አንዛኞች ገና የሚወጣ ሌላም ጉድ አለ ባይ ናቸው። እያደር የሚገለጥ ጉዳይ ስለመኖሩም የቪዲዮው ትረካ ያመላክታል። በስደት ያሉ ወገኖችን ለማቀራረብ፣ ለማቀላቀል ታልሞ የሚደረገውን ውድድር የግል ቡቲካቸው ያደረጉ ሁሉም ሊያፍሩ ይገባል። ሰርቶ ማግኘት፣ አለያም በጡረታም ያለችግር በሚኖርበት አገር ውስጥ ተቀምጠው እንዲህ ያለውን ዘረፋ የሚያካሂዱትን በተመልከተ ሁሉም የሚያውቀውን ሊናገር ይገባል። ህግ ያለበት ዞን ውስጥ ነንና!!

 

በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት የቦርዱ አባላት ለተሰብሳቢዎቹ እንደተናገሩት በ2017 ፌዴሬሽኑ በጣልያን ሮማ በተካሄደው ፌስቲቫል ከተለያዩ ገቢዎች የሰበሰበው ገንዘብ አብሯቸው ይሰራ በነበረ ባልደረባቸው ተዘርፏል። በርካታ ኢትዮጵያውያን በፌስቲቫሉ የህወሃት/ኢህአዴግ እጅ ገብቶበታል በማለት ማእቀብ እንዲደረግ ሲወተውቱ እንደነበር ይታወሳል።

ከዚህ በታች በስብሰባው ላይ የተሳተፈ ግለሰብ ሁኔታውን በፌስቡክ ገጹ ላይ የገለጸውን እንዳለ አቅርበነዋል። (ቪዲዮውን ከጽሁፉ መጨረሻ ያገኙታል)

የቀበረ ያርዳ ! ያየ ይናገር !
ሀቁ ይሄ ነው !

ክፍል ፩

በአውሮፓ የኢትዮጵያን ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ቅዳሜ Oktober 14.2017 በአምስተርዳም (ሆላንድ) ከተማ ሙሉ ቀን የፈጀ ዓመታዊ ጠቅላላ የቦርድ ዓባሎች የተገኙበት ጉባኤ አካሂዷል ።

ማሳሰቢያ!

እዚህ የቪዲዎ ጥንቅር ላይ: በተለምዶ ብር እየተባለ የሚነገረው ኦይሮ € ለማለት ስለሆነ፣ ኦይሮ € ተብሎ ይደመጥ!

ይህ ከ 21 የተለያዩ ክለቦች 45 ዓባሎች የተካፈሉበት ስብሰባ ገና ሲጀመር አነጋጋሪ ሆኖ ነው
ምክንያቱም ሊቀ መንበሩ እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ እንደአልባሌ ወራዊ ስብሰባ አራት አጀንዳ አስይዞ ሊቀጥል ሲል አንድ የበርሊን ተወካይ ተነስቶ ይህ ትልቅ ዓመታዊ ያውም አዲስ ስራ አስኪያጅ የሚመረጥበት ጠቅላላ ስብሰባ ነው በመሆኑም ኢንተርናሽናል ደንቡን ተከትሎ በስርዓት መካሄድ አለበት ብሎ በዝርዝር :

ሀ: ሊቀመንበሩ ቤቱን ከፍቶ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ ቤቱን የሚመራ ፣ ፕሮቶኮል የሚጽፍ ፣ ምርጫውን የሚከታተል ሰው ካስመረጠ በኋላ መቀመጥ እንዳለበት ።
ለ: ቤቱን የሚመራው ሰው ቤቱ የሚያስይዘው አጀንዳ ካለ መጠየቅ እንዳለበት
ሐ: የስራ አስኪያጁ የ2016/17 የስራ ሪፖርት በደመጥ እንዳለበት
መ: የ 2016/17 የኦዲተር ሪፖርት መነበብ እንዳለበት
ሰ: የቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ቤቱ ተወያይቶ ፣ ተከራክሮ አጥጋቢ ከሆነ ብቻ ዓመራሩን መሰናበት እንዳለበት
ረ: የዓዲስ ሰራ አስኪያጅ ምርጫ እንደሚካሄድ
ሸ: ቀጣዩን የስፖርት አዘጋጅ አገሮች መምረጥ
ቀ: የመጭውን ስራ ውጥን ተመካክሮ ስብሰባውን ለፍፃሜ ማብቃት ብሎ በሰፊው ትምርታዊ ገለፃ ሰጠ

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

ይህ ሐሳብ በቤቱ ተሰሚነት ቢያገኝም ሊቀመንበሩ ገለጻው ትክክል ቢሆንም እስካሁን በልማድ ስለሆነ ስንሠራ የኖርነው በዚሁ እንቀጥል ብሎ
በፅሁፍ የቀረበ የስራ ሪፖርት ባለመዘጋጀቱ እንዲሁ በቤቱ ግፊት በቃል ብቻ ለትንሽ ደቂቃ እንደነገሩ የ2016/17 የስራና የሂሳብ ዘገባ ማብራሪያ ሊቀመንበሩ ሰጠ ።
በዚህ የገንዘብ ያዡ እንኳ በስብሰባው ያልተሳተፈበት አሰራርና ሙያተኛ ያጣ የስብሰባ ሂደት በተደነቀው የስብሰባ ተሳታፊ ሌላ ምርጫ ስለሌለው ስብሰባው በዚሁ መልክ ቀጠለ:

ሊቀመንበሩ በመቀጠል 2016 ዴን ሐግ ( ሆላንድ ) ላይ 70,000 € ከስረናል

2017 ሮም ( ጣሊያን ) ላይ ስለተዘረፍን ከስረናል ወዘተ,, ብሎ ቁጭ አለ ።

ከዛም ዋናው ኦዲተር አቶ ሲሞን ባለመኖሩ ረዳት ኦዲተሩ አቶ ተስፋዬ ተነስቶ ቤቱንና ከሥረናል ባይ አመራሩን ያስደነገጠ ለ 2017 ምንም ማስረጃ ስላልሰጣችሁን ምንም ኦዲት ያደረግነው ነገር የለም 2016 ትን በተመለከተ ግን እናንተው ከሰጣችሁን መረጃ በመነሳት እንኳን 70,000 € ልትከስሩ
2030 € ገደማ ትርፍ አላችሁ ብሎ በ EXCEL የሰራውን ማስረጃ በማቅረብ ቤቱን አናጋዉ ።

ዘገባው ትንሽ ካጨቃጨቀ በኋላ ስምምነት ስለጠፋ ሊቀመንበሩ ግድ የለም እኔና አንተ እናመሳክርና ሰርተን እናቀርባለን ሲል ቤቱ ውስጥ ሳቅ ሰፈነና የለም አንዱ ተጠያቂ አንተማ አጣሪ አትሆንም ተብሎ ቀድመው ከተመረጡት አቶ ሲሞንና አቶ ተስፋዬ በተጨማሪ ሁለት ገለልተኛ ኦዲተሮች አቶ ሮቤርቶ ከጣሊያንና አቶ ክንፈ ከሆላንድ ተመርጠው በቅርብ አጣርተው ለአዲሱ ዓመራር ( ቦርዱ ) እንዲያቀርቡ ተወሰነ።

Related stories   በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ ዶላር ተያዘ

ይህም ማለት በመቀጠል ነባሩ ስራአመራር የቀረቡት ሪፖርቶች ህጋዊ ተጠያቂነት እንዳለ ይቆያል ማለት ነው ።

ሌላው ታላቅ ድራማ የታየበት ፣ ያነታረከው ፣ ያጨቃጨቀው የ2017 የሮምን ዝግጅት በሚመለከት ከዝግጅቱ በኋላ ሆቴል ውስጥ ተዘርፈናል በሚሉት አቶ ዮሐንስ ፣ አቶ ግርማ ፣ አቶ ከበደ ፣ አቶ ኢብራሂምና ዘራፊ በተባሉት በአቶ አንድነትና (ቀዮ ) ፍራንሲስኮ ተወካይነት መካከል የተደረገው ሱሪ አውላቂ መገፋፈጥና መከዳዳት ትያትር ነው።

ይህ በቀኑ በተቀረፀው ቪዲዎ ላይ አይቶ መደነቅ እንጅ ጨርሶ በፅሁፍ ማስረዳት የማይቻለው የህዝብ ገንዘብ ዘረፋ ሴራ ከሽቱትጋርት የመጣው ተወካይ በከፍታ ድምፅ እንዳለው ” ተስማምተው ተማምለው በኛ ላይ የሚሰሩብን ድራማ እንጂ ሁሉም አብረው ነው የፌዴሬሽኑን ገንዘብ ባንድነት የዘርፉን ” ሲል አቶ አንድነት አዎ የትኬት 35,000 € እና የመጠጥ 9,000 € በጠቅላላ 44,000 € የቀብድ እንጂ ያልከፈልኳቸውን ዕዳ ለማወራረድ ይዘው ከመጥፋታቸው በፊት ወሰድኩ እንጅ እነሱ እንደሚሉት 60,000 € ወይም 100, 000 € ኦይሮ አልወሰድኩምብሎ ያወራረደበትን የራሱን የሂሳብ መረጃ ኮፒ ለተሰብሳቢው አከፋፍሎ ራሳቸው ናቸው ቀሪውን ገንዘብ የዴን ሀግ ዕዳ ምናምን እያሉ በየኪሳቸው ሲያጉሩ የነበሩት አለ ።

ይህ ሁኔታ ሁሉንም የዓመራር አባሎች በህይወታችን ላይ ነው የመጣው አስፈሪ ሁኔታ ነበር ከማለት ውጭ አንገት አስደፋ እንጂ የረባ መልስ አልተሰጠበትም ።
ለምን አልከሰሱም ? እስካሁንስ ለምን ሚስጢር አድርገው አቆዩት ?

” ሰውየው ለምሳ ሲያስቡን ቁርስ አደረግናቸው” እንዳለው አይነት ነው ነገሩ ብሎ ከማልጎምጎም በስተቀር መልስ ስላልተገኘለት ይኼም በነዛው ኦዲተሮች ተጣርቶ እንዲቀርብ በቤቱ ተወሰነ ።

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

ባጠቃላይ በዚህ ቀን የተወሰኑ ዋና ዋና ውሳኔወች

—ዓመራሩ በጥቂቶች ዕጅ ብቻ እንዳይሆን ቁጥራቸው ወደ 9 ከፍ እንዲል ።
—የሚቀጥሉት ሁለት ዝግጅቶች የዴንሀግንና የሮምን ውድቀት ፣ ክስረት በማስታወስ በፌዴሬሽኑ ሳይሆን በክለቦች እንዲዘጋጅ ።
—በሮም ላይ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ሲከወን እንደታየው እንዳይሆን ወደፊት በየትኛውም የፌዴሬሽን ዝግጅት ላይ ጫት ፣ ሺሻና ጠንካራ የአልኮል መጠጦች ሜዳ ላይ ፈፅሞ እንዳይሸጥ
—አስካሁን ለተደረጉት ጥፋቶች ተጠያቂው ያለፈው ስራ አስፈፃሚ አካል መሆኑን ።
—ካሁን በኃላ አዘጋጅ አገሮችን የሚመርጠው በየዓመቱ የሚሰበሰበው የቦርድ አባሎች እንጅ አመራሩ እንደማይሆን ።
እንዲሁም:
—የ 2018 አዘጋጅ ቡድን ኢትዮ ሽቱትጋርት
— የ 2019 አዘጋጅ ቡድን ኢትዮ ዙሪክ እንዲሆን

በመጨረሻም

በአቶ በላይነህ ፣ በአቶ ክንፈና አቶ ዳኜ መሪነትና አሰመራጭነት: በአቶ ካሱ ቆጣሪነት ከቀድሞ የዓመራር አባል አንድም ደግሞ ሳይመረጥ ከ 11 ተወዳዳሪወች 9 በላጭ ድምፅ ያገኙትን እነደሚከተለው ቤቱ መርጧል:

1: አቶ አሳየኸኝ ጥላሁን ኖርዌይ (ሊቀ መንበር)
2: አቶ ተስፋዬ አበበ ኮለን (ፀሐፊ )
3: አቶ ብርሃኑ ኃይሌ ስዊድን ( ገንዘብ ያዥ)
4: አቶ ሮቤርቶ ካንቲ ሮማ
5: አቶ መስፍን መንግስቱ ሽቱትጋርት
6: አቶ ቴዲ መላኩ ቤልጅየም
7: አቶ ፋሲል ሰለሞን ካታንጋ ለንደን
8: አቶ ዳንኤል ብስራት ስዊዝ
9: አቶ ነቢዩ ሰቆጣው ፍራንክፈርት

ተጠባባቂ: ወ/ት ማህሌት ጌታቸው ኮለን ናቸው ።

P.s
ይህን ጉባዔ ያስደነቀው ከውጭም ሆነ ከውስጥ ፌዴሬሽኑ በገጠመው ችግር ዙሪያ ይባሉ የነበሩት በሙሉ አሉባልታ ሳይሆኑ በሐቅ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው መረጋገጡ ነው ።

የታገለ ያሸንፋል !

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *