“የምርጫ 2002 የድምጽ መስጫ እለት ይቅርታ ይደረግልኝ በማለት በኢቲቪ ለመናገር እንደደፈሩት ዛሬም ደፈር ብለው ባለፈው የአንድነት ሊቀመንበርነት የሥልጣን ቆይታየ በንግግሬ ያስከፋኋችሁ በድርጊቴ ያስቀየምኳችሁ ይቅርታ ታደርጉልኝ ዘንድ በአዲሱ የአንድነት ሊቀመንበርነት ወንበሬ ላይ ሆኜ እጠይቃለሁ፡፡

በቅድሚያ ኢንጅነር ግዛቸው አለማለቴ መጠሪያ አይደለም ከሚል እምነት የዘለለ ምክንያት እንደሌለው ይታወቅልኝ፡፡ለዚህ ጽሁፍ አብይ መነሻ ምክንያቱ  የሀብታሙ አያሌው ቅጥፈትና የባዶ ቅል መንኳኳት የሚለው የአቶ ግዛቸው ጽሁፍ  ነው፡፡ የሀብታሙ Image result for habtamu ayalewአያሌውን መጽሀፍ አላገኘሁትም፡፡ በአቶ ግዛቸው ጽሁፉ አንደተገለጸው  የአቶ ሀብታሙ መጽሀፍ አንዲህ ከእውነት ይልቅ በስሜት ከማስረጃ ይልቅ በጥላቻ የተሞላ ከሆነ አለማግኘቴን እሰየው እላለሁ፡፡ ምክንያትም ምላሽ በመስጠት ያደክመኝ ነበርና፡፡

የአቶ ግዛቸውን ጽሁፍ አንብቤ ዝም ለማለት ያለመቻሌ ምክንያት 1- በስም ተጠቅሻለሁ 2-ሀብታሙን ዋሸህ ብለው ጻፉት አቶ ግዛቸው ራሳቸው የዋሹት የማውቀው ነገር አለ 3- ከዚሁ ጽሁፍ ውስጥ የሀብታሙ አያሌውን ከውሸት የዘዘለ ቅጥፈት ለማየት ችያለሁና ነው፡፡

ከዚህ በዘለለ ስለ ሁለቱም ማለት የሚቻል ብዙ ነገር ቢኖርም  የዚህ ጽሁፍ መነሻም ሆነ መድረሻ በአቶ ግዛቸው ጽሁፍ ላይ በተጠቀሱ ጉዳዮች ላይ ብቻ ይሆናል፡፡ ለመንደርደሪያ ግን አንድ ነገር ልበል፡፡ አንድነት የፈረሰው በዋናነት በወያኔ ሳይሆን በራሱ አባላት ነው፤ ወያኔ ያገኘውን ክፍተት ተጠቅሞ አሰፋው፣ እነርሱ በለኮሱት እሳት ላይ ቤኒዚን አርከፍክፎ አቀጣጠለው ኋላም እሳት አጥፊ መስሎ ቀርቦ ወደ ግብአት መሬት አወረደው ብዬ ደጋግሜ ስጽፍ እንዳንዶች አንድነትን ወይንም በውስጡ የነበሩ ሰዎችን ከመጥላት አድርገው ይገልጹ ነበር፤ አሁን ምን ይሉ ይሆን፤የራስን ችግርና ድክመት በወያኔ እያሳበቡ መሻሻል አይቻልም፡፡  ከስሜት ወጥቶ ከጀሌነት ተላቆ እውነትን ማየት ካልተቻለ በወቅቱ ማዳን የሚቻለው ነገር ሁሉ ከተበላሸና የማይመለስበት ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ዋይ ማለት ነው ትርፉ፡፡ ከሁለቱ ሰዎች ዛሬ የሚወረወረው የቃላት አረረር  አንድነትን ከሞት አይመልሰውም፣ ሁለቱም በወቅቱ ይጻፍ ይነገር የነበረውን ነገር ቢሰሙ ኖሮ ግን ቢያንሰ አንድነት ሳይሞት ከነበሽታው ለመኖር በቻለ ነበረ፡፡

ለዚህ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ ፤   የአቶ ግዛቸውን ዳግም ወደ አንድነት ሊቀመንበርነት መምጣት አስመልክቶ  አቶ ታምራት ታረቀኝ በኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ  ላይ የኢ/ር ግዛቸው የውህደት ህልም በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ  “በምርጫ 2002 የድምጽ መስጫ ዕለት ለማንም የማይረሳ ድርጊት የፈጸሙት ኢ/ር ግዛቸው በምርጫ 2007 ዋዜማ ተመልሰው መምጣታቸው ግን አጠራጣሪም አጠያያቂም ነው፡፡” በማለት አቶ ግዛቸው በአንድነት ሊቀንበርነታቸው ወቅት ፈጸሙዋቸው ያሉዋቸውን ነገሮች በሰፊው ይዘረዘሩና   ወደ ማጠቃላያቸው ላይ “የምርጫ 2002 የድምጽ መስጫ እለት ይቅርታ ይደረግልኝ በማለት በኢቲቪ ለመናገር እንደደፈሩት ዛሬም ደፈር ብለው ባለፈው የአንድነት ሊቀመንበርነት የሥልጣን ቆይታየ በንግግሬ ያስከፋኋችሁ በድርጊቴ ያስቀየምኳችሁ ይቅርታ ታደርጉልኝ ዘንድ በአዲሱ የአንድነት ሊቀመንበርነት ወንበሬ ላይ ሆኜ እጠይቃለሁ፡፡ ያለፈውን በይቅርታ እንለፈውና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት መወጣት ስላለበን የተናጠልና የጋራ ድርሻ እናስብ፣ በምርጫ 2007 አሸናፊ ስለምንሆንበት እንምከር ወዘተ የሚል ጥሪ ማስተላለፍ ቢችሉ አዲስ ምዕራፍ ከፈቱ፣ያለፈውን ሁሉ የሚያካክስ ተግባር ፈጸሙ ህልማቸውንም አሳኩ ማለት ነበር፡፡ ነበር ያሉት፡፡ ይህ ሲጻፍ ዛሬ የተለያየ ስም ሰጥቶ የጻፈባቸው ሀብታሙ አያሌው በእልልታ ነበር የተቀበላቸው፡፡ አንድውም በአንድ ሎሌያቸው አማካኝነት የአቶ ታምራት ታረቀኝ ሰካራሙ ብእር በሚል ርእስ ጸሀፊውን በማውገዝ ነበር ምልስ የተሰጠው፡፡

1-የአቶ ሀብታሙ አያሌው ቅጥፈት፤ አቶ ሀብታሙ የመናገር አንደበትን ከመንፈሳዊ ኮሌጅ፤ ቅጥፈትን ደግሞ ከወያኔ ዶቦስኮ የተማረ በሚመስል መልኩ ሁለቱን አቀናጅቶ ሲደሰኩርና ሲጽፍ መታበዩ አስተውሎትን ከልቶበት፣ ውሸቱን ሊያጋልጥበት ቅጥፈቱን አደባባይ ሊያወጣበት የሚችል ሰው ያለ እስከማይመስለው ባይደርስ ኖሮ እንዲህ ከብዙ አቅጣጫ ብእር ባልተመዘዘበት ቃላት ባልተወረወሩበት ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ በአቶ ግዛቸው ጽሁፍ ውስጥ በስም ሳይቀር የተጠቀሱ ሰዎችን ማስታወሱ በቂ ነው፡፡

ስለ እውነት መመስከር ፈጣሪ ያስብ ይወስንበት ህሊና የሰጠው ሰው ሁሉ ግዴታ ነው ብየ ስለማምን፤ ቅዱስ መጽሀፍም ስለ እውነት እናንተ ባትመሰክሩ ድንጋዮች አፍ አውጥተው ይመሰከራሉ ይላልና የማውቀውን ልግለጽ፡፡  በአቶ ግዛቸው ጽሁፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ከሀብታሙ አያሌው መጽሀፍ የተጠቀሰ ቃል አለ፡፡

ሀ-ፓርቲው በኢንጂነር ግዛቸው እጅ እንዳይወድቅ ብርቱ ትግል አድረገን ..ይሁን እንጂ ሰውዬው ብርቱ የሥልጣን ፍላጎት የነበረው በመሆኑ በላይ ፍቃዱ ከተወዳደረ አልወዳደርም ብሏል..ኢንጂነሩ በጎን ተክሌን አንዲለቅለት እየተማጸነ በግርማ ሰይፉ ላይ ከፍ ሲል በአማራ ስም ዝቅ ሲል በሸዋ ስም የሴራ ፖለቲካ እየጎነጎነ ወደ ፊት ገጹ መጣ፡፡ ( ሀብታሙ አያሌው ገጽ 254-455)

እኔ የማውቀው ፣ የአቶ ግዛቸውን ለሊቀመንበርነት መወዳደር አንደሰማን አቶ ሀብታሙ አያሌውን ወደ አንድነት በማስገባት ትልቁ ባለድርሻ አንደበረ የሚነገርለትንና ራሱም ይህን በማድረጉ አንደሚኮራ የሚገልለጸውንና በወቅቱ የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የነበረውን አቶ ጸጋዬን እንዴት ኢ/ር ግዛቸውን ታመጣላችሁ በማለት ግዛቸው ሰራቸው ያልናቸውን በደሎች በመዘርዘር ስንጠይቀው  የርሱ መልስ አማራጭ አልነበረንም የሚል ነበር፤ እንዴት ሰንለው አሁን በአለው ሁኔታ ለሊቀመንበርነት ሊቀርቡ የሚችሉት ተክሌ በቀለና ግርማ ሰይፉ ሲሆኑ ግርማ ማሸነፉ ርግጥ ነው አለን፡፡ አቶ ግርማ  በወቅቱ የፓርላማ አባልም ነበርና ታዲያ ምንድን ነው ችግሩ ቢመረጥ ሰንለው፣ እሱ ቢመረጥ በማግስቱ የፓርቲዎች ምክር ቤትን ፊርማ በመፈረም አንድነትን ወያኔ ጉያ  ያስገባዋል አለን፡፡ ጸጋዬ የበላይ በፈቃዱም የሀብታሙ አያሌውም  ወዳጅ አቶ ግዛቸው ወደ ሊቀመንበርነት አንዲመጣም ደጋፈም  የነበረ  ከመሆኑ አንጻር  መረዳት የሚቻለው ሀብታሙ አያሌው በመጽሀፉ ግዛቸውን የወቀሰበት አግባብ ትክክል እንዳልሆነ ነው፡፡በአጭሩ ተለምኖ የመጣንና በከፍተኛ ድምጽ አሸነፈ ተብሎ በራሱ በፓርቲው የተነገረለትን ሰው ፓርቲው እሱ እጅ አንዳይወድቅ ብር ትግል አደረግን ማለት አንዴት ይዛመዳል፡፡ ለመሆኑ ታገልን ሲል ሀብታሙ ከእነማን ጋር ሆኖ ነው፤ በመጽሀፉ ተገልጸው ይሆን፡፤

ለ- ኢኒጅር ግዛቸው በአንድነት ፓርቲ ቤት የሸዋ ፖለቲካ ጢባጢቤ ሲጀምር ኢኒጂነር ይልቃ ያለውን ሀይል ይዞ ደህና ሰንብት ያለው በጎጃምኛ ነበር ፡፡ ይህን ሳነብ የአቶ ሀብታሙን የአእምሮ ጤነኛነት ተጠራጠርኩት፡፡ ህመም ካልሆነ በስተቀር ድፍረት ብቻውን አንዲህ  አያናግርም፡፡በትንሹ ላስረዳ፤

  • አቶ ግዛቸው አንድነትን ለመበጥበጥ የበቁት በሸዋ ፖለቲካ እሳቤ ሳይሆን በብርቱካን ተሸንፈው ሊቀመንበርነቱን በማጣታቸው ነው፡፡
  • የውስጥ ተቃውሞ በጀመሩት አባላት መካከል ይልቃል አንድ አባል ከመሆን ያለፈ ምንም ሚና አልነበረውም፤
  • አቶ ሀብታሙ የማስተዋል ግርዶሹ ከፍቶ አንጂ እነ ፕ/ር መስፍን ወልደ ማሪያም እነ ዶ/ር ሽመለስ እነ አቶ አምሀ ዳኘው እነ አቶ ታምራት ታረቀኝ ወዘተ የዚህ ተቃውሞ አካል ነበሩ፡፤
  • መቼም እነርሱ ከአንድነት የወጡት ይልቃልን በጎጃምኛ እስክስታ እያጀቡት ነው ብሎ ለመናር የሚደፍር ካለ ይህ መታበይ   ብቻ ሳይሆን እብደት ይሆናል፡፡
  • ልደቱን በወሎ ፖለቲካ መፈረጅም ኢዴፓን አለማወቅ ይሆናል፡፡ ግን ሀብታሙ እንዲህ የሆነው ባህር ማዶ ከተሻገረ በኋላ ወይንስ ከጅምሩ ፤ ዲያስፖራውንም መናቅ ይሆናል፡፡ ወይ አንድነት ስንት ጉድ ይዞ ነበር፤

2- ¾›„ Ó³†¨< ¨<gƒ&

  • የሕውት/ኢህአዴግ የሆኑ ኃላፊዎች ወደ ተቀዋሚው ጎራ አንዲመጡ ክፍት መሆን ጠቃሚ ነው በሚል አጠቃላይ መርህ ነበር፡፡ በዚህም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳና  ስዬ አብርሀ በብዙ ውይይትና ክርክር ዴሞክራሲያዊ በሆነ ውሳኔ ሊገቡ ችለዋል፡፡ ”ይህ አገላለጽ ፍጹም ውሸት ከመሆኑ በላይ አቶ ግዛቸው ዛሬም ከስምንት አመት በኋላ በጥፋታቸው የማይጸጸቱ መሆናቸውን ነው የሚረፈጋግጠው፤ ላስረዳ፤

ሀ-      የወያኔ ሰዎች ወደ ተቃውሞው ጎራ በመግባታቸው ተቃውሞ ባይኖረኝም ክፍት መሆን አጠቃላይ መርህ ያሉት ግን አንድነት ውስጥ ያልነበረ ስለመሆኑ በርግጠኝነት ስጽፍ በወቅቱ የነበረውን የመተዳደሪያ ደንብ በማስረጃነት በመጥቀስ ነው፡፤

ለ-  በብዙ ውይይትና ክርክር ሳይሆን በአቶ ግዛቸውና በአቶ አስራት ጣሴ ልመናና ደጅ ጥናት ነው የገቡት፤ ለዚህ ደግሞ አቶ ስዬ ለማባባበያና ለማማለያ በተዘጋጀለት የግዮን ሆቴል ግብዣ ላይ የተናገረውን ማስታወስ በቂ ነው፡፡ በፍጹም መታበይና ኩራት እኔ ስዬ አንድነት የምገባው ደንብና ፕሮግራሙ ከተስተካከለ ብቻ ነው ነበር ያለው በአጭሩ ሲገለጽ፡፡

ሐ-  የገቡት አቶ ግዛቸው አንደሚሉት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሳይሆን በህገ ወጥ መንገድ የፓርቲው ደንብና ፕሮግራም አቶ ስዬ በጠየቀው መሰረት ተለውጦ በአቶ ግዛቸውና አቶ አስራት የተንኮል መንገድ ነው፡፡

መ-   ሁለቱ ሰዎች ወደ አንድነት አንዲገቡ የተደረገው በወቅቱ መርህ ይከበሮች ይፋ አንዳደረጉት መረጃ የወቅቱን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስና የመርህ ይከበሮችን ጥያቄ ዝም ለማሰኘት ከማለም ነው፡፡ ይህም የተሳካ ይመስለላል በወቅቱ ይፋ ሆኖ የተመለከትነው ከምርጫ ቦርድ የተጻፈውና በወቅቱ የቦርዱ ጸሀፊ አቶ ተስፋየ መንገሻ ፊረርማ ወጪ የሆነው ደብዳቤ ከዛሬ ጀምሮ እድነትን ነን ብትሉ ወዮላችሁ የሚል ማስጠንቀቂያ የያዘ ነበር፡፡

  • ኢኒጂነር ይልቃልና ሌሎቹ የሄዱት በስዬ አብርሀና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አንድነትን ሲቀላቀሉ በተፈጠረ የሀሳብ ልዩነት ነው፡፤ በዚህ የሀሳብ ልዩነት ሌሎች ተዛማች ጉዳዮች የተቃውሞ ጽሁፍ ቀርቦ በዚህ መሰረት ብሄራዊ ምክር ቤት ኮሚቴ አቋቁሞ ጉዳዩን ከአስጠናና ጥልቅ ውይይት ከተካሄደ በኋላ የቀረበው የተቃውሞ ጽሁፍ ተቀባይነት ሲያጣ እነ ኢንጅነር ይልቃልና ቡድኖቹ ከፊሉ በራሳቸው ፈቃድ ከፊሉ በም.ቤት ውሳኔ የተሰናበቱ መሆኑን በወቅቱ የተጻፈው ቃለ ጉባኤ ያስረዳል፡፡ ሌላው ቢቀር እድሜ ከውሸት አይገራም?   ያሳዝናል ይሄ ሙልጭ ያለ ውሸት አቶ ግዛቸው ዛሬም ከስምንት አመት በፊት ከቆሙበት ቦታ ወደፊት ሆነ ወደ ኋላ ንቅንቅ ያላሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፤ ይህን ጉዳይ በተመለከተ በወቅቱ በቂ መረጃዎች እየተጣቀሱ ብዙ ተጽፏል ፣ጥቂቱን ላስታውስ፡፤

G- የሀሳብ ለዩነቱ የተጀመረው በሁለቱ ሰዎች ጉዳይ ሳይሆን አቶ ግዛቸው  ብርቱካንን የራስሽ ጉዳይ ነው፤ ይህ ፓርቲውን አይመለከተም በማለት ለወይኔ አረንጓዴ መብራት ባሳዩበት ግዜ ነው፡፡

K-ሁለቱ ሰዎች አንድነት ሲገቡ ዝም አንልሞች አልነበሩም፣

N የተቃውሞ ጽሁፍ የተባለው የተቃውሞ ሳይሆን በእነ /ፕ/ር መስፍን ተጽፎ አምስት የሚሆኑ ሰዎች የፈረሙበት መፍትሄ አመላካች ጽሁፍ ነበር፡፡ ይህ የቀረበለት ም/ር ቤትም አቶ ግዛቸው አንዳሉት ሳይሆን ጽሁፉን ከነባራዊ ሁኔታው ጋር አዛምዶ የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብለት በአቶ አክሉ ግርግሬ የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቁሞ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ ከመፍትሄ አመላካቹ ጽሁፍ ጋር እያገናዘበ መርምሮ ሀያ አንድ ውሳኔዎችን አሳላፈ፡፡ ነገር ግን በአቶ ግዛቸው መሪነትና በአቶ አሥራት ጣሴ ዘዋሪነት ይመራ የነበረው ቡድን እነዚህ ውሳኔዎች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ በማድረጉ የተወጠረው ከሮ ለመበጠስ በቃ፡በዚህ ወቅት እነ ስዬ አንድነት አልገቡም፡፡ ለምን ይዋሻል፡፡ አቶ ግዛቸው በስም የጠቀሱት በወቅቱ የምክር ቤቱ ጸሀፊ የነበረው አቶ በቀለ ወልደሚካኤል አቶ ግዛቸው የተናገሩትን ውሸት ለመድገም የሚያስችል የሞራል ዝቅጠት ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፡፡

S.አቶ ግዛቸው ኢ/ር ይልቃልና ቡድኑ በማለት ሲጽፉ ትንሽም አለማፈራቸው ይገርመኛል፡፡ ለምን ቢባል በወቅቱ ይልቃል የቡደን መሪ እንዳልነበረ ያውቃሉና ፡፡ ፖለቲከኞቻችን ጡረታ ወጥተውም እውነት የማይናገሩት ምን ቢለክፋቸው ይሆን፡፡

በመጨረሻም፣ስንጽፍም ሆነ ስንናገር ከእኛ በቀር ስለ ጉዳዩ የሚያውቅ ስለመኖሩ ማሰብ አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ ላለመሆን ወይንም ርጥቡ ሬሳ ደረቅ ያስነሳ እንዳይሆን ለማድረግ ያስችላል፡፡ ሲሆን ሲሆን ከመነሻው የሥልጣን ጥምንም ሆነ የነዋይ ፍቅርን ገታ አድርጎ ለእውነት መቆምይበጃል ፤ሲለጥቅ ደግሞ አመልካች ጣት የሚለ ውን የተዋቂውን ድምጸዊ ጥላሁን ገሰሰን ሙዚቃ ማስታወስ መልካም ነው፡፤ ሌላው አይን ውስጥ ያለችን ትንሽ ሰንጥር ለማመለክት ብእር ሲመዙ ራስ አይን ውስጥ ያለውን ግንድ የሚነግሩ የሚያመለክቱ አያሌ ብእሮች ከአፎታቸው ሊመዘዙ እንደሚችሉ ማሰቡ ጠቃሚ ነው፡፡

– ይገረም አለሙ

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *