

በቡኖ በደሌ ዞን በተጠቀሱት ወረዳዎች ውስጥ በተካሄደ ዓመጽ ነዋሪዎች በቃንቃቸው እየተለዩ የተጠቁበት ክስተት መፈጠሩን ለማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ያጠናቀርነውን ዘገባ እንደሚከተለው አቅርበናል።

**በቡኖ በደሌ የተፈጠረው ምንድነው?

በቡኖ በደሌ ዞን በጮራ እና ዴጋ ወረዳ ባገባደደነው ሳምንት መጨረሻ ላይ አስተባባሪው ያልታወቀ ህዝባዊ ሰልፍ መካሄዱን አቶ አዲሱ አረጋ ይናገራሉ።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹም ባልታወቀ ምክንያት እና መሪነት በአካባቢው ነዋሪ በሆኑና እና የኦሮሞ ተወላጅ ባልሆኑት ላይ የዘረፋና የግድያ ተግባራት እንደተፈጸሙ በሀዘን የሚናገሩት አቶ አዲሱ አረጋ “ኦህዴድ በአሁኑ ሰዓት እያካሄደ ባለው ተሃድሶ ወሳኝ የሆኑ እርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት ወቅት ጥቅማችን ተነክታል የሚሉ ወገኖች ይህን የድርጅታችንን ማጠናከሪያ ተግባር በስኬታማነት እንዳንወጣ በህዝቦች መካከል ደም መፋሰስና መጋጨት እንዲነሳ አጥብቆ እየሰራ ያለ ድብቅ ሃይል ስራ ነው” በመለት ሲገልጹ የዚህን ድብቅ ሃይል ማንነት ግን ሳይገልጹ አልፈውታል።

Related stories   እንግሊዝ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እቅዷን ይፋ አደረገች፤ ዶክተር ዳንኤል የማይካድራን ጂኖሳይድ ዝም ማለቱ ክህደት ነው

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ11 እንደሚበልጥ የሚጠቁሙ መረጃዎችንም ማግኘት ቢቻልም ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጫ ስላልተገኘለት ከመጠቀም ተቆጥበናል።

ሆኖም በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን በመተው ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲሉ በየፖሊስ ጣቢያና በየእምነት ተቃማቱ ተጥልለው እንዳሉ ቢቢሲ የአካባቢውን ባለስልጣን ዋቢ ጠቅሶ ዘግባል።

የወረዳውን ፖሊስ ጣቢያ ምክትል ኮማንደር ሳጂን ኢተፋ መዝገቡን ቃል ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው ማቾቹ የአማራና ኦሮሞ ተወላጆች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን የትግራይ ተወላጆችም ሰለባ ሆነዋል የተባለውን መረጃ ግን እሰከ አሁን በተጨባጭ የተገኘ ማስረጃ አልተገኘም ሲል ዘግባል።
ረብሻው በሰላማዊ ሰልፈኛው ውስጥ በተነሳ ረብሻና ሁከት ምክንያት ወደ ንብረት ዘረፋ በመሸጋገሩ በመካከሉ ንብረታቸውን ከዘራፊዎች ለመከላከልና ብሎም ለመዘረፍ በሄዱ ሰዎች መካከል በተከፈተ ተኩስ የአብዛኛው ሰለባ ህይወት ሊጠፋ ችላል ሲሉ የቡኖ በደሌ ዞን የጸጥታና አስተዳደር ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ተመስገን አያና መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግባል።

በአቶ አዲሱ በኩል ክስተቱ በአካባቢው ለዘመናት ተከባብሮና ተሳስቦ ሲኖር በነበረ ወንድማማች በሆነው የኦሮሞና አማራ ህዝብ መካከል ሴራ ሲሸርቡና ተንኮል ሲያቀነባብሩ በቆዩ የሁለቱ ህዝቦች አንድነትና ህብረት ያልተደሰቱ ሃይሎች እርምጃ ነው ሲሉ የገለጹት ሲሆን በድርጊቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ልባዊ ሀዘናቸውን ገልጸው ግጭቱ የአማራን እና ኦሮሞን አንድነት እና ህብረት እንዲያበላሽ አንፈቅድም ሲሉ ይገልጻሉ።
ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየፖሊስ ጣቢያው የተጠለሉ የአማራ ተወላጆች ቁጥርም በሞቶ የሚቆጠር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን እሁድ ማምሻው ላይ ንብረትነቱ የህወሃት እንደሆነ የሚነገርለት ENN የቴሌቪዢን ጣቢያ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ የነበረውን የእግር ካስ ጨዋታን በማቃረጥ በሰበር ዜና አቀረራብ በቡኖ በደሌ በኦሮሞና አማራ መካከል ጦርነት እየተካሄደ ነው በሚል ማሰራጨቱ ከሁሉም በላይ በግጭቱ የህወሃት መራሹን መንግስት እጅ እንዳለበት ያረጋገጠ ማስረጃ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተናግራዋል።

Related stories   የኮሚሽነር አበረ ህልፈት "በነጋዴዎች" እይታና ፤ የሃኪም ትክክለኛው መረጃ " ቸልተኛነት አይተናል"

በተለይም ይላሉ ታዛቢዎች “በተለይም ግጭቱ የህወሃት ፍላጎትና እጅ እንዳለበት የሚያረጋግጠው ሆን ብለውና ተዘጋጅተውበት ብዙ ተመልካች አትኩሮቱን በቴሌቪዢን ላይ በሚያደርግበት የእግር ካስ ፕሮግራም ላይ እንደ አዲስ ክስተት በቀጥታ ስርጭት ሰበር ዜና ብለው ማቅረባቸው ሁለቱ ህዝቦች እርሰበርስ እንዲፋጁ ካላቸው ዓላማና ተግባራቸው አንጻር ነው” ሲሉ ይናገራሉ።

በሳምንቱ መጨረሻ አካባቢ የተፈጸመን ጥቃት ግዜ ጠብቆ እሁድ በእግር ካስ ፕሮግራም ላይ ስርጭቱን በማቃረጥ ሰበር ዜና ብሎ የሁለቱን ህዝቦች እርሰበርስ እየተጨፋጨፉ ናቸው ብሎ ሃላፊነት በጎደለው መልኩ ማቅረብ ዓላማ ይዘው ካልሆነ እንደመንግስት ፈጽሞ ሊፈጸም የማይገባ ነበር ሲሉ ታዛቢዎች ይከራከራሉ።

Related stories   የኢትዮጵያ “ትንሣኤዋን እውነተኛ ልጆቿ እንጂ ጠላቶቿ ወዲያው አያዩትም” ተመስገን ትሩነህ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መግስት ይህንን ይህንን አስነዋሪ ድርጊት አጥብቆ ያወግዛል ያሉት አቶ አዲሱ አረጋ የህዝቦችን ወንድማማችነትን እና አንድነትን የሚጎዱ ማንኛቸውንም ድርጊቶች ዳግም እንዳይከሰት መስተዳድሩ ከእንግዲህ አጥቅብቆ ይሰራል ሲሉ ተናግራዋል።

በፖሊስ ጣቢያ ተጠልለው ካሉት ውስጥ “የእኛ ጠላትና ያስፈጀን ረዳት ኮሚችነር ደምላሽ ገብረመስቀል” የተባለ ትውልዱ በምእራብ ሸዋ ሆኖ ኦሮሚኛ ተናጋሪ የትግራይ ተወላጅና የአካባቢው የህወሃት ተወካይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሆኖም ይህንን የተጎጂዎቹን ጥቆማ የሚያጠናክር መረጃ ከአካባቢው ባለስልጣናት ዘንድ እስካሁን ያልተደመጠ ሲሆን የሰውዪው ቁልፍ ባለስልጣንነት እንዳያጋልጡት እንዳገዳቸው ነው ተጎጂዎቹ እየተናገሩ ያሉት።
የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ማሰማራቱን እና ጉዳዩም በቁጥጥር ስር እንደዋለ አቶ አዲሱ ተናግረዋል።

በወንድወሰን ተክሉ satenaw

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *